የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዕውነታዎች
መግቢያ እና የአጠናን ዘዴ
የዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ዕውነታ ጥናት ዓላማ መፅሐፍ ቅዱስን እራሳችን በራሳችን በቀላሉ እንድናጠናው ይረዳናል፡፡ ይህን ትምህርት ስናጠናቅቅ እየሱስ በወንጌል ያስተማረንን ግልጽ ምስል እንዲኖረን ይረዳናል፡፡ እየሱስ ለሐዋርያቱ ወንጌልን ለአለም ሁሉ እንዲያስተምሩና ያመንቱንም በውኃ እንዲያጠምቁ አዟቸዋል፡፡ ይህን መፅሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዳጠናቀቅን በወንጌሉ ለማመን እና ለመጠመቅ እንደምንወስን ተስፋ እናደርጋለን ፡፡ ይህ የጅማሬ ትምህርት ነው፡፡ በተቻለን መጠን እግዚአብሔር ቃሉን እንዲገልፅልንና መረዳቱንም ይሰጠን ዘንድ በፀሎት እንጠይቅ! የኑሮአችንንም ሁሉ እንቆቅልሽ ለእግዚአብሔር በመንገር እርሱም እንዴት እንደሚመራን እንመልከት!
በዚህ መፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ በ 12 ክፍሎች ተከፍሎ የቀረበ ነው፡፡ ከዚህም በኋላ የመፅሐፍ ቅዱስ ዕውነታ ጥናት ውስጥ በስፋትና በጥልቀት የተብራሩ ርዕሰ እንመለከታለን፡፡ ሁሉም ትምህርት ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነፃ እና ምንም ዐይነት ገንዘብ በፍፁም አንጠየቅበትም፡፡
እየሱስ ዳግመኛ ስመጣ እና የእግዚአብሔር መንግስት በምድር ላይ ስትመሰረት በመንግስቱም ቦታ እንድናገኝ በዚህ ትምህርትም እናንተን ለመርዳት በእውነት ከልብ እንሰራለን፡፡ ስለዚሀም እንፀልያለን በዚህ ትምህርት ዙሪያ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልሶቻችሁን እንዲሁም ማንኛውንም አስተያየት በጉጉት በመጠባበቅ ነው፡፡
ትምህርቱን እንዴት ማጥናት እንችላለን?
ለንባብ ከተሰጡን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በሚገባ ከቀረበበው ትምህርት ጋር በማንበብ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ጥቅም ማግኝት እንችላለን፡፡
በእያንድንዱ የጥናት ክፍል መጨረሻ ላይ በምርጫ መልክ የቀረቡ የተወሰኑ ጥያቄዎች አሉ ስለ መልሶች እርግጠኛ መሆን ካልቻልን በቀረበው ትምህርቱን ማብራሪያ ደግመን እያመሳከርን ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ እንፈልግ፡፡ ነገር ግን ለትምህርቱ የቀረበውን ፅሁፍ በፍጥነት አንብበን መልሱን መልሱን ለመገመት መሞከር የምንጥርበት ምንም ምክንየት የለንም፡፡ በቂ የሆነ መረጃ እናንተን ትክክለኛ መልስ ለጥያቄዎች አንድታገኙ ተደርጎ ቀርቧል ይህም ይህን መፅሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ስናጠናቅቅ ለሚኖረን ጠለቅ የለ ትምህርት በቂ የሆነ መሰረት ሊሆነን ይችላል፡፡
ስለ መለሳችሁት መልሶች እርግጠኛ ስትሆኑ በተሰጠው አድራሻ ይላኩልን፡፡ መልሶቹም ለእርሶ የመፅሐፍ ቅዱስ የግል አስጠኝዎ በመላክ በመልሳችሁ ላይ አስተያየት በመፃፍ እና በማረም ለእናንተው ያሳውቃሉ፡፡
እናንተም በማንኛውም መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጉዳዮች ላይ ያልዎትን ተጨማሪ ጥያቄ የሆነ አስተያየት ብታደርሱን በደስታ አንቀበላለን፡፡
Carelinks Publishing, PO Box 152, Menai NSW 2234 AUSTRALIA www.carelinks.net
email: info@carelinks.net
ትምህርት ክፍል 1፡ መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስ ትልቁ ማረጋገጫችን ነው፡፡ አንደተብራራውም ደራሲውም የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ዐላማው በታላቅ ስልታን አስረግጦ ያሳየናል፡፡ ይህም የሚያረጋግጥልን ውሸት ከሆነ እንደ መፅሐፍ ቅዱስ የአለምን ህዝብ ሁሉ ወደ ስቃይ እና ወደ ተሳሳተ አቅጣቻ በመምራት ወደ ሐሰተኛ እምነት እንዲከተሉ ሊያደርግ ከሚችሉ መጸህፍት አንዱ እና ዋነኛው ይሆናል፡፡ ቢሆንም የመፅሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ እውነት ከሆነ እኛ በዚህች አለም ካሉት ታላቅ እና ውድ ነገርን ይዘናል ማለት ነው፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ እንደ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል የሠላምና የደስታን ቁልፍ ይዟል በውስጡም በጣም ግራ ለሚያጋቡ ጥያቆዎች ለምሳሌ፡- ስለ መኖራችን ትርጉም እና አላማና በትክክለኝነት እና በስህተት መካከል ስለሚኖረው ትግል የመጨረሻውን ውጤት ሙሉ በሙሉ መልስ ይሰጠናል፡፡
የመፅሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ
ጳውሎስ ስለ ብሉይ ኪዳን ጽሁፍ እንዲህ ብሏል፡: “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2ኛጢሞ 3፣ 16” የእያንዳንዱ መፃህፍት ቃል የተጻፈው በቀጥተኛ መለኮታዊ መሪነት ስር ነው፡፡ ሐዋሪያው ጴጥሮስም አስረግጦ ተመሣሣይ እውነታን እንዲህ ይነግረናል፡ “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። 2ኛ ጴጥ 1፣ 21”
ሁለቱም ወንጌላውያን የሚነግሩን የብሉይ ኪዳን ከእነርሱ ጊዜ በዘመናት ቀድመው የተጻፉት በመለኮታዊ ስልጣን እንደሆነ ነው የሚያረጋግጥልን፡፡ የዚህን መለኮታዊ ስልጣን ኃላፊነት የተሟላ ስምምነት በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርትን እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ ጸሀፊዎችም የጻፉት በተለያየ ገዜ እና በተለያየ የትምህርት ደረጃ፡ ሥራ፡ ልምድ እና የማህበረሰብ ደረጃ ቢሆንም የሁሉም ጸሐፊዎች ጽሁፍ በአንድ ሲጠረዝ አንድ እርስ በእርሱ የማይጣረስ እና ወጥ የሆነ አንድ ወጥ የሆነ መጽሐፍ ሆኗል፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ ለምን ተፃፈ
መፅሐፍ ቅዱስ የስው ዘር መቼ እንደ ጀመረ ይነግረናል እንዲሁም እንዴት የእግዚአብሔር የድነት ዕቅድ እውነት በሐሰት ላይ ሊኖረው የሚችለውን የመጨረሻ ድል እና ስለ ኃጥያት ክፋት ሙሉ በሙሉ መወገድ ይነግረናል፡፡ የመፅሐፍ ቅዱስ ዋና ዓላማ ዕድለኛ በሆነው የስው ዘር በእየሱስ ክርሰቶስ ድነትን የሚያገኙበትን መንገድ ማሳወቅ እና በዚህም አካሄድ መምራት ነው፡፡ ብሉይ እና አዲስ ኪዳን ሲጣመሩ የሚያሳየን የእየሱስ ብቸኛው የአለም ህዝብ ሁሉ አዳኝ እንደሆነ ነው፡፡ “ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል። የሐ 20፣31” የመፅሐፍ ቅዱስ ገጾች የምናገኝው ሁሉንም አስፈላጊ ትምህርቶች ለሠዎች ታላቅ መንፈሳዊ ሕይወትን እንዲያገኙ ያስችላል፡ የትክክለኝነት እና ስህትት መለኮታዊ ትርጉም እና የሰዎችን ኃላፊነት ለእግዚአብሄር እና ለእርሱ ተከታይ ሠዎች፡፡ 2ኛጢሞ 3፣ 15-17”
በመጨረሻም መፅሐፍ ቅዱስ ለእኛ የተስጠን በስፋት እና ዘርዘር ባለ መልኩ ወደፊት ምን እንደሚጠብቀን ስለዚህም የክርስቶስን መምጣት ተዘጋጅተን እንድንጠብቅ ያደርገናል፡፡ (የሐ 20 ፤ 31)
የመፅሐፍ ቅዱስ ይዘቶች
መፅሐፍ ቅዱስ የመጻህፍት ስብስብ ሲሆን ይህም በሁለት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፡፡ የብሉይ ኪዳን መፃህፍት የተጻፉት ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው፡፡ እናም የአዲስ ኪዳን መፃህፍት የተፃፉት ከክርስቶስ ልደት በኃላ ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ የ 66 መፃህፍቶች ስብስብ ነው፡፡ የእነዚህ መጽሐፍት ዝርዝርም የመፅሐፍ ቅዱስ መግቢያ ገፅ ላይም እናገኛለን፡፡ የተፃፉትም ወደ 40 የሚጠጉ የተለያያዩ ጸሐፊዎች ሲሆን ጽሁፉም ሲጠናቀቅ የ 1500 ዓመታትን ጊዜ ፈጅቷል፡፡ የፃፉትም በተለያያዩ ሐገራት እንደ እስራኤል፤ ግብፅ፤ ጣሊያን እና ባቢሎን ነበር፡፡
መጽሐፍቶቹ ሁሉ ወጥ የሆነ ሐሣብን ይዘዋል፡፡ እግዚአብሔር ለሠዎች ሊያደርግ ያቀደውን ከኦሪት ዘፍጥረት አለም ተፈጠረ ጀምሮ እስከዚህ ጊዜ ድረስ እንደተፃፈው ፡ “ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም። የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል” (የሐ.ራዕይ 11፣15)
-
ብሉይ ኪዳን
የብሉይ ኪዳን መጽሐፍቶችን በአራት ዋና ዋና ክፍሎች እንከፋፍለዋለን፡-
ሀ. የሙሴ መጻህፍት
የመጀመሪያው ዘፍጥረት ሲሆን ትረጉሙም የመጀመሪያው ማለት ነው፡፡ የሚነግረንም እግዚአብሔር ከዚህች ምድር ሰው ጋር የደረገውን ስምምነትን ነው፡፡ ከዚህም በመቀጠል ኦሪት ዘፀአት፤ ኦሪት ዘዳግም፤ ኦሪት ዘሌዋውያን እና ኦሪተ ዘኍልቍ፡፡ የሚነግሩንም እንዴት እግዚአብሔር አብርሐምን እንደጠራው እና ለእሱ እና ለእሱ ዘር ሐረግ ቃልኪዳን መግባቱን፤ የእርሱም ዘሮች ከግብፅ ነፃ መውጣት እና አሁን እስራኤል የምንላትን ምድር መስጠቱን ይነግረናል፡፡
ለ. የታሪክ መጻህፍት
እነዚህም መጻህፍት ከመጽሐፈ እያሱ እስከ መጽሐፈ አስቴር በእነዚህም የተጻፈው የእስራኤላውያን (አይሁዳውያን) ታሪክ ሲሆን እግዚአብጀሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ንግግር ያሳየናል፡፡
ሐ. ስነ-ፅሁፋዊ መፅሐፍት
ኢዮብ፤ መዝሙረ ዳዊት፤ መጽሐፈ ምሳሌ፤ መጽሐፈ መክብብ እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን የተሣተፉት በዕብራይስጥ(በእስራኤላውያን ቋንቋ) በስነ-ጽሁፋዊ ዘይቤ ነው፡፡ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችን ስለ እግዚአብሔር መንገድ እና የሠው ስሜት እና የሥራ ይዟል፡፡
መ. የትንቢት መጻሕፍት
ትንቢት ማለት የሚመጣውን ነገር ቀድሞ ማወቅ የሚችል ማለት ሲሆን እነዚህም የሚመጣውን ነገር መተንበይ ብቻ ሣይሆን እግዚአብሔር ምን እንደሚፈልግም ማወቅ ይችላል፡፡ ረጃጅም የትንቢት መፃህፍትን ኢሣያስ፤ ኤርምያስ እና ሕዝቅኤልን በመከተል ቁጥር ያላቸው አጫጭር የትንቢትን መፃህፍትን በማስከተል በትንቢተ ዘካሪያስ ያልቃል፡፡
-
አዲስ ኪዳን
አዲስ ኪዳን አራት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ነው፡፡
ሀ. ወንጌል
ለዚህም ውስጥ አራት የተለያዩ በእየሱስ ሕይወት ዚሪያ ያቶኮሩ ሲሆኑ የተፃፉትም በማቴዎስ፤ ማርቆስ፤ ሉቃስ እና የሐንስ ስሆን እያንዳንዳቸውም ስለ ወንጌል (የምስራች ዜና) በራሳቸው መንገድ ፅፈዋል፡፡
ለ. የሐዋሪያት ሥራ
ይህም የተፃፈው በሉቃስ የሚነግረንም ከእየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሣ በኃላ ስለተከስተው ክስተቶች ይነግረናል፡፡ በዚህም መፃህፍ እንደተነገረን እንዴት የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን እንደተመሠረተ እና ሐዋሪያትም የምስራች ቃን ለሮማውያን ግዛት ሁሉ አስተምረዋል፡፡
ሐ. የመልዕክት መጻህፍት
እነዚህም የተጻፉት ከተወሰኑ ሐዋርያት ሲሆን ይህም ቀድሞ ትንሽ ቅጥር ያላቸው ፤ተበታትነው የሚገኙ ጀማሪ አማኞችንና ቤተ-ክርስቲያንን ለማገዝ ነው፡፡
መ. የራዕይ መጻህፍ
የእየሱስ የመጨረሻ መልዕክት ሲሆን ይህም ለደቀመዝሙር የሐንስ በራዕይ ተሰጥቶታል፡፡
መፅሐፍ ቅዱስን የምናምንበት ምክንያት
-
እየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ስላመነ
እየሱስ ክርስቶስ የመፅሐፍ ቅዱስ ዓላማ መዕከላዊ ምስል እና እርሱም በተወለደበት ወቅት አዲስ ኪዳን አልነበረም፡፡ ይጠቀምባቸው እና ያጠናቸው የነበረው መፅሐፍት የብሉይ ኪዳን መጽሐፍትን ነበር፡፡ እየሱስም በእነዚህ መጻሕፍት አምኖበታል ትምህርቱም መሠረት ያደረገው በእነርሱ ላይ ነበር፡፡ እናም ያለምንም ጥርጥር እና ነቀፌታ ተቀብሏቸዋል፡፡
የሐ 5፣46-47 ሉቃ 24፣ 25-27 ማቴ 22፣ 29 ፤ ማር 7፣ 6-13 ኢየሱስ ስለ አብርሃም፣ ይሣቅ፣ ያዕቆብ፣ ዳዊት፣ ሠለሞን እና ስለ ሌሎች ከብሉይ ኪዳን ስለምናገኛቸው ሠዎች እና ትምህርቱንም መሠረት ያደረገው በእነዚሁ በዕውነታው አለም ባሉ ሠዎች መሆኑ እና ሁሉም የብሉይ ኪዳን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡
-
መጽሐፍ ቅዱስ በምንም መልኩ ሐሰት መሆኑን ማረጋገጥ አልተቻለም
ሁሉም የሰለጠነ አስተሣሠብና ቴክንሎጂ ዕድገት በጥቅሉ የሚያሳን መፅሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈሩት ሁሉ እውነት መሆናቸውን ነው፡፡ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጠላቶች በጣም ሊቅ የተባሉ ሠዎችን ጨምሮ የመጽሐፍ ቅዱሰን ሐሰተኝነት ለማረጋገጥ እጅጉን ጥረዋል ነገር ግን ሁሉም ያን ማረጋገጥ ሣይችሉ ቀርተዋል፡፡ የተወሰኑትም ስህተተኝነቱን ለማረጋገጥ ጀምረው በመጨረሻም አምነውበታል፡፡ በእርግጥም ዕውነታው እርስ በእርሱ አይጣረስም፡፡ በተፈጥሮ የምንጠብቀው የእግዚአብሔር ቃል እኛም ከምናውቀው ዕውነታ ጋር መስማማት እንዳለበት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለዘመናት የመቀመጡን አግባብም ብንመለከት ይህም ተጨማሪ ስለ እውነትነቱ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሰትነትን ለማረጋገጥ በተቻላቸው አቅም ሁሉ ተጠቅመው ተቋውሟቸውን በታላቅ ድል አድራጊነት ስሜት የሚገልፁም ሠዎች አልጠፉም ፡፡ ይህም የተወሰኑ ሠዎች እንዲያቆሙና እንዲከለከሉ ተደርጓል፤ ሙሉ በሙሉም ተቃጥሏል እናም ብዙ መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስን ስህተትነት ለማረጋገጥ ተፅፈዋል፡፡ ይህም ሆኖ ምንም ዐይነት መፅሀፍ በተከታታይነት እና ለተቃውሞ ታቅዶ ዐላማ አድርጎ የተዘጋጀ ቢኖርም ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱስ ሣይለወጥ ባለበት እንዳለ ይገኛል፤ ሊናወጥም ሆነ ሊበረዝ አልቻለም፡፡
-
የአርኪዮሎጂስቶች ግኝት የሚያረጋግጥልን መጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሆኑን ነው
የመጽሐፍ ቅዱስ የቀድሞው ታላላቅ ሠዋች ታሪካቸው እስካሁን መኖሩና በሰው ዘር ላይ የሚያሳድሩት ጫና ሊካድ የማይቻል ዕውነታ ነው፡፡ የአርኪዮሎጂስቶች ግኝት የሚያረጋግጠው ሮውሊንሰን፣ ላያርድ፣ስሚዝ፣ ውሊይ እና ኬንዮን በግብፅ፣በኒንቬህ፣በአስሪያ፣በባቢሎን፣በኡር፣በሲሪያ፣በሊባኖስ እና በእሰራኤል ሁሉም በሚገርም መልኩ የሚያረጋግጡልን የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ እውነትነትን ነው፡፡ በአለም ዙሪያ ሁሉ በሚገኙ ሙዚየሞች ለዕይታ እንደሚቀርበውና በግልፅ የሚያሳዩንም ይህን ዕውነታ ነው፡፡ ከእስራኤል ጋር በጦር የተዋጉና በነዚህም መካከል የተደረገው መንግስታዊ የመልዕክት ልውውጥ የሚያረጋግጥልን የመፅሐፍ ቅዱስ ስለነዚህ ክስተትና የቀድሞ ልማድና አከባባዊ ወግ የሠጠውን ማብራሪያ እውነታነት አረጋግጧል፡፡ ዛሬም ቢሆን አርኪዮሎጂያዊ ግኝቶች የሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን እውነትነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተጨማሪ ማረጋገጫዎችን በማግኝት ላይ ይገኛሉ፡፡
የአይሁዳውያን ኮፒስቶች ዋናውን ፅሁፍ ሲፅፉ ስለስጡት ጥንቃቄ የተሰጠው ሂስ እንደሚያሳየን የፈፀሙት ስህተት ጥንታዊ ፅሁፎች ግኝት የእነሱን ውድቅ አድርጎባቸዋል፡፡ የሚያስደንቀው የ 1947 ግኝት የ ሙት ባህር ጥቅል መጽሐፍ የሚያሳየን አሁንም እጅግ ጠቃሚ ተጨማሪ ማረጋገጫ በመሆን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታነትን አሳይቷል፡፡ እነዚህም የተወሰኑ መፃህፍት ቀድመው የነበሩና ከክርሰቶስ ልደት በፊት የሁለተኛውን ክፍለ ዘመን ወደኋላ ይመልሰናል፡፡ ከዕድሜያቸው መቆየት ባሻገር የተወሰነ ልነት ሊታይ የሚችለው በተወሰነ ፊደል አጣጣል አንፃር ብቻ ሲሆን ይህም በፍፁም የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ፣ ትንቢትና ታሪካዊ ሃቆችን ያላዛባ ነው፡፡ ስለዚህም የአርኪዮሎጂስቶች ሥራ የመጽሐፍ ቅድስን እውነታና ታማኝነትን በሚያስረግጥ መልኩ ያረጋገተ ሲሆን በዚህም በተዘዋዋሪም የሚያረጋግጥልንም በመለኮታዊ ስልጣን የተፃፈ መሆኑን ጭምር ያረጋግጥልናል፡፡
-
ትንቢትም የመፅሐፍ ቅዱስን እውነትነትን ያረጋግጥልናል
እግዚአብሔር እራሱ እንደ ትልቅ ወደር ስለሌለውና ፈፅመው ይሆናሉ ብለን ስለማንገምታቸው ነገሮች ላይ ያለውን ስልጣን ለማሳየት ትንቢትን መረጧል (ት.ኢሳ 46፣ 9-10 ፤ ት.ኢሳ 42፣ 9)
ከጊዜ ወደ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ከመቶ ዓመታት በኋላ ሊከሰት ስለሚችለው ነገር ነው፡፡ በማቶዎስ 2 እንደተፃፈው አንድ ጠቢብ ሠው ወደ እየሩሣሌም በመምጣት እንዲህ ሲል ጠይቆታል፡ "የአይሁድ ንጉስ ሊሆን የተወለደው እርሱ ወዴት ነው? " ሄሮድስም ይህንኑ ጥያቄ ሊቀ-ካህናቱን ይህንን ጥያቄ በጠየቃቸው ወቅት፤ ሁሉም በአንድነት እንዲህ ሲሉ መልሰውለታል፡ "በይሁዳ ቤተልሔም" ምክንያቱም ከ 100 ዓመታት በፊት በብሉይ ኪዳን መጻህፍት በአንዱ ተተንብዮ ነበር፡፡ (ት.ሚክያስ 5፣2)
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት በተጨማሪ በብዛት ከጥንታዊው መንግስታት ጋር የሚዛመዱና በስፋት ደግሞ ስለ አይሁድ በትንቢት ተነግሯል፡፡ አብዛኞቹ ጥንታዊ መንግስታት ከአለም ጉዳዮች ዛሬ ጠፍተዋል ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን አይሁዳውያን መቆየት ችለዋል፡፡ አሁንም አይሁዳውያን እንደ መንግስት እራሳቸውን ችለው ዛሬ መኖር ችለዋል፡፡ በአንፃሩም እነርሱን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እጅጉን ቢጣርም (ት.ኤርምያስ 30፣ 10-11) መጽሐፍ ቅዱስ በሠው ልጅ ተጽፎ ቢሆን ኖሮ በታሪክ አጋጣሚ ውስጥ በሆነ ቦታ ላይ ሐሰት በሆነ ነበር፡፡ ይባስ አይሁዳውያን አብረውን ዛሬም አሉ፤ በእራሳቸው ግዛት እስራኤል እናም በዋና ከተማ በሆነችው እየሩሣሌም ማዕከል በማድረግ ዛሬም ይገኛሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም ለነዚህ ሁኔታዎች ምክንያትን ይስጠናል፡፡ ይህም ሃያል ማረጋገጫ መጽሐፍ ቅዱስ በመለኮታዊ ስልጣን የተጻፈ መሆኑና ስለዚህም በፍፁም አይሣሣትም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈሰወ ቅዱስ መሪነት መጻፉን የሚያረጋግጡልን የተወሰኑ ማጠቃለያ ነጥቦች
-
መፅሐፍ ቅዱስ በመለኮታዊ ሃይል የተፃፈ መሆኑን የምናምንበት የተወሰኑ ምክንያቶችን ሰናጠቃልል፡-
-
የመልዕክቶቹ ወጥነት፤ ይህም እጅግ ቁጥር ባላቸው ግለሰቦች ከመፃፉም ባሻገር ረጅም ጊዜ ፈጅቷል፡፡
-
በሚያስገርም መልኩ ሣይለወጥ መቆየቱ
-
የአርኪዮሎጂስቶች ግኝት ማስረጃ
-
የመፅሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች እውን መሆን (ተጨማሪ ምሣሌዎችን በቀጣይ ትምህርተ ክፍል እንማራለን)
ሊሟሉ የሚገባቸው ሁኔታዎች
እኛ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ካስፈለገን እየሱስ እንደተናገረውልክ እንደህፃናት መሆን ይኖርብናል (ማቴ 11፣ 25) እኛም ሊኖረን የሚገባን እምነት እንደ ህፃናቱ መሆን ይኖርበታል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ዕውነታነት እና ጥበብ በእራሳችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈልገን የማግኝት ፍላጎትም ሊኖረነረ ይገባል፡፡ (ምሳሌ 2፣3-6) እና እግዚአብሄር ትዕዛዛት በተስማማ መልኩ እንዲሆንም ከልባችን መፈለግ ይኖርብናል፡፡
እየሱስም እንዳለው “ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።”(የሐ 13፣17) እና “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።”(ማቴ 7፣21) ሐዋሪያው ጳውሎስም እንድፃፈው “ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤” (ፊሊ 2፣12)
እንዴት አድርገን መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ማጥናት እንችላለን?
እንደማንኛውም የትምህርት አካሔድ ቋሚነት ባለው መልኩና በዕቅድ ላይ የተመሠረተ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡
ለመጀመር ያህል በዚህ የትምህርት ክፍል ውስጥ የቀረቡትን አማራጭ መከተሉ ጥሩ ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ እራሱን በሚገባ መግለፅ ይችላል፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ያነበብነው አንቀፅ መረዳት ያለብን በተፃፉበት ሁኔታ ሲሆን ያነበብነውም ከሌሎች የመፅሐፍ ቅዱስ አንቀጾች ጋር በማነፃፀር ሊሆን ይገባዋል፡፡
በዚህም ትምህርት በጥልቀት ስንሄድ እያንዳንዱ የምናምንባቸው መሠረታዊ ሃሣቦች በግልፅና በበጎ ጎኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታገዘ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ይህን መሠረት በማድረግ ሲታዩ አስቸጋሪ ወይም እርስ በእርሱ የሚጣረስ የሚመስሉ ጥቅሶችን ማብራራትና በግልፅ መረዳት ይቻላል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ የግረጌ ማጣቀሻ፣ አንድምታ አንዳነዴ ጠቃሚዎች ሆነው ብናገኛቸውም ይህን የሚያጠናቅሩት ግን በመለኮታዊ ሥልጣን አይደለም፡፡ ይህ የተጠናቀረው ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ያዘጋጁት ተሣስተዋል ማለት እንችላለን፡፡(የሐ 10፣ 35 እና የሐዋ 5፣ 29)
የዚህ ትምህርት ዓላማ በእራሳችን መጽሐፍ ቅዱስን እንድናውቅ መገዝ ነው፡፡ ስለዚህም ስለምንነቱ የምንቀበለው ነገር ይኖረናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ለመስማት እና ለመፈፀም ለሚስማሙ ሁሉ የዘላለማዊ ሕይወት ተስፋን ይሰጣቸዋል፡፡
ማጠቃለያ
-
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
-
መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሉን፡፡
-
በመጽሐፍ ቅዱስ አምነን ለእግዚአብሔር እስካልተገዛን ድረስ የዘላለማዊ ህይወትን እናገኛለን፡፡
ለንባብ የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
2ኛውጢሞ 3 ፤ 2ኛውጴጥ 1 ፤ ሉቃ 24 ፤ ሐዋ 28፣ 23-31 ኤፌ 4፣ 21- 32
ትምህርት ክፍል 1፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
የመጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ ያሉ እያንዳንዱ መጽሐፍ ደራሲው ማነው?
ሀ. ጳውሎስ ለ. ሙሴ ሐ. እግዚአብሔር መ. ዳንኤል
-
እየሱስ በኢማኡስ መንገድ ላይ ለሁለት ደቀ-መዘሙራን ስለ እራሱ እያብራራላቸው የነበረው ከየትኛው የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ ክፍል ነው?
ሀ. ከነብያት መጻሐፍት ሐ. ከመዝሙረ ዳዊት
ለ. ከሙሴ መጻሐፍት መ. ከመጻሐፈ ምሳሌ
-
የሙት ባህር ጥቅል መጽሐፍት የተገኝው በስንት ዓመተ ምህረት ነበር?
ሀ. 1749 ለ. 1794 ሐ. 1914 መ. 1947
-
ነብዩ ሚኪያስ እየሱስ የት ይወለዳል ብሎ ነበር?
ሀ. እየሩሣልም ለ. ቤቴል ሐ. ቤተልሔም መ. ባቢሎን
-
መጽሐፍ ቅዱስን ፅፎ ለማጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ወስዷል?
ሀ. 50 ዓመታት ለ. 15 ዓመታት ሐ. 1500 ዓመታት መ. 150 ዓመታት
-
እየሱስ እንደተናገረው "እነዚህን ነገሮች ካወቃችሁ የተባረካችሁ ናችሁ"
ሀ. ለሌሎች ብንነግር ለ. ብንፈፅም ሐ. ብናስብ መ. እርግጠኛ ብንሆንባቸው
-
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል መጻሕፍትን በውስጡ ይዟል?
ሀ. 66 ለ. 27 ሐ. 39 መ. 23
-
ጴጥሮስ በሁለተኛው መልዕክቱ ላይ ያጣቀሰው እርግጠኛ ቃል ምን ነበር?
ሀ. የንግግር ለ. የመዝሙር ሐ. የትንቢት መ. የእምነት
-
በሐዋ 28፣ 23- 31 ይህ ሲፃፍ ጳውሎስ ይኖር የነበረው በየትኛው ከተማ ነበር?
ሀ. ሮም ለ. ኤፌስዮን ሐ. እየሩሣሌም መ. አሌክሳንደሪያ
-
ስለ እግዚአብሔር እና ለዚህች ምድር ስላለው ዕቅድ እና ዓላማ ሙሉ በሙሉ ማወቅ የምንችለው ከየት ነው?
ሀ. የሙት ባህር ጥቅል መፅሐፍት ሐ. መፅሐፍ ቅዱስ
ለ. የአይሁዳዉያን ህግ መ. የአርኪዮሎጂስቶች ጥናታዊ ጽሁፍ
ትምህርት ክፍል 2፡ እግዚአብሔር
ስለ እግዚአብሔር ህልውና በርካታ አለመግባባቶች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ የነገረንን ከማየታችን በፊት እነዚህን የሚከተሉትን ሁለት ሐሳቦች እንመለከታለን፡፡
ስለ እግዚአብሔር ህልውና ላይ ያሉ አለመግባባቶች
-
የምልከታ መላምት (Watch argument) ፡
ቀድሞ የነበረ ነገር ግን አይተነው የማናውቀውን ነገር መሬት ወድቆ ብናገኝ እናነሳና ነገሩን በጥልቀት ማጥናት እንፈልግ ይሆናል፡፡ አንድ በአንድ የዕቃውን ክፍል በመፈታታት እና የተሠራበትን የተወሳሰበ ሂደት በመመልከት እንዴት ጥቃቅን ነገሮች እርስ በእርሳቸው መስራት እንደቻሉ በማስተዋል እጃችንን በአፋችን በመቻን ልንገረም እንችላለን፡፡
ይህ የተወሳሰበና አስቸጋሪ ዘዴ የተሠራ መሆኑንም ልንገነዘብ እንችላለን፡፡ ይህ ምልከታ በእርግጥም ሲነደፍ በዕቅድ ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ምልከታው እራሱን በፍፁም ሊፈጥር አይችልም፡፡ እያንዳንዱ አካላትም እንዲሁ በድንገት በአንድ ላይ አልተሰባስቡም፡፡ እውነታውም ይህ ነው የምንመለከታቸው ነገሮች ሁሉ መኖራቸው የሚያረጋግጡልን ወደድንም ጠላንም ለመኖራቸው በዕቅድ ንድፍ አውጥቶ የፈጠራቸው መኖሩን ነው፡፡
ህዋ የተፈጠረው በሚሊዮን በሚቆጠሩ ከዋክብት ነው፡፡ ያለንባት ምድር በእርሷ ዙርያ የምትዞራት አንድ ጨረቃ አላት፡፡ ፀሀይና ፕላኔቶች ሁሉም የዚህ እጅጉን በተዋበ ደግሞም ውስብስብና አስቸጋሪ ስርዐት አካል ናቸው፤ ከእያንዳንዱ አካላት ለእነርሱ በተዘጋጀላቸው ዛቢያ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይህ ከየትኛውም ከምናያቸው ነገሮች የተወሳሰበ ምልከታ ነው፡፡ ይህም እንዲሁ በአጋጣሚ የሆነ አይደለም፡፡ ለዚህም የግድ ንድፉን የነደፈ ይኖራል፡፡
“ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።” (መ.ዳዊ 19፣1)
-
የመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ
ስለ እግዚአብሔር ህልውና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስረግጦ ከሚነግረን አንዱና ዋነኛው የተፃፉ ትንቢቶች ናቸው፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ትንቢቶችን ስለ ነገስታት እና ሀገራት መሾምና ውድቀት እንዲሁም ስለ ግለሰቦችና ጥቃቅን እስከምንላቸው ክስተቶችን እንኳን ሳይቀር የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ በተለያዩ ሁኔታዎች እነዚህን ትንቢቶች ከመፈፀማቸው ከመቶ አመታት በፊት ነው፡፡ ይህም ሠዎች ሊያደርጉት ከሚችሉት አቅም በላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ብቻ ነው ሁሉንም ነገሮች የሚቆጣጠር ስለዚህም እነዚህ ትንቢቶችን ወደፊት በምንማረው የትምህርት ክፍል ውስጥ እናጠናለን፡፡ ይህን የማጥናታችን ጠቀሜታ እግዚአብሔር ስለ እራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ያሳወቀንን ለመፈተሸ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ምን ይነግረናል
“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” (ኦ.ዘፍ 1፣1)
“እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።” (ት.ኢሳ 45፣12)
“እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ። እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ።” (ኦ.ዘፀ 34፣6-7)
“ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።” (መ.ዳዊ 90፣2)
“ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም ከዘላለም ነህ።” (መ.ዳዊ 93፣2)
“የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።” (ቀ.ዜና 16፣26)
“አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥” (መ.ዳዊ 139፣2-3)
ዳዊት በዚህ ጥቅስ ላይ እንደሚነግረን አይምሮአችን የእግዚአብሔርን ታላቅነት ለመረዳት እጅግ ትንሽ መሆኑን ነው፡፡ (ቅጥር 6) ነገር ግን እግዚአብሔር እንደሚያየንና ሁሉን ነገር እንደሚያውቅ ከተረዳን ይህ ታላቅ ምቾት እና የጥንካሬያችን ምንጭ ይሆነናል፡፡
“እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።”(መ.ዳዊ 139፣9-10)
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የእግዚአብሔር ጆሮዎች ሁሌም የልጆቹን ጩኽት ለመስማት ክፍት ናቸው፡፡እንዲሁም እግዚአብሔር እንዳሳወቀንም፡”አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤”(ዕብ 13፣5 ፤ መ.ኢያ 1፣5)
-
የእግዚአብሔር አንድነት
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንድ እግዚአብሔር መኖሩ አስፈላጊ ነው፡፡ በተግባር ግን ብዙዎቹ በዚህ አያምኑም፡፡ ይህም በግልፅ እንደተቀመጠው የብሉይ እና የአዲስ ኪዳን ትምህርት ነው፡፡ እነዚህን ጥቅሶች በሚገባ እንመልከት፤ ት.ኢሳ 45፤5 ፡ 1ኛቆሮ 8፡6 እና ኤፌ 4፤6
ሐዋሪያው ጳውሎሰ ለጢሞትዮስ ሲፅፍለት፡ “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” (1ኛጢሞ 2፣5)
ኢየሱስም እራሱ ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ አስፈላጊነት አንክሮት በመስጠት ነግሮናል፡፡”እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”(የሐ 17፣3)
-
የሶስትነት (ሥላሴ) አስተምሮ
የተወሰኑ አሰተምሮ (ዶግማ) እንደ አጠቃላይ በአብዛኞቹ በአለም ዙሪያ ባሉ ክርስቲያን ተቀባይነት ያገኝው ዶግማ የስላሶ አስተምሮ ላይ ነው፡፡ ይህም በሮማ ካቶሊክ፤በግሪክ ቤተክርስቲያን እና በሁሉም ፕሮቴስታንት ማለት ይቻላል፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ እነርሱም እርስ በእርሳቸው የሚለያዩበት የተወሰኑ ነጥቦች ቢኖራቸውም በዚህ ላይ ግን ይስማማሉ እናም የሚያምኑት "እግዚአብሔር አባት፣ እግዚአብሔር ወልድ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዲሁም ደግሞ ሦስት እግዚአብሔር ሣይሆኑ ነገር ግን አንድ እግዚአብሔር ነው" ከዚህም በተጨማሪ የሚያምኑት እነዚህ ሦስቱም እኩል እና ህያው መሆናቸውን ነው፡፡
ይህ ትክክለኛ አስተምሮ ይሆን? ከሆነ ሣናውቀውና ሳንረዳው መቀበል ይኖርብናል? እንዴትስ ልናውቀው እንችል ይሆን? እንደሚታወቀው እግዚአብሔር እራሱን ሊያሳውቀን በፈቀደበት ቃሉ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ወደ መፅሐፍ ቅዱስ በመሔድ እና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዚህን ገናና አስተምሮ ሊደግፈው የሚችል ምንም አይነት ድጋፍ በየትኛውም ገፅ ላይ ማግኝት እንደማንችል በፍጥነት እናረጋግጣለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱሰ ሁሌም የሚያስተምሩት ስለ እግዚአብሔር አንድነት እንጂ ሦስትነትን አይደለም፡፡ ከዚህ በታች የምናገኛቸው ጥቅሶችም ይህንኑ በግልፅ ያሳዩናል፡ ” ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥” (ማር 12፣29)
“እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው” (ኦ.ዘዳ 6፣4)
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም ከእኔም በቀር አምላክ የለም በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።” (ት.ኢሳ 45፣5)
“ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።”(ኤፌ 4፣6 )
ከዚህም በተጨማሪ ብዙ ጥቅሶች መጥቀስ ይቻላል ሁሉም የሚነግሩን የእግዚአብሔርን አንድነትን እንጂ ሦስት መሆኑን አይደለም፡፡ ከላይ ከቀረቡ ጥቅሶች የመጨረሻው ጥቅስ በሚገርም መልኩ አስረግጦ ይነግረናል፡፡ በዚህ ወቅት ኢየሱስ ተወልዶ፡ ሞቶ ከሞትም ድል አድርጎ በመነሣት በአባቱ ቀኝ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ ጳውሎስ የሚነግረን አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ነው፡፡ እናም ይህ ማነው? የኦርቶዶክሰ የእግዚአብሔር ሶስትነት አባት፣ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ? አይደለም አባት ነው፡፡ ይህም ጳዉሎስ ያመልከው የነበረ እግዚአብሔር ነው፡፡
-
ኢየሱስ እግዚአብሔር ወልድ ነበርን?
ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት? ኢየሱስ እግዚአብሔር ወልድ አልነበረም? በዛሬ አገላለጽ የዚህ ቃል ተደጋግሞ መጠቀምን ስንመለከትና በሚደንቅ መልኩ የዚህ ቃል በመፃሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለመገኝት መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥም “የእግዚአብሔር ልጅ” እንጂ “እግዚአብሔር ልጅ(ወልድ)” አልተባለም፡፡ ከተፈጥሮአዊው አገባቡም መረዳት እንደሚቻለው ይህ አስተምሮ ምንም አይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ የአቴንስ ሐይማኖታዊ ዕምነት መሠረት አብ እና ወልድ እኩልነትንና ዘላለማዊነትን ያስተምራሉ፡፡ በዚህም ለየት ያለ አስተሳሰብ ስንመለከት አብ እና ወልድ ሁለቱም ለዘላለም የሚኖሩ ናቸው፡፡ ስለ እኩልነታቸው መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይነግረን ይሆን? ስለ ጉዳዩም በቀላሉ ልንረዳው በምንችልበት አግባብ ይነግረናል፤ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት እዚህየነበረው ክርስቶስ በእውን ከአብ ጋር እኩል ይሆን? እራሱ ይህን ጥያቄ እንዲመልስልን እንተውለት
“እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።” (የሐ 5፣30)
“ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤” (የሐ 7፣16)
“እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።” (የሐ 14፣28)
ከእውነታው መረዳት እንደሚቻለው የላከው አባቱ ነው (የሐ 5፤ 37-38፡ 20፡ 2 ፣ 1ኛየሐ 4፡ 14) እኩል ናቸው የሚለውን ሐሳብ ይፃረራል፡ ይህም ሲሆን ኢየሱስ ዳግም ስለ መማጫው ግዜ አለማወቁ ለዚህ ገናና አስተሳሰብ ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሆናል፡ ከሥላሴ አንዱ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ከእርሱ የተሸሸገ ነገር መኖሩን ለአንድ ሠው ይህን አምኖ ለመቀበል ይከብዳል፡፡ ይህ እኩልነት አልነበረውም፡፡ በቀድሞው ወቅት ብቻ ሣይሆን አሁንም ቢሆን የለም፡፡ የጳውሎስን ቃላት በጥልቀት ስንመረምረው እንዲህም ይለናል”እግዚአብሔር እና የጌታ ኢየሱስ አባት” ( 2ኛ ቆሮ 11v 31 በእርግጥም ኢየሱስ እራሱ ከሞት ከተነሣ በኃላ አባቱን እንዲህ ሲል አመላክቶታል “አምላኬ” (የሐ 20፤ 17) ተጨማሪ እውነታ እንደሚያሳየን “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”(1ኛጢሞ 2፣5) “ የሚያሣየን ተመሣሣይ ነገርን ነው፡፡
-
የክርስቶስ የወደፊት ሥልጣን
እነዚህን ማረጋገጫዎች በቀጣይም የምናያቸው ይሆናል፡፡ አስቀድሞ የወደፊት ሊሆን የሚችለውን በመመልከት የክርስቶስ የ 1000 ዓመታት በምድር ላይ የንግስናው ጊዜ ሲጠናቀቅ ምን እናይ ይሆን?
“በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል። ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤ ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።” (1ኛ ቆሮ 15፣24-28)
ይህም እንደሚያሳየን አብ ቀድሞ፣ አሁንም ሆነ ወደፊት ለኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ስልጣን በላይ ኃያል ነው፤ ከአባቱ ጋር እኩል ነው የሚል ሃሣብ ፈፅሞ አልቀረበም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው? በማቴዎስ እና ሉቃስ ወንጌል እንደተፃፈው ከድንግል የተወለደ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
“እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።” (ማቴ 1፣20)
“መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” (ሉቃ 1፣35)
በቅዱስት መጻህፍት እንደተፃፈው፤ እየሱስ በዚህች ምድር ሲኖር ተፈትኗል፤ ስቃይን ተቀብሏል እናም ሞቷል፤ በኋላም አባቱ ከሞት አስነስቶታል እናም በእግዚአብሔር ቀኝ ሊቀ ካህን እና አማላጅ ሆኖ ተቀምጧል” ዳግመኛ ወደዚህች አለም ላይ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመመስረት እስከሚመጣ ድረስ በዚሁ ይመጣል፡፡
-
የእግዚአብሔር ፍቅር
የኃያላን አምላክ እግዚአብሔር በሰው ከተሠሩ አማልክት የሚለይበት መለያ ባህሪ አንዱ እግዚአብሔር ለኛ ያሳየን እና የሠጠን ፍቅር ነው፡፡
እስቲ ቆም ብለን አንድ ቤተስብ ለልጆቻቸው የሚያሣዩትን ፍቅር እናስብእግዚአብሔር፡፡ እግዚአብሔርም ያሳየን ይህን ከመሠለው ፍቅርም በላቀ ደረጃ ነው፡፡
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (የሐ 3፣16)
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን የቻለ የትምህርት ክፍል ይወጣዋል፡፡ የሠዎች የድነት ፍላጎት በሠፊው እንመለከታለን ቢሆንም እግዚአብሔር ለዚህች ምድር ዓላማና የሠዎችን ፍላጎት እዚህ ጋር መዘርዘር ይጠበቅብናል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በግልፅ እንደሚያሣየን እግዚአብሔር ይህችን አለም ወደፊት የመለወጥ ሲኖረው፤ ምድራችንን የመረዙ ክፋቶችን በሙሉ ያስወግድልናል፡፡
-
እግዚአብሔር ለዚህች ምድር ስላለው ዕቅድ
በእስራኤላውያን ቀደምት ታሪክ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር እንደገለፀው፡ “ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።” (ኦ.ዘኁ 14፣21)
አሁን የምናያት ምድር በተገለፀው ደረጃ በእግዚአብሔር ክብር አልተሞላችም ነገር ግን የእግዚአብሔር ዓላማው ስለሆነ ይህም ይሆናል፡፡
ሐዋሪያው ጳውሎስ ለአቴንስ ህዝቦች ሲናገር እና ሲያስረዳቸው ይህቺን አለም በእግዚአብሔር በተሾመ ጻዲቅ ንጉስ ትመራለች፡፡ እናም ይህም እርግጠኛ የሚያደርገን የህም ኢየሱስን ከሞት አስነስቶታል፡፡
እስካሁን ድረስ በፃዲቅ ሠው አልተመራችም ነገር ግን ወደፊት ይሆናል፡፡ ይህም ጊዜ ሲመጣ የእግዚአብሔር መንግስት ይባላል፡፡ እናም ኢየሱስም በዚህ ይነግሣል፡፡የእግዚአብሔር ለዚህች ምድር ያለው አላማ በሚቀጥለው የትምህርት ክፍል በስፋት እናያለን፡፡ አንዱና ዋነኛው እግዚአብሔር ለሠዎች ያለውን ፍቅር ያሣየበት ስለእርሱ ዓላማ በመጽሐፍ ቅዱስ ሊያሳውቀን የቻለበትም አግባብ ነው፡፡ በተጨማሪም ደግሞ አንድያ ልጁን አሳልፎ በመስጠት ምን ያህል እንደሚወደን አሳይቶናል፡፡
-
መንፈስ ቅዱስ
ስለእግዚአብሔር በምናጠናበት ወቅት ስለ ታላቅነቱ እና ስራው ጋር የሚያያዙ ሁለት ነገሮችን ካላብራራ መልዕክቱ ሙሉ አይሆንም፡፡ “መንፈስ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኝ ሲሆን ትርጉሙም እግዚአብሔር ኃይል ማለት ነው፡፡ ይህንንም በሁለት ስፍራ እናገኛለን፡፡
“ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?” (መ.ዳዊ 139፣7)
“አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።” (መ.ዳዊ 143፣10)
-
መንፈስ ቅዱስ
“ቅዱስ” የሚለው ቃል ትርጓሜ “ልዩ፤ የተለየማለት ሲሆን ስለ መንፈስ ቅዱስ ስናስብ መጽሐፍ ቅዱስ እየነገረን ያለው ስለ እግዚአብሔር ኃይል ነው፡፤ ይህንንም ለተወሰኑና ልዩ ለሆኑ አላማዎች ተጠቅሞበታል፡፡ ይህን ቃል የተጠቀሰበትን ቦታዎች ሁሉ ስንመለከት ትርጓሜው ግልፅ ነው፡፡
የኢየሱስ እናት የሆነችው ማርያም ኢየሱስ የሚባል ልጅ እንደሚኖራትና ቀድሞ የተነገራት ሲሆን፤ መንፈስ ቅዱስም በላይዋ እንደሚፀልልባት እናም ሉቃስ የዚህን ትርጉም በአንክሮ ሲገልፅእንዲህም ብሏል፡” መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” (ሉቃ 1፣35) ይህን ጥቅስ እንመልከት፡፡ መልዓኩ ስለ ኢየሱስ መወለድ ሲገልፅ በእግዚአብሔር ልዩ ስልጣን በማርያም ላይ ታምራትን ሠረቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ችሏል፡፡
-
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አፃፃፍ
በሁተኛው የጴትሮስ መልዕክት ላይ ያየነው ጥቅስ እንዲህም ይላል፡ “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።” (2ኛጴጥ 1፣21) የነገረውን በእግዚአብሔር ልዩ ስልጣን ነብያት እንዲናገሩ እና የቅዱሳን መጻህፍት ጸሐፊያኑም የእግዚአብሔርን ቃል ማስፈር ችለዋል፡፡ የፃፉትም በእግዚአብሔር ሥልጣን በመመራት ነበር፡፡ “መንፈስ” የሚለው ቃል በመጀመሪያ በብሉይ ኪዳን በዕብራይስጥ ቋንቋ በአዲስ ኪዳንም በግሪክ ቋንቋ የተተረጎመ እንደመሆኑ ትርጓሜውም “እስትንፋስ” ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሠዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተዋል ስንል ሊባል የተፈለገው “እግዚአብሔር አስትንፋሱን ላኮላቸዋል” ከዚህ ትርጉም ጀርባ ይህ ቃል የሚያስተምረን እጅጉን ውብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ስልጣን ይነግረናል፡፡ ይህን ደግሞ ጳውሎስ ለጢሞትዮስ ለምን ቅዱሳን መፃህፍት የእግዚአብሔር አስትንፋስ ናቸው ያለበትን ምክንያት ይህ ስለሆነ ነው፡፡ “በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።” (2ኛጢሞ 3፣16)
አዲስ ኪዳን የሚነግረን የመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ለኢየስስ መስጠቱን ነው፡፡ በኋላም ደቀ መዛሙረቱም ይህ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፤ ይህም ታምራትን ይሠሩ ዘንድ አድርጓቸዋል፡፡ የማርቆስ ወንጌል የመጨረሻ ቁጥር(ማር 16፤20) የሚነግረን የዚህ ዓላማው ሐዋርያት የነገሩንን ለማስረገጥ ነው፡፡
ጳውሎስ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ አሰጣጥ መንገድ ነግሮናል፡፡ ከምንም በላይ ሊኖረንና ልናዳብረው የሚገባን ፍቅር ነው፡፡ ከስጦታዎች ሁሉ የበላይ ፍቅር ነውና፡፡ (1ኛቆሮ 12፤ 28-31) ቀጥሎም 1ኛቆሮ 13 እናንብብ፡፡
እግዚአብሔር በብዙ መንገዶች ለእኛ ያለውን ፍቅር አሳይቶናል፡፡ እኛም ደግሞ ባለን ህይወት እርሱን ደስ የሚያሰኝ ነገርን ብቻ በማድረግ ፍቅራችንን ልናሳየው ይገባናል፡፡
ማጠቃለያ
-
አንድ እግዚአብሔር አለ፡፡
-
እርሱም ፈጣሪ ነው- መጀመሪያና መጨረሻ የለውም፡፡
-
እግዚአብሔር ሁሉን ያያል ያውቃልም፡፡
-
እግዚአብሔር ቅዱስና ተወዳጅ ነው፡፡
-
እግዚአብሔር ዓላማውን በመጽሐፍ ቅዱስ አሳይቶናል፡፡
-
እግዚአብሔር ሥልጣንና ኃያልነት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጧል፡፡
-
ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን በመንፈስ ቅዱስ ተፅፈዋል፡፡
-
ኢየሱስ በማርያም ላይ ባደረባት መንፈስ ቅዱስ ስልጣን ተወለደ፡፡
-
የእግዚአብሔርን ማንነት መረዳት ለድነታችን እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡
ለንባብ የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ኦ.ዘፍ 34 ፤ ኦ.ዘፀ 34፣6-7 ፤ መ.ዳዊ 139 ፤ ት.ኢሳ 45 ፤ የሐ 17፣10-32 1ኛጢሞ 6 ና 1ኛየሐ 4
ትምህርት ክፍል 2፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
ሠማይና ምድር በማን ተፈጠረ?
ሀ. ባጋጣሚ ለ. በእግዚአብሔር ኃይል ሐ. በዘገምተኛ ለውት ሂደት መ. ቢንግ ባንግ
-
እውነተኛው እግዚአብሔር……
ሀ. የመፅሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሐ. የባአል ምስል
ለ. የግብፃውያን ጣዖት መ. አናውቀውም
-
ከሚከተሉት አንዱ ስለ እግዚአብሔር ህልውና ማረጋገጫ ነው?
ሀ. ብሔራዊ መዝሙር ሐ. ባህላዊ ታሪኮች
ለ. የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት መ. ተፈጥሮ
-
በመዚሙረ ዳዊት 139፤ 6 ጸሐፊው የተናገረው
ሀ. “እንዲህ ያለ ዕውቀት እጅጉን ለእኔ አስፈላጊ ነው”
ለ. “እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ያያልም እንዲሁም ያውቃል”
ሐ. “”እግዚአብሔር የኃያላን ኃያል ነው
መ. “ስቀመጥም ስነሣም አንተ ታውቃለህ”
-
መጽሀፍ ቅድስ ያስተማረን
ሀ. እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ናቸው
ለ. እግዚአብሔር አንድ ነው
ሐ. እግዚአብሔር ብዙ አማልክት በአንድነት
መ. እግዚአብሔር የለም
-
የሐንስ 3፤16 እንደሚነግረን ልጁን ለእኛ በመስጠት ያሳየን…
ሀ. ተስፋውን ለ.ፍቅሩን ሐ. እምነትን መ. ፍትህን
-
እግዚአብሔር ለዚህች አለም ሊያደርግ ያቀደው
ሀ. ለማጥፋት ሐ. በእርሱ ክብር ለመሙላት
ለ. እንዲሁ እንዳለች ለመተው መ. እግዚአብሔር ልጂ ለመስጠት
-
የእግዚአብሔር መንፈስ ማለት ምን ማለት ነው
ሀ. የእግዚአብሔር ኃይል ሐ. የእግዚአብሔር ነፃ ምኞት
ለ. የእግዚአብሔር ፍቅር መ. እግዚአብሔር ክብር
-
እግዚአብሔር መፅሐፍ ቅዱስ እንዲፃፍ ያስቻለው በምንድነው
ሀ. በታላቅነቱ ለ. በመንፈስ ቅዱስ ሐ. በእውነታው መ. ለክብሩ
-
በሐዋርያት ሥራ 17፤ 12 እንደምናነበው እነዛ ቤሪያ ያሉ፡
ሀ.ለእግዚአብሔር ምስጋና ይዘምራሉ
ለ. ዕለት ተዕለት መጽሐፍ ቅድስን ይፈልጋሉ
ሐ.ህዝቡን ያውካሉ
መ. የከተማውን ህዝብ በውጥረት ያስጨንቃሉ
ትምህርት ክፍል 3 - የእግዚአብሔር ዕቅድ እና ዓላማ
የእግዚአብሔር ፍቅር በባለፈው ትምህርት ክፍል በጥልቀት አይተናል፡፡ የሚወደውን አንድያ ልጂን አሳልፎ እስከሚሰጥ ድረስ ይህችን አለም ወዷታል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ያሳየን ፍቅር አንድሁ በዚሁ ልክ ልኛሳየው ይገባናል፡፡ በችልተኝነት ወይም በተራ ፍላጎት ግራ መጋባት አይኖርብንም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በጥልቀት ስለ እግዚአብሔር ቅዱስነት እና ፍትሐዊነት ያሳየናል ምክንያቱም ኢየሱስ ከሞት መነሣቱ የእግዚአብሔር ፍጹም ፍትሐዊነት እንዲሁም ለሰዎች ያለውን ያሳየናል ምክንያቱም ኢየሱስ አንዳችም ስህተት አልሰራም፡፡ ስለዚህም ሞቶ መቅረት አይገባውም (የሐ.ሥራ 2፤ 24) ለኢየሱስ ሞቶ በመቃብር መቅረት አግባብነት አልነበረውም እናም የእግዚአብሔር ከሞት አሰነስቶታለ፡፡
በተመሣሣይ መንገድ ይህቺ አለም ኃጥያት የነገስባት እና የክፋት መናህሪ የምትቀጥልበት አግባብነት አይኖረውም፡፡ የመጽሐፍ ምሣሌ እንደሚነግረን፡ “አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።” (መ.ምሣ 11፣1)
የሚከተሉትን ጥቅሶእ አንመልከት፡
“እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው፥ ኃይለኛም ታጋሽም ነው፥ ሁልጊዜም አይቈጣም።” (መ.ዳዊ 7፣11)
“ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤” (2ኛተሰ 1፣6-8)
ይህ የእግዚአብሄር ባህሪ የተገለፀበት መንገድ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቅድስና የዚህች አለም ክፋት እና ድክመት እንዲቀጥል አይፈቅድም፡፡ የእግዚአብሔርም ህች አለም የተሣሣተ ህግን በማውጣት አለምን እንዲመሯት አሳልፎ የማይሰጥበት ጊዜ ይምጣልህ፡ እንደ እግዚአብሔር አላማ አንድ ቀን አለማችን ፃዲቅ በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትገዛለች፡፡ (የሐ.ሥራ 17፤ 31) በእርሱ ንግስና ወቅትም አሁን ያለው የሠዎች ፈተና እና ይህ እግር የሆኑ ነገሮች ሁሉ መፍትሔ ያገኛሉ፡፡ ይህን የወደፊት ልዩ ወቅትን የእግዚአብሔር መንግስትን ያመላክታል፡፡
ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ መንግስትህ ትምጣ ብለው እንዲፀልዩ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አሁን መላዕክትን በሠማያት እንደሚታዘዙት ሁሉ በተመሣሣይ አኳሃን በምድር ላይም እንዲሆን ያደርጋል፡፡ (ማቴ 6፤10)
ይህ እንዲመጣ የተነገሩ ትንቢቶች
በመፅሐፍ ቅዱስ እንደምናገኝው በጣም በእርግጠኝነት ስለወደፊት ክስተት ይነግረናል፤ አንድ ነጠላ ወይም በእጅ የሚቆጠር ሣይሆን ነገር ግን በደርዘን የሚቆጠሩ ትንቢቶች አሉ፡፡ ስለ ግለሰቦች የተነገሩ ትንቢች የተወሰኑትም እስካሁን በትንቢቱ ወቅት ጀምሮ አልተከሰቱም፡፡ የረጅም ጊዜ እና የአጭር ጊዜ ትንት ሁለቱንም እናገኛለን፤ የነገሮችን ወደፊት መከሰት በትንቢት ተነግሯል፤ ከዚህም ቀደም በፍፁም ተከስቶ እንኳን በማያውቅ መልኩ፡፡ እጅጉን ወጣ ባለ ልማድ ይህም ሃገራት ሊኖራቸው የሚችለውን ቀድሞ ተተብዮ ይህም ልምድ በፍፁም የማይጠበቅና የማይገመት ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ በመፅሐፍ ቅዱስ እናገኛለን፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ትንቢቶች አብዛኞቹን በማይገመት መልኩ ሙሉ በሙሉ እንደተነገረው ትንበቱ ሲፈፀም አይተናል፤ ቀሪዎቹ ደግሞ አሁንም እየተፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ውጤት መሠረት በእርግጠኝነት እስካሁን ያልተፈፀሙት ትንቢቶች (ከእነዚህም ስለ እየሱስ ዳግመኛ መምጣት) በትክክለኛው ጊዜ ላይ እንደሚሟላው እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ይህ እንዲሆን የእኛ ድርሻ ምንድነው? ይህን ሠዎች በእራሳቸው ማድረግ ይችላሉን? በእርግጥ አይችሉም፡፡ አንድ መደምደሚያ ላይ ብቻ መድረስ ይቻላል፡፡ መፅሐፍ ቅዱስን የፃፉ ሠዎች ከእግዚአብሔር መመሪያን በመውስድ ነበር፡፡
“ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።” (2ኛጴጥ 1፣21)
በፍጽም መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ማጣጣል አይኖርብንም፡፡ ጴጥሮስ በዚህ ምዕራፍ እንዳሳርፈው የተናገረለትም “በጣም እርግጠኛ የሆነን ነገር የትንቢት ቃል ነው” ይህንንም ብርሃን በጨለማ ቦታ ላይ ከማብራት ጋር አነፃፅሮታል፡፡ (ቁጥር 19) ይህም በጣም ትክክለኛ ንፅፅር ነው፡፡ በአከባቢችን የምናገኛትን አለም ስንመለከት ሁሉም ግራ የሚያጋባ መስሎ ይታየናል ሁሉም ሁሉም ትክክለኛ ትርጉም እና ዓላማ ውጭ ይመስላል፡፡ ታሪክ በእራሱ ዝም ብሎ ልክ ያለ ዕቅድ እና ያለ ቅድመ ተከተል የሚከሰት መስሎ ይታየናል፤ ግልፅ ባልሆነ ግብ፤ የአለምን ውጣ ውረድ እጅጉን በአስቸጋሪ መልኩ ከተወቱ ሠዎች የሩቅ ዓላማ ያላት ትመስላለች፡፡ ቢሆንም መፅሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ስናጠና የሚያሳየን ከዚህ ስጋት ባሻገር የሠዎች ሁሉ ጉዳይ በቁጥጥር ስር ነው እናም ወደፊት እየተጓዙ ወደማይጠበቅ ከፍተኛ ፅንፍ ላይ ደርሰዋል፤ የማይጠበቅ ስንል ለሁሉም ማለታችን ሣይሆን ለጥቂቶች ነው፡፡
“ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል አለው።” (ት.ዳን 4፣32)
የህ ቃል የተነገረው ለባቢሎን ንጉስ ለናቡከደነፆር ነበር፡፡ እርሱም `እጅጉን ዕድለኛ ና ደስተኛ` ስም ኑሮት ሣይሆን ነገር ግን ሃያል አንባገነን የቀድሞ አለም መሪ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት የእርሁ ከተማ ባቢሎን ቁፋሮ ተካሂዶበታት መጽሐፍ ቅዱስ በተነገረለት አግባብ አቅም የነበራት ከተማ መሆኗ ተረጋግጧል፡፡ ወደ መቶ ሺህ ጡቦች ከቁፋሮው የተገኙ ሲሆን በእያንዳንዳቸው ላይ የኩራተኛው አምባገነን በወቅቱ የነበረችውን አለም ሲያስተዳደር የነበረው መሪ ስም ታትሞበታል፡፡ በእርግጠኛነት ናቡከደነፆር የአለማችን የመጀመሪያው አንባገነን መሪ በማያሻማ መልኩ ነበር ማለት እንችላለን፡፡ እናም ለዚህ ሠው እንዲህም ተብሎ ተሰይሟል “የኃያላን ሁሉ ኃያል የሠዎች መንግስት ገዥ” ነገር ግን ለእርሱ ከዚህም በላይ ተብሎለታል፡፡
የናቡከደነፆር ህልም
-
የሚያስደንቅ ራዕይ
ንጉሥ ናቡከደነፆር በዚህ ሰፊ ግዛት ገዢነቱን ከእርሱ ህልፈት በኃላ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ ሊመኝ ይችላል፡፡ እነዚህን መሰል ጥያቄዎች ካለመልስ ይቀጥላሉ ምክንያቱም ማንም ሠው ወደፊት ምን እንደሚገጥመን ማወቅ አንችልም ነገር ግን ናቡከደነፆር ከእግዚአብሔር መልስ ተሠጥቶታል፡፡ ይህንንም በትንቢተ ዳንኤል ሁለተኛው ምዕራፍ ላይ መንበብ እንችላለን፡፡ እባካችሁን እራሳችሁን በእርጋታ አንብቡት እጅጉን ለየት ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ነው፡፡
በዚህም ምዕራፍ የተነገረን ናቡከደነፆር በህልሙ በምስል መልክ ስለ ወደፊቱ መንግስት ተነግሮለታል፡፡ ታላቁ እግዚአብሔር ለምን ሓይማኖት የለሽ ንጉስን የሚያስጨንቀውን ስለ ወደፊት መናገር ለምን አስፈለገው የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፤ ለምንስ በህልም መንገሩን መረጠ እናም የታየው ራዕይ ግልፅ ባልሆነና ንጉሱ ሊረዳ በማይችለው ምስልስ ለምን ሆነ?
የሚከተሉትን ስንመለከት መልሱን እናገኛለን እናም ስለ ትንቢቱም በዝርዝር ያስተዋውቀናል እንዲሁም እየተፈፀመ ስለመሆኑም እናለን፡-
-
የናቡከደነፆር አስፈላጊነት በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ስለ ታላቅ ንጉስነቱ ብዙም ስፍራ ባይኖረውም እውነታው እንደሚያሳየን የእርሱ የበላይነት የእስራኤል ምድርንም ያካተተ ነበር እናም አይሁዳውያን(የእስራኤል ደቡባዊ መንግስት) ወደ ባቢሎንለ 70 ዓመታትበግዞት ተወስደው ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መሬት እና የእግዚአብሔር ህዝብ ለናቡከደነፆር መንግስት ተገዢ ሆነው ነበር፡፡
-
መረጃውንም በመስጠት የተጠቀመበት ዘዴም ለአይሁዳዊው ዳንኤል ቀድሞ በማሳወቅ እርሱም ብቸኛው ህልሙን ፈቺ መሆን ችሏል፡፡ ይህም እውነትነቱን እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል፡ “ሚስጥርን የምትገልፅ በሰማይ የምትገኝ እግዚአብሔር” በተለይም ደግሞ የእስራኤላውያን እግዚአብሔር፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ዓላማ ያሳየናል፡፡
-
በምሳሌያዊ አገላለፅ መረጃን ማስተላለፍ እጅጉን ውጤታማና ሠፊ ሃሣብን በተጠናቀረ አቀራረብ ማቅረብ የምንችልበት መንገድ ነው፡፡ በሰለጠነው ፖለቲካዊ ክስተቶችን በካርቱን ሰዕላዊ አገላለጽ ማሳየት የተለመደ ሲሆን ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህን ካርቱን የሚመጣውንና የአሁኑን ጊዜ ክስተት ፍንትው አድርጎ እንደሚያሳየን የናቡከደነፆር ህልም ብርሃኑን የወረወረው ገና ወደ ፊት የሚመጣውን ለማሳየት ነው፡፡
-
የህልሙ ትርጓሜ
ንጉሥ በህልሙ ያየው የሠው ምስል ከተለያዩ ብርቶች ውህድ የተውጣጣ ሲሆን - “የዚህም ምስል ራስ ጥሩ ወርቅ፥ ደረቱና ክንዶቹም ብር፥ ሆዱና ወገቡም ናስ፥ ጭኖቹም ብረት፥ እግሮቹም እኩሉ ብረት እኩሉም ሸክላ ነበረ። እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች ሲመታና ሲፈጭ አየህ።የዚያን ጊዜም ብረቱና ሸክላው፥ ናሱና ብሩ ወርቁም በአንድነት ተፈጨ፥ በመከርም ጊዜ በአውድማ ላይ እንዳለ እብቅ ሆነ ነፋስም ወሰደው፥ ቦታውም አልታወቀም ምስሉንም የመታ ድንጋይ “ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈጽሞ ሞላ” (ት.ዳን 2፣32- 35)
ይህ ሁሉ ማለት ምን ምንድነው? የዳንኤል ቃላት ለዚህ ከግራ መጋባት ጀርባ ያለውን ትርጉም ግልፅ ያደርግልናል፡፡ ምስሉ የወከለው የሠዎችን መንግሥታት ከዛ ዘመን ጀምሮ እስከሚቀጥለው ድረስ ያለውን ያሣያል፤ በወቅቱ ይታወቁ የነበሩ የአለም መንግስታት ለባቢሎን ንጉስ ታዛዥ ነበሩ፡፡ በወርቅ ራስ የተወከለው ማን ነበር “በሚቀመጡበትም ስፍራ ሁሉ የሰው ልጆችንና የምድር አራዊትን የሰማይ ወፎችንም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፥ ለሁሉም ገዥ አድርጎሃል “አንተ የወርቁ ራስ ነህ።” (ቁጥር 38)፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሁለተኛ ላ የነበረው “ብር” መንግስት ቀጥሎ ሶስተኛና አራተኛ፡፡
አራተኛውም መንግስት “እንደ ብረት ጠንካራ” ነገር ግን ጥንካሬው እየተሸረሸረ ሲዳከም፡ “እግሮቹና ጣቶቹም እኩሉ ሸክላ እኩሉም ብረት ሆኖ እንዳየህ፥ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየሁ፥ የብረት ብርታት ለእርሱ ይሆናል።የእግሮቹም ጣቶች እኩሉ ብረት እኩሉም ሸክላ እንደ ነበሩ፥ እንዲሁ መንግሥቱ እኩሉ ብርቱ እኩሉ ደካማ ይሆናል።ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ፥ እንዲሁ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም።” (ት.ዳን 2፣ 41-43) አሁን መመለስ የሚኖርበት ጥያቄ ፤ እንዴት ይህ የታሪክ እውነታ ከትንቢት ጋር ይነፃፀራል? ትክክለኛ መጣጣም ይታይበታል፡፡ እጅግ በጣም ተጣጥሟል ስለዚህም የተወሰን ሠዎች ሁለተኛው የዳንኤል ምዕራፍ የተፃፈው የተገለፁት ነገሮች ከተከስተ በኃላ ነው ለማለት ሞክረዋል፡፡ ይህ ስለ ትንቢት ትክክለኛነት በቂ ማሳመኛ ነው ነገር ግን በግልፅ ስህትት ነው፡፡ ምክንያቱም ትንቢቱ አሁንም በመፈፀም ላይ ነው! በተጨማሪም የዳንኤል መፅሐፍ ግልባጩ በሞት ባህር ጥቅል መፅሐፍቶች ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ መፅሀፍት መሀከል ሊገኝ ችሏል፡፡
-
የአለም ታሪክ ቅድመ ተከተል
አራት ታላላቅ የአለም ነገስታት ተከታትለዋል፡፡ ማንኛውንም ወቅቱን ያካተቱት የታሪክ መፃህፍት ብምናመሳክር እንዴት ባቢሎን በሜዲስ እና ፐርሽያ ስር እንደ ወደቁ ያብራራልናል፡፡ እነዚህ ጥምር ነገስታት በመጀመሪያ ሜዲያስ እና ፐርሺያ ቀጣዩን ስፍራ እንደያዘ ይነግረናል፡፡ የነዚህም የበላይነት ፍፃሜ ያገኝው የግሪክን ግዛት ያገኝው በታላቁ አሌክሳንደሪያ ነበር ይህም በምላሹ ለጠንካራ ኃያላን እጁን ሠጥቷል፤ ሮማውያን በማያጠያቅ መልኩ ከአራቱም ጠንካራ ነገስታት በጣም ለረጅም ጊዜ መግዛት የቻሉ ነበሩ፡፡
ሮም ለዘመናት ጫና ስያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አለማችን በፍፁም “እንደ ብረት ጠንካራ” የሆነና የሚንነፃፀር እንደ ሮም መንግስት ኃያል አልገጠማትም፡፡ ምን አይነት በምድር ላይ ያለው ኃይል ሊሰብረውና ሊወረው ይችላል? ምንም አይነት ነጠላ ኃይል አይችልም፡፡ ሮማውያን በማንኛውም ኃይል እጂ አልሰጡም፡፡ በባቢሎን፣ሜዶ-ፐርሽያ፣ግሪክ እና ሮም በእነዚህ ነገስታት የንግስና መስመር ላይ ሌላ እንዲህ ያለ ልላ ኃያል እና ታላቅ ንጉስ አልተነሣም፡፡
በመጀመሪያ ግዛቱ በሁለት ተከፈለ ምስራቃዊ ሮም ሚገዙትም ከኮንስታንቲኖፕል እና በምዕራባዊ ሮም የሚገዙት ከሮም ግዛት በመጀመር (ማስታወስ ያለብን ከናቡከደነፆር ያየው ሁለት ከብረት የተሰሩ ነገሮችን) በኃላም ሁለቱም ክፍያዎች ለውጨዊ ኃይል ተጋላጭ በመሆናቸውና የመፈራረስ ሂደትም በውስጣቸው ሲካሄድና ብዛት ያላቸው እራሳቸውን በቻሉ መንግስታት በዚህ በሮማውያን ይተዳደር የነበሩ ሠፊ ግዛት ውስጥ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ የተወሰኑት ጠንካራ፣የተወሰኑት ደግሞ ደካማ ነበሩ፡፡ እንዲህ አይነት የግዛት ጉዳይ ቀደም ሲል በፍፁም ተከስቶ አያውቅም ነበር፡፡ ምንም አይነት አምስተኛ ኃያል መንግስት በእነዚህ በተጠቀሱት አራት የንግሥና መስመር ውስጥ የተከተለና የእስራኤል ምድርን አካቶ የገዛ መንግስት የለም፡፡ ብዙ ሙከራዎች ቢደረጉም ነገር ግን ሁሉም ሙከራ አልተሳካም፡፡ የእስፔኑ ዳግማዊ ፊሊፕ፣ ቀዳማዊ ናፖሊዎን፣ ዳገውማዊ ቄሳር ዊልሔልም እና ሒላተር፡፡ ዛሬ እንደምናየው የአውሮፓ ሀገራት የእርስ በእርስ ትስስር ሁሉም በመተባበር ጥምረትን ማምጣት እየሞከሩ ነው፡፡ ዓላማው ምንድነው!(ማስታወሻ፡ አውሮፓ እስራኤልን አታካትትም) የትንቢቱ ቃላቶች ምንኛ እውነት ናቸው “እርስ በእርስ አይተባበሩም፤ ልክ ብረት እና ሸክላ እንደማይዋሃድ”
ማን ይሆን ይህን ሁሉ ሁለት ከግማሽ ሽህ ዓመታትን ቀድሞ ማወቅ የሚችል? ማን ይሆን በልበ ሙሉነት ወደፊት አደራት ታላላቅ ነገስታት እንደሚነግሱ አስረግጦ የሚናገር ነገር ግን ሦስት፣አምስት ወይም ስድሰት ሳይል? ይህን ሊያደርግ የሚችል ሠው ይኖር ይሆን ከዚህ ሁሉ ስለ ሠዎች ቅድመ ትንብያ እናውቃለን፣መመለስም የሚኖርብን አይኖርም፡፡ ማስታወሻ መያዝ ያለብን ዳንኤል ሁሉንም ስለስጠው መልዕክት ዕውቅና ለእግዚአብሔር ሰጥቶታል፡፡ “ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን ሸክላውንና ብሩን ወርቁንም ሲፈጨው እንዳየህ፥ እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አስታውቆታል ሕልሙም እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።” (ት.ዳን 2፣ 45)
ወንድም ሆነ ሴት ሁልጊዜም ቢሆን ይህንን ትንቢት ከተማርን በኃላ እግዚአብሔር እና በቃሉ ላይ መተማመናችንን በጠንካራ መሠረት ላይ እናደርጋለን፡፡ ይህንንም መተማመኛ ይህን ያነበብን ሁሉ እንጋራለን፡፡
-
አሁንም የተወሰኑት ትንቢቶች ወደፊት ይፈፀማል
በተጨማሪም በወቅቱ በትክክል የዳንኤል ቃላት መፈፀማቸው በታደሰ ፍላጎት ወደ መጨራሻው የትንቢቱ ደረጃ ለማየት ይመራናል፡፡ እንዴት አድርገን ይህን አስደንጋጭ ክስተት በምስሉ እግር ላይ የወደቀውን ድንጋይ መረዳት አንችላለን፣ ምስሉንም ወደ ብናኝነት ማድቀቁንና ቀጥሎም ታላቁን አለም የሞላ ተራራ መሆን መቻሉን?
ምስሉ የወከለው የሠዎችን መንግስት ከሆነ ድንጋዩ ሊወክል የሚችለው በግልፅ ሊታወቅ እንደሚችለው ከሠው ውጭ የሆነ ሌላ ይል ይህም የሠዎችን መንግስታት በማፈራረስ የራሱን ስልጣን በምድር ላይ ይመሰርታል፡፡ ይህም ወደፊት “በሠላም ይፈታል” ይህንንም ዳንኤል የሰጠው ማብራሪያ ነው፡፡ “በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።” (ት.ዳን 2፣44)
ይህ በመፅሐፍ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ይህን አለም ምንኛ እንደሚፈልግ ከገለፀበት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እሱም ለደነታችን ዕቅድ አውጥቷል፡፤ እናም የዕቅዱ ማዕከላዊ የሚያደርገው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በማስተዋል የሚያነቡ ድንጋዩ ምን ሊሆን እንደሚችል በቅፅበት ይለያሉ፡፡ “ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።” (ማቴ 21፣42-44)
ሁሉም ምልክቶች እንደሚያሳዩን በቶሎ ያ ድንጋይ ይወድቃል፡፡ በዚህች ምንም በማትጠብቀው አለም ላይ ይህን መስል ውድመት ይከሰታል፡፡ እኛስ ከዚህ ውድቀት እናመልጥ ይሆን? ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በሚመሠርታት በእግዚአብሔር መንግስትን በመጋራት በዚያ ተጠቃሚ እንሆን ይሆን?፤ኢየሱስ እራሱ ማዳን ሥልጣን አለው፡፡
ነገር ግን የዳንኤል ትንቢት ከማለፋችን በፊት ማስታወሻ ስለ ናቡከደነፆር ህልም ትምህርት ለዳንኤልም በራዕይ መታየቱንም በይበላጥ እናብራራው፡፡ በዳንኤል 17 እንደተፃፈው በምስል የተቀመጠው በመለወጥ እና በጥልቀት በመዘርዘር የአራት አራዊት ምስልን በመጠቀም አራቱ ታላላቅ መንግስታትን ከናቡከደነፆር ህልም ጋር በምስል አጣምሮታል (ት.ዳን 2፣44)ከ እግዚአብሔር መንግስት ጋር አቻ ሊሆን የሚችል ሌላ ጥቅስ በዳንኤል ቃል ተሰጥቷል፡፡ ት.ዳን 7፣ 27 ከዚህ እንደሚከተለው፡
“መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።”
-
የእግዚአብሔር መንግስት
ማንም ይህን የሚያነብ ስለ እግዚአብሔር መንግስት መምጣት ትንቢት በብሉይ ኪዳን በነዚህ አሁን አጣቅስን ባየናቸው ሁለት መዕራፍ ብቻ ነው የተፃፉት ብሎ ያስባል አንልም፡፡ ሌላም ተጨማሪ ምሳሌዎች በትንቢተ ኢሳያስ መጽሀፍ ላይ ስለ እግዚአብ ሔር መንግስት መምጣት በቀላል ቋንቋ ተነግሯል ይህም ማለት ያለምንም ምልክት ወይም ምስል፡፡ ምክንያቱም ስለ እግዚአብሔር መንግስት ብዙ ማጣቀሻዎች ከዚህ መፅሐፍ ነው፤ ኢሳያስ የሚጠቅሰውም የእግዚአብሔር መንግስት ነብይ ተብሎ ነው፡፡ የተወሰኑት ምሳሌዎችም፡፡
“ለንጉሡም ሕልሙን እንዲነግሩት ንጉሡ የሕልም ተርጓሚዎቹንና አስማተኞቹን መተተኞቹንና ከለዳውያኑንም ይጠሩ ዘንድ አዘዘ እነርሱም ገብተው በንጉሡ ፊት ቆሙ።ንጉሡም። ሕልም አልሜአለሁ፥ ሕልሙንም ለማወቅ መንፈሴ ታውኮአል አላቸው።ከለዳውያኑም ንጉሡን በሶርያ ቋንቋ። ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ ለባሪያዎችህ ሕልምህን ንገር፥ እኛም ፍቺውን እናሳይሃለን ብለው ተናገሩት።” (ት.ኢሳ 2፣ 2-4)
“እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።” (ት.ኢሳ 40፣ 10)
እኩል አስፈላጊ የሆነ ጥቅስ ደግሞ ስለ ድነት ሁኔታ ነው፡፡ አንድ የዚህ ምሣሌም ትንቢተ ኢሳያስ 66፣ 2
“እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።” (ት.ኢሳ 66፣ 2”)
-
የዳንኤል ማብራሪያ
ይህ ማብራሪያ የዚህ ትምህርት አዘጋጆች ግኝት አይደለም፡፡ ትንቢተ ዳንኤል 2 በእራሳችን እናንብብ፡፡ ዳንኤልም እንዲህ ይላል፡-
“ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን ሸክላውንና ብሩን ወርቁንም ሲፈጨው እንዳየህ፥ እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አስታውቆታል ሕልሙም እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።” (ት.ዳን 2፣ 45)
የእግዚአብሔር መንግስት
ሜዶ-ፐርሽያ ከባቢሎን እንደተከተሉ፤ ሮምም ግሪክን እንደተከተለች እንዲሁ አምስተኛ አጠቃላይ መንግስት እንደሌለ ሁሉ ስለዚህም የመጨረሻው የትንቢቱ አካልም ይሟላል፡፡
“በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።” (ት.ዳን 2፣ 44)
ድንጋዩ በዘመናት የሠዎች መንግስታት የሚወከለውን ምስሉ እንደጠፋው እና እርሱም በማደግና አለምን ሁሉ የሞላ ተራራ ሆኗል፡፡ ይህም ድንጋይ የሚወክለው የእግዚአብሄርን መንግስት ነው፡፡
ዳንኤልም ትንቢቱን ስያጠናቅቀ እንዲህ በማለት ነበር፡-
“ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን ሸክላውንና ብሩን ወርቁንም ሲፈጨው እንዳየህ፥ እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አስታውቆታል ሕልሙም እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።” (ት.ዳን 2፤45)
ይህም ብቸኛውና ከብዙዎቹ ትንቢቶች አንዱ ሲሆን ይህም በእግዚአብሔር ለዚህች አለም ያላ አላማ እንደሚሟላ ሙሉ መተማመን ይስጠናል፡፡
-
የብሉይና የአዲስ ኪዳን ትምህርት
በመጀመሪያ በባለፈው ትምህርት ላይ ያየነውን ሁለትሁሉ ከመፅሐፍ ቅዱሳችን እንመልከት ኦ.ዘኍልቍ 14፤ 21 አና የሐ.ሥራ 17፤ 31
የእግዚአብሔር ምንግስት ሲመሠረት መንግስቱን በሚመራበት አካሔድ መለኮታዊ ፍትህ ይኖራል፡፡ ምንም አይነት ጭቆናና አድሎ አይኖርም፡፡
“እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንምነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፥ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።” (ት.ኢሳ 11፤ 3-5)
በዚህ ጊዜ በኦ.ዘኁ 14፤21 የምናገኝው ቃል ገና የሚሟላ ነው፤ ልክ መላዕክት ኢየሱስ ሲወለድ እንደዘመሩለት ኢየሱስም በአለም ላይ ሁሉ ሲነግስ ይህ ሁኔታ ይኖራል፡፡
“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።” (ሉቃ 2፤14)
የመፅሐፍ ቅዱስ የመጨረሻው መፅሐፍ እንደሚገልፀው የሚኖሩ የሀገራት ጉዳዮች በእግዚአብሔር አላማ ውስጥ ይሟላል፡፡
“ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።” (ራዕ 21፤ 3-4)
-
ትክክለኛ ንጉስ
ጴጥሮስ ለሌሎች ደቀ-መዘሙር እንደ ዐፈ-ጉባኤ ሆኖ ነበር ኢየሱስን ጥያቄ የሚጠይቀው፡፡
“በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው።” (ማቴ 19፤ 27)
የኢየሱስም መልስ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እርሱም አፅንዖት በመስጠት ሲያስተምራቸው የነበረው መንግስቱም ትክክለኛ መንግስት ሲሆን ደቀ-መዘሙርቱም የዚህ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡
“ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።” (ማቴ 19፤ 28-29)
-
ኢየሱስ ዳግመኛ ይመጣል
ትክክለኛዋን መንግስት በምድር ላይ ለመመስረት እየሱስ በእርግጥ ተመልሶ ይመጣል፡፡ እርሱም ትምህርቱን ጨርሶ ወደ ሠማይ ሲያርግ፤መላዕክት ለደቀመዛሙርቱ ነግሯቸዋል፡፡
“ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” (የሐ.ሥራ 1፤ 11)
የኢየሱስ መመለስ እግዚአብሔር ለዚህች ምድር ያለውን በቀጣዩም የትምህርት ክፍል በጥልቀት ስለምንማረው የመጨረሻ ደረጃ አላማውን ዕውን ማድረግ ይሆናል፡፡ የኢየሱስ አብዛኞቹ በምሳሌ ያስተማራቸው ትምህርት እንደሚያሳየን ተመልሶ ሲመጣ ፃድቃን ይሸለማሉ፡፡ ስለዚህም ለእርሱ መምጣት ተዘጋጅቶ መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ማጠቃለያ
-
መፅሐፍ ቅዱስ የሚያብራራው ስለ እግዚአብሔር ፅድቅና ፍትህ እንዲሁም ስለ እርሱ ፍቅር ነው፡፡
-
እግዚአብሔር አለምን አሁን ባለችበት ግዛት እንድትቀጥል አያደርግም፡፡
-
እግዚአብሔር በአለም ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ይገባል እናም መለኮታዊ አገዛዝም በእየሱስ ንግስና ይመሠረታል፡፡
-
ስለ አለም ክስተት በት.ዳን 2 የተዘረዘረው በሙሉ መተማመን ስለ መጨረሻው የእግዚአብሔር ዕቅድ ሊመጣ እንደሚችል ይነድረናል፡፡
-
ኢየሱስ በእግዚአብሔር መንግስት ሊገዛ ተመልሶ ሲመጣ የእርሱ ተከታዮች በእርሱ መንግስት ቦታን ያገኛሉ ነገርግን ስለ መምጣቱ ተዘጋጅተው መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡
ለንባብ የተመረጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ት.እሳ 11 ፤ ት.ኢሳ 35 ፤ ት.ዳን 2 ፤ ማቴ 19 ፤ ማቴ 25
ትምህርት ክፍል 3፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
እግዚአብሔር እንዲሁ አለምን ወዷልና ……….
ሀ. ወቅቶችን ላከ ሐ. መላዕክትን ሠጠ
ለ. አንድያ ልጁን ሠጠ መ. ህግን ሠጠ
-
ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ በናቡከደነፆር ህልም መሠረት ሁለተኛው መንግስት የወከለው (ብር) የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ባቢሎን ለ. ግሪክ ሐ. ሮም መ. ሜዶ-ፐርሺያ
-
ናቡከደነፆርበህልሙ ሲጋጭ ያየው ነገር ምንድነው?
ሀ. ጣኦት ለ. ድንጋይ ሐ. እጅ መ. ሠይፍ
-
ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ ይዘምሩ የነበረው ስለ ምድራችን ሁኔታ እየሱስ ንጉስ ሲሆን መን እያሉ ነው?
ሀ. ማንኛውማ የፈቀደውን ያደርጋል ሐ. ማንም ሠው ስራን አይስራም
ለ. ማንኛውም ሠው ለሌላው ትሁት ይሆናል መ. በምድር ሠላም ይሆናል
-
ምድርን በፅድቅ የሚመራው ማን ነው?
ሀ. የእግዚአብሔር ልጅ ሐ. ሐዋሪያው ጴጥሮስ
ለ. ሐዋሪያው ጰውሎስ መ. ነብዩ ኤልሳ
-
በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 2 እንዳነበብነው “በእነዚህ የነገስታት ዘመን የሠማዩ እግዚአብሔር መንግስቱን ይመሠርታል…… “ ይህ የሚወክለው ምንድነው?
ሀ. 6,000ዓመታት ለ. የሕይወት ቆይታ ሐ.ዘላለማዊ መ. 100,000
-
ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ቃል ኪዳንን ሲገባላቸው ምን ተስፋ ሰጥቷቸዋል?
ሀ. ሀብትና ብልፅግናን ይጎናፀፋሉ ሐ. በእስራኤል ነገድ ላይ ትፈርዳላችሁ
ለ. ረዥማ ዕድሜ ይኖራቸዋል መ. ስኬታማ እና ደስተኛ እንደሚሆኑ
-
መፅሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር አላማ አሁን ባለችበት ግዛት ትቀጥላለችን?
ሀ. አዎ ለ. አይ ሐ. አይታወቅም መ. አልተገለፀም
-
ኢየሱስ በአሁን ወቅት የት ነው ያለው?
ሀ. በምድር ላይ ለ. በሠማይ ሐ. በመቃብር መ. በእስራኤል
-
ጳዉሎስ ለአቴንስ ህዝብ (የሐ.ሥራ 17) ሲያስተምር እግዚአብሔር ይህች አለም በፃድቅ ሠው እግዚአብሔር በመረጠው ትገዛለች ለዚህም ዋስትና ሰጥቶናል፡፡ ይህም ዋስትና የኢየሱስ?
ሀ. ልደት ለ. ሕይወት ሐ. ስቅላት መ. ትንሣኤ
ትምህርት ክፍል 4፡ ሞት
የተፈጥሮ አደጋ በማይለዋወጥ መልኩ የዜናዎቻችን ዋና ርዕስ ናቸው፡፡ ድንግተኛ እና አሰቃቂ ግድያን የመስማት ፍላጎት እጅጉን አይሏል፤ ይህ ለውስጣችን ሠላም አይስጠንም፡፡ አሁን ቆም ብለን ቀድመን ያየናቸውን ሁለት አረፍት ነገሮችን እናንብ፤ ከ 25-30 ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ይገመታል ( ይህም ከ 6,250 በላይ ሥዝብ በሠአት ወይም 150,000 በቀን) አንድ ቀን እኛም ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እንሆናል! እንድ ዕድል ሆኖ ከእነዚህ በአንዱ አሰቃቂ አደጋ አልተጋለጥንም ማለትም አንፃራዊ አነስተኛ ሞት በሚከሰትበት አካባቢ ሆነን ይሆናል፤ ነገር ግን በአንድም ወይም በሌላ ተራችን ቀን የዕለት ተዕለት ሩጫ ሊቆም ይችላል፤ አለምም ያለ እኛ ጉዞዋን ትቀጥላለች፡፡ በዚህም ምክንይት ሞት ዋናው አስፈላጊ ትምህርት መሆን ችሏል፡፡
የሞት ትምህርት ለእነዚህ አይነት ጥያቄዎች ያስነሣል “እኔ ማን ነኝ? ስሞት በእኔ ላይ ምን ይከሰታል? እናም እኔበእግዚአብሔር የፍጥረታት አላማ ውስጥ እኔ ምን ስፍራ አለኝ?”
በሞት ዙሪያ የሚነሱ አስተሳሰቦች
በመሠረቱ ሦስት አይነት አስተሳሰቦችን እናገኛለን፡-
-
ችላ ብሎ መተው
-
አመለካከታችን ይሆናል ብለን እንደምናስበው አይነት አለመሆኑ
-
ከእውነታ ጋር ተጋፍጦ ማምለጫ መንገድ መፈለግ
ከዘህ በታች አንድ በአንድ በዝርዝር ሶስቱንም እንመልከት
-
ችላ ብሎ መተው
ይህ ያስተሳሰብ ዝንባሌ በምዕራባዊያን ባህል ተፅዕኖ ያደጉ ሠዎች ሲሆንቁስ ላይ ያተኮረ ሕይወት ፍልስፍና ቀደምት የምዕራባዊያን ማህበረሰብ የሕይወተወ ፍልስፍና ነው፡፡
ማዕከል የሚያደርጉትም ሣይንስን ነው፡፡ በሣይንሳዊ አቀራረብ የሕይወትን ችግር ለማትናት የሚከተሉት መለኪያቸው በዚህ ዘዴ ነው፡፡ ሙሉ መረጃ ሣይንራቸው እራሳቸውን ለሣይንሣዊ ዘዴ አሳልፈው በመስጠታቸው በከፍተኛ ደረጃ ከዕውነታው ዕርቀዋል፡፡
ሣይንስ በፈጠረው ግራ አጋቢ እንዲሁም አስደናቂ አቅጣጫዎች ብዙ ሠዋች በዚህ ታውረዋል፡፡ ስለ ሞት ያላቸውን ሐሳብ በሙሉ በተቻላቸውአቅም ሁሉ ከአዕምሮአቸው አስወግደወደዋል፡፡
-
በአመለካከታችን ይሆናል ብለን እንደምናስበው አይነት አለመሆኑ
ይህ በብዙ ዋናዋነ ሐይማኖቶች የዕድሜ ልክ የአስተሳሰብ እይታ ሲሆን፤ ሞት የሚባለው የሕይወት ፍፃሜ ሳይሆን ነገር ግን ወደ ዘላለማዊነት የመግቢያ ዋና መግቢያ ነው፡፡የዚህ የተለየ መልክ ያለው ሠው “ህያው የሆነ ነብስ” አለው ከሚል መነሻ ሃሳብ የመነጨ ስሆን ይህም ማለት ደግሞ በሠው ውስጥ አንዳች የማይሞት ነገር እንዳለ አካልን ለቆ በመውጣት በተለየ መልኩ ሕይወትን ይቀጥላል፡፡
ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ ካለ፤ን የኑሮ ልምድ ሆነ ከሐይማኖታዊ መፅሐፍት ማረጋገጥ አልተቻለም ፤ ከመፅሐፍ ቅዱስ ወጣ ባለ መልኩ (2ኛ ጢሞ 3፣ 16) በተሟላ መልኩ ባልቀረበ መረጃ ያለ ምንም መሪነት በራሳቸው አዕምሮ እየተነዱ በጨለማ ሕይወት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ያለምንመ የቃላት ምልልስ ከአንድ ግለሠብ አዕምሮ ጋር በቀጥታ የሚደረግ ሥነ-ልቦናዊ እና እጅጉን የረቀቀ የስሜት ሕዋሳትን የሚመረምር ጥናት በቅርቡ የተገኝ ግኝት እንደሚያረጋግጥልን ከሳይንስ ይልቅ ለሠዎች የቀረበ ስሆን ነገር ግን አንድ ሠው ሲሞት ከእርሱ ሣይሞት በሕይወት የሚቀጥል አካል መኖሩን አላረጋገጡም፤ ሠውም ፈጣሪው በሆነከእግዘጀአብሔር ታማኝነት ያለውን ራዕይ በሞት ዚሪያ ሊሰጠው ይገባል፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ ብቸኛው ይህን የሚነግረን መፅሐፍ ነው፡፡ ይህም ሠዎች እውነታን እንዲጋፈጡ ያደርጋቸዋል፡፡
-
ከእውነታ ጋር ተጋፍጦ ማምለጫ መንገድ መፈለግ
-
ህያው ሕይወት
በመጽሐፍ ቅዱስ በአንዲትም ስፍራ ላይ ሰው ከሞት በኃላ ህያው የሆነ ነፍስ አለው የሚል ሃሣብ ማግኝት አንችልም፡፡ ይህ ለኦረቶዶክስ ክርስትና አማኞች ሊያስደነግጥ የሚችል ነው፡፡ ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ፡፡
“ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና ሙታን ግን አንዳች አያውቁም መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም።አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።” (መ.መክ 9፣ 5 ና 10)
ይህ እውነታ ብዙም ምቾት የማይሠጥ ሲሆን ነገር ግን ይህ በሚገባ እንደሚያስረዳው አንድ ሠው አፋጣኝ የማምለጫ ፍላጎቱን መቀስቀስ ያስታውሰናል፡፡
-
ድኅነት
እግዚአብሔር እንደገለፀው “እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።” (ት.ኢሳ 66፣ 2) “ትሁት” ማለት የትዕቢት ተቃራኒ ነው፡፡ “ላጠፋው ጥፋት ከልብ ይቅረታን የሚጠይቅ” የሚለውም ተመሣሣይ ፍችን ይዟል ነገር ግን ለፈፀምነው ጥፋት ይቅርታን የመጠየቂያ ዘዴ ነው፡፡
ሠው በተፈጥሮው ትዕቢተኛ ፍጡር ነው፡፡ የህያው ነፍስ ባለቤትነት ፍላጎት ስወለድ የገኝው ትዕቢት ውጤት ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉን እውነታ ማወቅ ከፈለግን ቀደም የተፀነሱ አስተሳሰቦችን በሚገባ ወደ ጎን መተው ይኖርብናል፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሐሳብ ሌነቶች ላ ግትር ባለመሆን እና አግዚአብሔር ለሠው ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ያሣወቀንን በእርጋታ ግምት ውስጥ በማስገባት መመልከት ይኖርብናል፡፡ የሠው ልጅ ተፈጥሮ
መፅሐፍ ቅዱስ በዚህ ሠፊ ትምህርት ከሥሩ ጀምሮ በሚገባ ይነግረኛል፡፡ ከሠው ልጅ መፈጠር ጀምሮ ፣ ሞት እንዴት እንደመጣ ይነግረናል፡፡ ስለ መጀመሪያው የሠው ዘር አዳምና ሔዋን የተፃፈው ምንመ ዐይነት የሐሰት መረጃ የለውም! የመጽሐፍ ቅዱስ የመክፈቻ ምዕራፍ ላይ የተጠቀሰውን እውነታውን በጥልቀት መረዳት ይቻላል፡፡ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።” (ኦ.ዘፍ 2፣ 7)
የአዳምን አካላት የተሠራው ከሁሉም ጥቃቅን ነገሮች ላይ በመመስረት ነው፤ እነዚህም ቅንጣቶች ቅርጽ የያዙት የሁሉም የበላይ በሆነው ፈጣሪ ሲሆን ይህም እጅጉን የሚያስደንቀውን የተወሳሰቡ የሠውን አካላት ፈጥሯል፡፡ሁሉም የእራሳቸው ተግባር አና እርስ በእራሳቸው የተቆራኙ ናቸው፡፡ በመርህ ደረጃ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ እጅግ አስደናቂው ውህደት ዛሬም ቢሆን በማህፀን ውስጥ በፅንስ ዕድገት ላይ ይህ ይከሠታል፡፡ከአፈር አካላቱን ያገኝው አዳም ሕይወትን እግዚአብሔር ሠጥቶታል “በአፍንጫው የሕይወትን አስትንፋስን ሰጥቶታል”
ነፍስ
ሕይወትን በትክክል ትርጉሙን ወይም ምንነቱን መግለፅ ይከብዳል ነገር ግን እንደሚታወቀው ለመረዳትበቀላሉ ይቻላል፡፡
“ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።” (ያዕ 2፣ 26)
“ነፍስ” የሚለው ቃል በስፋት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (በይበልጥ በቀድሞው ትርጉም) ለሠውም ሆነ ለእንስሳት አፈጣጠር ተጠቅሷል፤ ይህም ሲተረጎም “አዕምሮ” ፣ “እንስሳ”፣ “ተፈጥሮ” ነገር ግን በፍጹም በማንኛውም አግባብ ስለ ህያውነት የተነሳ አሣብ የለም፡፡ በመፅሐፈ መክብብ 3፣ 19-20፡
“የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው ድርሻቸውም ትክክል ነው አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም።ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል ሁሉ ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል።”
ነፍስ ከሠው ይሁን ከእንስሳ አካል አካል ተለይቶ መኖር አይችልም፡፡ ከላይ ያጣቀስነው ጥቅስ እንደሚያሳየን ሠው ሙሉ በሙሉ ሕይወቱ በእግዚአብሄር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሕይወት እስትንፋስን ዌም መንፈሱን ከሠዎች ሲያወጣ፡ “ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ።” (መ.ዳዊ 104፣ 29) ይህን ሁላችንም ልንረዳው ይገባናል፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች የሚያምኑት ሠው ሊሞት የማይችል እና ነፍስ ሲኖረው ከሞትም በኃላ ይኖራል፡፡ ይህ ግን የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም፡፡ ይህ በእርግጥም በኤደን ገነት የእባቡ ውሸት ነበር፡፡ ለሔዋን እንዲህ አላት “ሞትን አትሞቱም”ይህ እግዚአብሄር ለአዳምና ሔዋን ካላቸው ጋር በቀጥታ የሚነፃጸር ነው፡፡
ዕዮብ 34፣ 14-15 የሠው ልጅ በሕይወት ለመኖሩ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር ላይ በመደገፍ መሆን እንዳለበት ያረጋግጥልናል፡፡ “የፈረሰውን ለራሳቸው ከሚሠሩት ከምድር ነገሥታትና መካሮች ጋር፥ወይም ቤታቸውን ብር ከሞሉ ወርቅም ካላቸው መኳንንት ጋር፥” (ኢዮ 3፣ 14-15) ህም አንድ ሠው ሲሞት ወደ ሠማይ እንደማይሄድም ያረጋግጥልናል፡፡ የሐ 3፣ 13 ብንመለከት በይበልጥ ይህን ቃል ብንመለከት “ወደ ሠማይ የወጣ ማንም የለም” ሠው በኃጥያት ምክንያት ይሞታል፡፡ “እነሆ፥ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ደግሞ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።.... እርሱም ቀማኛና ደም አፍሳሽ ልጅ ከዚህም ሁሉ አንዳቸውን የሚያደርገውን ቢወልድ፥ (ት.ሕዝ 18፣ 4 ና 20) እናም በሮሜ 3፣ 23 እንደምናገኝው፡፡ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤” (ሮሜ 3፣ 23)
ስለዚህም ሁሉም በቀኑ ይሞታል እስከ ሙታን ትንሣኤም ምንም የሚያውቀው ነገር አይኖርም 1ኛቆሮ 15 ስለዚህም በተወስነ መልኩ ስለ ሙታን ትንሣኤ ተስፋ ያብራራልናል፡፡
ሠው - እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ ሊኖር የተፈጠረ
የሠው ልጅ መፈጠር አላማው እንደልሎች ፍጡራን ሁሉ የእግዚአብሄር ፍቃድ ለማድረግ ነው፡፡(ፊሊ 2፣ 13)
ከእንስሳት አፈጣጠር በተለየ መልኩ ሠው ነፃ ምኞት ተሰጥቶታል፤ ለእግዚአብሄር የመገዛትም ሆነ ያለመገዛት ምርጫ የእራሱ ነው፡፡ ይህም እጅጉን የሚያስደንቅ የሠው ልጅ በነፃ ፍቃዱ እግዚአብሄር ምን ያህል ደስተኛ ሊሆን እንደሚችል፡፡ የሠው ልጅ በነፃ ፍቃዱ ከእራሱ ይልቅ ለእግዚአብሄር ለመገዛት ቢመርጥ እግዚአብሄር ምን ያህለ ሊደሰትብን እንደሚችል መገንዘብ እንችላለን፡፡ በገዛ ፍቃዳቸው ልጆች ለወላጆቻቸው ሲታዘዙና ሲያከብሯቸው የሚስጣቸውን ደስታ በዚህ ዝቅተኛ ደረጃ ማየት እንችላለን፡፡
የሠው ውድቀት
የሠው ልጅ በዚህ የነፃ ፍቃድ ምን እንደሚያደርግበት ለማየት፤ እግዚአብሄር አንድ ቀለል ያለ ህግ ለአዳምና ሔዋን ሠጥቷል፡፡ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” (ኦ.ዘፍ 2፣ 16-17)
የሠው ልጅ በኃጥያት ወድቋል ስለዚህም በእራሱ ላይ የሞትን ደብዳቤ አምጥቷል፡፡ አዳም እና ሔዋን እባቡ ባቀረበላቸው “እንደእግዚአብሄር ክፉንና ደጉን ትለያላችሁ” የሚለውን ሃሣብ ተፈትነዋል፤ ምክንያቱም ፍሬው ለአይን የሚያጓጓ እና ለመብላትም መልካም ነበር፡፡ በዚህም ምክር የእራሳቸውን ፍላጎትና ትልቅ ጉጉት ሊያሸንፋቸው ችሏል፡፡ እነዚህ ሁለት ባህሪያት ከዛዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሠው ልጅ ባህሪ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡ በጥንቃቄ እባቡን ሔዋንን ለመፈተን የተጠቀመበትን ቃላት እንመልከት፡ “ሞትን አትሞቱም” (ኦ.ዘፍ 3፣ 4)፡፡ ይህ ውሸት ነበር፤የእግዚአብሄርን ቃል መካድ ነው፡፡ እናም ይህ ውሸት ከዛ ጀምሬ እስከ ዛሬም ድረስ ሠው ሠራሽ ሐይማኖትን እንዲፈጥሩ መሠረት ሆኗቸዋል፡፡
የሠው ልጅ ፍርድ
አዳም እና ሄዋን ከእግዚአብሄር ፍርድነ ይጠብቃቸዋል፡፡ በእርሱም የቀረበባቸው የፍርድ ቃላት ትርጉም አዘል ነበር ምክንያቱም ስለ ሞት መሠረታዊ ትርጉም ይሠጠናል፡፡
“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።” (ኦዘፍ 3፣ 19)
ያም አንድ ሠው ሲሞት የሕይወቱ ፍፃሜ ሲሆን አካላቱም ወደ ተስራበት ቅንጣት ተመልሶ የፈራርሳል፡፡
“ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል ያን ጊዜ ምክሩ ሁሉ ይጠፋል።” (መ.ዳዊ 146፣ 4)
ሞት ላለመታዘዛችን ቅጣት ነው፡፡ እግዚአብሄር ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ ፤ ከዚህ የሕይወት ዛፍ እንዳይበሉ ጠባቂን አስቀምጧል፡፡
“እግዚአብሔር አምላክም አለ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር” (ኦ.ዘፍ 3፣ 22)
ኃጥያት
ሞት የኃጥያት ቅጣት ነው፡፡ “እነሆም፥ በቈላው እንዳየሁት ራእይ የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበረ።” (ት.ሕዝ 18፣ 4)
በዚህ ውስጥ ቀላል ሃሣብ በዚህ አረፍተ ነገር እናገኛለን፡፡ ኃጥያት ሞትን አመጣች፡፡ ከዘላለማዊ ሞት የማምለጫ መንገድን ፈልጎ ለማግኝት ስለ ኃጥያት ማወቅ እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡
ኃጥያት የእግዚአብሄር ፍቃድ አለመቀበል ሲሆን (1ኛየሐ 3፣ 4 ፤ ያዕ 4፣ 17) የዚህም ተፅዕኖ አለማቀፋዊ ነው፡፡
“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤” (ሮሜ 3፣23)
“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፣23)
አዳምና ሔዋን እንዲሁም ለዘሮቻቸው ሁሉ ወደ ሞት ለሚወስዳቸው ምኞት ውስጥ አልፈዋል፡፡ ይህ የሠው ድክመት “የሠው ተፈጥሮ” ወይም የመፅሐፍ ቅዱስ እንደሚጠራው “የሥጋ ፍቃድ” ወይም “ሥጋዊ አዕምሮ”
ይህም ወደ ተለያዩ ውጤቶች ይመራናል፡፡ “የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” (ገላ 5፣ 19-21)
እነዚህም ተፈጥሮአዊ ሂደቶች ከዛሬ ከስድት ሺህ ዓመታት በፊት አዳምና ሔዋን የጀመሩት የሕይወት መንገድ ነው ፡፡ በእግዚአብሄር መንገድ አለመከተላችን ዛሬ አለማችን ላይ የምናየው ስቃይን ሊያመጣ ችሏል፡፡
ብቸኛው ተስፋ
በትምህርት ክፍል 2 ላይ የእግዚአብሄርን ባህሪያት አይተናል አሁን ደግሞ የሠውን የተወሰኑ ባህርያት ዘርዘር ባለ መልኩ አንመለከታለን ፡፡ እንደምንጠብቀው እና በእግዚአብሄር ነቅተን እንድንጠብቅ በዕነዚህ ቃላት በአንክሮ ነግሮናል፡፡
“አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር፦ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።” (ት.ኢሳ 55፣ 8-9)
ሠው ለምን ይሞታል ብቻ ሣይሆን ለምን መሞት እንዳለበት ግልፅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍሕታዊ እንደመሆኑ የትኛውም ኃጥያተኛ ዘላለማዊ ሕይወትን አይሠጣቸውም ሁለቱ ተጨማሪ የእግዚአብሄር ባህሪያት ምስጉን እና ይቅር ባይ ነው፡፡
“ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና።” (መ.ዳዊ 130፣4)
“በእርሱ ላይ ምንም እንኳ ያመፅን ብንሆን፥ በባሪያዎቹም በነቢያት እጅ በፊታችን ባኖረው በሕጉ እንሄድ ዘንድ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ምንም እንኳ ባንሰማ፥ ለጌታ ለአምላካችን ምሕረትና ይቅርታ ነው።” (ት.ዳን 9፣9)
“አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ መዓትህ የራቀ ምሕረትህም እውነትህም የበዛ” (መ.ዳዊ 86፣ 15)
የሠው ልጅ ኃጥያትን ከመስራት ስለማይቆጠብ የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡
“ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።” (1ኛየሐ 1፣8)
መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንገድ ከኃጥያት እና ሞት ነፃ መሆን የምንችልበት ብቸኛውን መንገድ ምን እንደሆነ ያብራራል፡፡ መንገዱም በዚህም ሐረግ ውስጥ “በማመን” (ገላ 2፣16) እግዚአብሔር ከእኛ እጅጉን የተለየ እምነትን የፈልጋል፡፡ ይህንንም ሲገልፅልን፡ “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።” (ዕብ 11፣1)
እምነት ማለት በጭፍን በተዘጋጀ ነገር ላይ ማመን ወይም ትርጉም በማይሰጥ መልኩ ሐይማኖት አድርጎ መቀበል ማለት አይደለም፡፡ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር መታመን እና እግዚአብሔር በእርግጥ ቃል የገባልንን እንደሚፈፅምልን ደግሞም፤ ተፈፃሚነቱ ሊከሰት ማይችል ቢመስልም ከልብ ማመን ማለት ነው፡፡ እምነታችንንም የምናሳየው ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት ተገዥ በመሆን ነው፡፡ በዕብራዊያን መልዕክት ምዕራፍ አስራ አንድ ላይ ብዙ የቀረቡ ተግባራዊ የእምነት ከሁሉ የበላይ ነው፡፡ “ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሄኖስንም ወለደ” (ኦ.ዘፍ 15፣6) እምነቱንም ያሳየው ለእግዚአብሔር ታዛዥነቱን በማሳየት ነው፡፡
ያዕ 2፣17-26፡ “እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።” (ያዕ 2፣17)
ይህም በእግዚአብሔር ምህረት ያመኑትና የታዘዙት ለኃጥያታቸው ይቅርታን ያገኛሉ፡፡ በሂደትም ዳግም ሞትን ድል ያደርጉታል፡፡ ይህም የሠው ልጅ ሞትን ድል የሚነሣበት ብቸኛው ተስፋ ነው፡፡ በእምነት ዘላለማዊ ሕይወት ስጦታ ነው፡፡
“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፣23)
በቀጣይ በሚኖረን ትምህርት እንደምንማረው ይህ ሊሆን የቻለው ኢየሱስ ክርስቶስ በከፈለው መስዋትነት ነው፡፡ ዘላለማዊ ሕይወት ወደፊት የሚሰጠን ሲሆን ይህም የሚሆነው በሙታን ትንሣኤ ወቅት ነው፡፡
“በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።” (ት.ዳን 12፣2)
በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ህዝቦች ይህን ውድ የሆነ ስጦታን ወደ ዘላለማዊነት መለወጥን ይሰጣቸዋል፡፡ የሙታን ትንሣኤ በራሱ የሚታመንበት አይደለም ነገር ግን ማመን ከሚኖርብን ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እንደምናውቀው ሁሉ ነገር ለእግዚአብሔር ይቻለዋል፡፡ ይህም ትንሣኤ ሙታን የሚከሰተው ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ወደ ምድር ሲመጣ ነው፡፡
“ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤” (1ኛተሰሎ 4፣ 16)
በትምህርት 9 የተወሰኑ ስለዚህ ወቅት መቃረብ ምልክቶችን የሚነግሩንን ምልክቶች የምንማር ይሆናል፡፡ ለዚህም ቀን የተዘጋጀን መሆን ይኖርብናል፡፡
ማጠቃለያ
-
ሞት የሕይወት ፍፃሜ እንጂ ዘላለማዊነትን የማግኛ ዋና በር አይደለም፡፡
-
የሞት መንስኤው ኃጥያት ነው፡፡
-
ኃጥያት ማለት የእግዚአብሔርን ፍቃድ አለመፈፀም ማለት ነው፡፡
-
ሁሉም ሰው ኃጥያተኛ ነው ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዕርዳታ ውጭ ኃጥያትን ከመስራት መቆጠብ አንችልም፡፡
-
ድነት የሚጀምረው በቅን ልብ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ነው፡፡
-
የእግዚአብሔርን ቃል በማመን እና ለፍቃዱም በመገዛት ምህረትን ማግኝት እንችላለን፡፡እምነት ማለት በእግዚአብሔር ቃል ማመን እና ለቃሉ መገዛታችንን ማሳየት ማለት ነው፡፡
-
ዘላለማዊ ሕይወት እግዚአብሔር በእርሱ ለሚያምኑ ልጆቹ የሚሠጠው ስጦታ ነው፡፡
-
ዘላለማዊ ሕይወት በእግዚአብሔር ለሚያምኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ዳግመኛ ሲመጣ በትንሣኤ ሙታን የሚሰጣቸው ሲሆን፤ይህም የሠው ልጅ የተሠጠው ብቸኛው የዘላለማዊ ሕይወት ተስፋ ነው፡፡
ለንባብ የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ኦ.ዘፍ 2 እና 3፣ መ.ዳዊ 49 እና 146 ፣ መ.መክ 9፣ ሮሜ 5 እና 6፣ 1ኛቆሮ 15
ትምህርት ክፍል 4፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
ከሚከተሉት ዐረፍተ ነገር ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ሁሉም ሠው ኃጥያተኛ ነው ሐ. መልካም ሠዎች አይሞቱም
ለ. ሞት የኃጥያት ውጤት ነው መ.ዘላለማዊ ሕይወት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው
-
በየትኛው ቁጥር ላይ ነው ሞት ሙሉ በሙሉ እራስን አለማወቅ እንደሆነ የተፃፈው?
ሀ. ት.ሕዝ 9፣5 ለ.መ.ምሳ 9፣5 ሐ. መ.አስ 9፣5 መ. መ.መክ 9፣5
-
ከአንድ ድነትን ከእግዚአብሔር ከሚመኝ ሠው ከእርሱ የሚጠበቅ የሠው ልጅባህሪ የትኛው ነው?
ሀ. እራስ ወዳድነት ለ. ጤና ሐ. መታዘዝ መ. ደስተኝነት
-
መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን እግዚአብሔር የሠውን ልጅ ከምን ፈጠረው?
ሀ. ከሌላ ፍጥረት ለ. ከምድር አፈር ሐ. ከውሃ መ. አልፈጠረውም
-
“ህያው ነፍስ” ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ህይወት ያለው ፍጥረት ሐ. የማይሞት አካል
ለ. ዐይን መ. የማይሞት የአካላችን ክፍል
-
ዘላለማዊ ሕይወትን እንዴት እናገኛለን?
ሀ. መልካም በመሆን
ለ. ሁሉም ሠዎች ህያዋን ሆነዋል
ሐ. ለኃጥያታችን ይቅርታን በመጠየቅ እና ለእግዚአብሔር በመታዘዝ
መ. ዘላለማዊ ሕይወትን ማግኝት አይቻለንም፤የሠው ልጅ ዘላለማዊ ሕይወት ስለሌለው ሞትም
ፍፃሜው ነው
-
በአዳምና በሔዋን አለመታዘዝ ምን ተፈረደባቸው?
ሀ.ተመተዋል ሐ. በድንጋይ ተወግረዋል
ለ. ሞት ተፈርዶባቸዋል መ. እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ አስወግዷቸዋል
-
ኃጥያት ምን ማለት ነው?
ሀ. ስጋዊ አስተሣሰብ ሐ. የእግዚአብሔር ህግ መተላለፍ
ለ. ሞት መ. የሠው ተፈጥሮ
-
እምነት ማለት………..
ሀ. የማይቻለንን ማምለክ ሐ. በማናቀው መታመን
ለ.የእግዚአብሔር ዕቅድ ማወቅ መ.በእርግጠኝነት ተስፈ በሚሰጡን ነገሮች
-
መፅሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን ………
ሀ. ምንም ተስፋ እንደሌለ ሐ. ሁሉም ከመቃብር በኋላ በሚኖረው ሕይወት
ለ. ትንሣኤ ሙታን መ. ፃድቃን በሠማያት የሚኖራቸው ሕይወት
ትምህርት ክፍል 5፡ የእግዚአብሔር ቃልኪዳን -1
በትምህርት ክፍል 4 ሠው ለምን እንደሚሞት ከመፅሐፍ ማባራራት ተችሏል፤ የሞት ተፈጥሮ እና በመቃብር ከዘላለም ሞት ለመዳን የሠዎች ብቸኛ ተስፋን ለማየት ሞክረናል፡፡ በትምህርት ክፍል 5 ስለ ድነታችን በቅዱሳን መፃህፍት እንዴት እንደ ተተነበየ የተወሰኑ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ላይ በመመስረት ሠፋ ያለ ግንዛቤን እናገኛለን(ተጨማሪ ቃል ኪዳን በትምህርት ክፍል 7 እንመለከታለን)
የቃል ኪዳን አሰጣጥ
በመጀመሪያም አዳምና ሔዋን ትዕዛዙን ካፈረሱ በኋላ በሰዎች ኃጥያት የተነሳ እግዚአብሔር እነደ ተናገረው ተረግመዋል፡፡ አጭር ነገር ግን የሚያስደንቅ የቃል ኪዳን ፍንጭ ተስጥቷቸዋል፡፡ በቀላሉ መረዳት እንድንችል ሆኖ በዚህ ቁጥር ላይ እናገኝዋለን፡፡
“እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።” (ኦ.ዘፍ 3፣14-15)
የዚህ ጥቅስ ሙሉ ትርጓሜ ከዚህ የትምሀርት ክፍል ወሰን በላይ ነው፤ እናም ይህም “የመጽሐፍ ቀዱስ ዕውነታ” ውስጥ ይካተታል ነገር ግን የእግዚአብሔርን የድነት ዕቅድ ሠፋ ያለ ግንዛቤ እናገኝበታለን፡፡ ይህም በግልፅ እንደሚያሳየን ይህ የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ሲሆን በሄዋን የዘር ግንድ በአንዱ ኃጥያትን ሙሉ በሙሉ ድል ይነሳል፡፡ ኃጥያትም ይሞታል፡፡ ነገር ግን ይህን የሚያደርገው የዘር ግንድ ለጊዜው ቆስሏል “በስዕላዊ አገላለፅ ስንገልፀው ራሱ በአሜኬላ ቆስሏል፣ እጅና እግሮቹ የተቸነከሩበት ቆስለዋል” ይህም ለሚመጣው አዳኝ የተገባለት ቃልኪዳን ሲሆን መፅሐፍ ቅዱስም ይህ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በማያከራክርና ያለ ጥርጥር እንድንቀበለው ያደርገናል፤ ሁሉም የእግዚአብሔር ቃልኪዳን የሚያመለክቱት ወደ እርሱ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በኤደን
አዳምን ሄዋን የእግዚአብሔር ተዕዛዝ እንዲተላለፉ ምክንያት የሆናቸው እባብ የኃጥያት ምልክት ሆኗቸዋል ኢየሱስም ለጠላቶቹ ተመሣሣይ ቃልን ተሠቅሟል፡፡ ፈሪሳውያኑን ለመግለጽ የተጠቀመበት ቃላት “ማቴ 23፣33” እራስን ይቀጠቅጣል ይህም እባቡን ለሞት የሚያደርስ ቅስለትን ያስከትልበታል፤ይህም ቃልኪዳን የኃጥትንና ፍፃሜና ውድመትን ያሳየናል፡፡ የሴቷም ዘር አፍራሽ እና ይህንንም ስራ በሚፈፀምበት ወቅት እግሩን ቢነድፍም ከቁስለቱ ግን በቶሎ ያገግማል፡፡
መጽሐፍን በትኩረት ብናነብ የሚያሳየን የሴቷን ዘር የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት፣ሞትና ትንሣኤ በምሳሌ ይነግረናል፣ እንዴት አድርጎ በኃጥያትና ሞት ላይ ድል እንደተቀዳጀ በአርሱ ለሚያምኑ ሁሉ የዘላለም ሕይወት ምንገድን ጠርጎልናል፡፡
ይህንንም የሴቷን ዘር ለመለየት የሚያስችሉን ሰጥተውናል፡፡ “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” (ት.ኢሳ 7፣ 14)
የዚህን ጥቅስ መልዕክት በድጋሚ ተወስዶ ለማርያም እጮኛ ለሆነው ዮሴፍ መልዐኩ እንዲህ ብሏታል፤ “ልጅን ትወልጂያለሽ እርሱም ህዝቡን ከኃጥያታቸው ያድናቸዋልና ስሙም ኢየሱስ ትለዋለህ” ይህ ሁሉ የሆነው በነብያት የተነገረው ፍፃሜ እንዲያገኝ ነው፡፡ ከትንቢተ ኢሳያስ 7 የወሰድነውን ጥቅስ በመቀጠልም፤ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሲያብራራ፡፡ “ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ። እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ብሎአልና፤” (ገላ 4፣ 4)
ኢየሱስ በኃጥያትና ሞት ላይ ስኬትን ተቀዳጅቷል፡፡እባቡ(ኃጥያት) እራሱን ተቀጥቅጧል፤ ያም እርሱ በይፋ ጠፍቷል(ክርስቶስን ስንመለከት) ይህን ለመጎናፀፍ በነረው ሂደት ውስጥ በመስቀል ላይ ለመሞትበመቃብር ለተወስኑ ቀናት በመቆየት ሰኮናውን ተቀጥቅጧል ነብዩ ኢሳያስ ቀድሞ እንደነገረን፡፡ “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” (ት.ኢሳ 53፣ 5)
የእግዚአብሔር ዕቅድ የመጀመሪያው ደረጃ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ የሠዎችን ኃጥያት ስርየት ማስገኝት ይህ የተፈፀመ ሲሆን ነገር ግን ሌላ ሁለት ተጨማሪ ደረጃዎችን ሰብልን ለመስብስብ ኃጥያት እና ሞት ሙሉ በሙሉ መጥፋት ይኖርብናል፡፡
ሁለተኛው ደረጃ የሚጠናቀቀው ክርስቶስ ለወዳጆቹ ሊሸልማቸው ሲመጣ ነው፡፡ ያዘዛቸውን ለፈፀሙ ሁሉ(የሐ 15፣ 14) እና የእግዚአብሔርን ጠላቶች ይቀጣል፡፡ እነዚህንም ከሞት የተነሱትን የዘላለም ሕይወትን ወይም ዘላለማዊ ሞትን ይስጣቸዋል፡፡ የዘላለም ሕይወትን የተስጣቸው ከክርስቶስ ጋር በመሆን በእርሱ የሚተዳደሩትን ህዝቦች እርሱ በመጣ ጊዜ አብረው ይመራሉ፡፡ (ራዕ.የሐ 20፣ 4) ይህም ደረጃ የሚጠናቀቀውም በሺህ ዓመታት ውስጥ ይሆናል፡፡
ሶስተኛውና የመጨረሻው ደረጃ የሚሆነው በሺህ ዓመታት ፍፃሜ ላይ የሆናል፤ በዚህም ጊዜ የመጨረሻው ፍርድ ይሆናል፡፡ እናም ኃጥያትና ሞት ሙሉ በሙሉ ይጠፋል፡፡”ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤” (1ኛቆሮ 15፣ 25-26)
አለማመን እን አለመታዘዝ ሞትን እንደሚያመጣ፤ስለዚህም በወንጌል ማመን፣ መጠመቅ፣ ዕለት ተዕለት መታዘዝ በእግዚአብሄር ቃል ኪዳን ዘላለማዊ ሕይወትን ይሰጣል፡፡
የእግዚአብሄር ዕቅድ መረዳት
-
ኖህ
የአዳምና ሔዋን ዘሮች እየበዙ ሲመጡ ኃጥያትም ጨምሯል እና ሠዋች ቀስ በቀስ የፈጠራቸውን እረስተዋል፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት እንደተፃፈው “ኦ.ዘፍ 6፣ 5” ይህም ጠሰው ልጆችን ሁኔታ ያሳየናል፡፡
“እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።” (ኦ.ዘፍ 6፣ 6)
ኖህ እግዚአብሄር የሚደሰትበበት ብቸኛው ሰው ነበር (ኦ.ዘፍ 6፣ 8-9 እንመልከት) እግዚአብሄር እንደ አዲስ ከፍጥረቱ ጋር ለመጀመር ቀቋሚ አላማን ወስኖና ኖህንም በዚህ ሊሳካ በተፈለገው ግብ ተጠቅሞበታል፡፡
“እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፦ የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።” (ኦ.ዘፍ 6፣ 13)
እግዚአብሄርም ምድርን በጥፋት ውሃ ሊያጠፋት መረጠ ሁሉም አየር በመተንፈስ የሚኖር ፍጡር ሰውን ጨምሮ በውሃው ተጥለቅልቀዋል፤ ከጥፋት ውሃ መጽሐፍ ቅዱስ ሊያስተምረን የፈለገው ታላቅ ሞራል(ማቴ 24፣ 37-38፣ 1ኛጴጥ 3፣ 20-21) የኖህ ሕይወት የሚያሳየን የእምነት ምሳሌነቱንና በሌላ በኩል ደግሞ በወቅቱ የነበሩ እምነት የሌላቸውን በማነፃፀር ነው፡፡
-
የእግዚአብሄር ቃልኪዳን
በዚህ ወቅት እግዚአብሄር እንደገለፀልን በጥፋት ውሃ ዳግመኛ ምድርን በፍፁም አያጠፋትም፡፡እግዚአብሄር በዚህች ምድር ላይ አላማ አለው እናም ቃል እንደገባውም ከዚያ ጊዜ በኋላ ወቅቶች በእራሳቸው ተራ መፈራረቃቸውን ቀጥለዋል፤ ቀንና ሌሊትመረ ያለ ምንም መዛነፍ በስርአታቸው መቀጠል ችለዋል፡ኦ.ዘፍ 8፣ 21-22 እንመልከት፡፡ “እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና አልመታም።በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።” (ኦ.ዘፍ 8፣ 21-22)
-
ጥቂቶች ድነዋል
ተጨማሪ ትምህርት ከዚህ ፅሁፍ እንደምንማረው እግዚአብሄርን ለማመን የተዘጋጁ ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ የተዘጋጁትና በዚህም ምክንያት ሊድኑ የሚችሉትም ጥቂቶች ይሆናሉ ይህ መርህ ስለ ጥፋት ውሃው በግልፅ ያሳየናል፡፡ (1ኛጴጥ 3፣ 20) ይህም ከዘላለማዊ ሞት ወደ ታላቅ ድነት ይውላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለው (ማቴ 7፣ 13-14)
ይህ እና ተመሳሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሎዎች እና አረፍተ ነገሮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማኞችንና ደጋፊዎችን ዕውነታውን አምነው የተቀበሉትን ሐይማኖት እንዲጠራጠሩ ያደርጋቸዋል፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ከዘላለማዊ ሞት ድነትን ማግኝት ግላዊ ጉዳይ ነው እና ይህም የእግዚአብሄር ፈታኝ የሆኑ ፍላጎቶችን ለሟሟላት ጥቂቶች ለመቀበል ተዘጋተዋል፡፡ ይህም ጥንካሬን የሚጠይቅ እና ጠባብ የእምነት ምገድ ነው፡፡
-
አብርሃም
በእግዚአብሄር ቃል ስለነበረው እምነት ብዙ አስቸጋሪ ፈተናዎችን በመቻል ሙሉ በሙሉ የተወጣ እና ለመቀበልም ቀደም ብሎ የተዘጋጀ ልዩ ምስክር ነው፡፡
-
አርኪሎጂስቶች መፅሐፍ ቅዱስን ወደ ሕይወት መልሰዋል
አብርሃም የኖረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ወደ 2000 ዓመታት ሲሆን በጥንታዊቷ ኡር ከተማ ነበር ይህቺም ከተማ የምትገኝው በፐርሺያ ባህር ዳርቻ አቅራቢያ ነው፡፡ በአሁን ወቅት ይህ ስፍራ በአርኪዮሎጂስቶች ቁፋሮ እየተካሔደበት ይገኛል፡፡ ግኝታቸውም እንደሚያሳየን ይህቺ ከተማ በከፍተኛ ደረጃ የስለጠኑ ሲሆን በወቅቱ ትላልቅ ቤቶችን፣ ቤተ መንግስት እና ቤተ መቅደስና እጅግ የረቀቁ የዕደ ጥበብ ስራዎችን መስራት የቻሉ ነበሩ፡፡ የአርኪዮሎጂስቶችም በመጥሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ የሚያግዙን ስለ ቀደምት ዘመናት ግልፅ የሆነ ምስል ይሰጡናል፡፡ የአብርሃምን በእምነት ታላቅነት እንድኛስተውል ያግዙናል፤ እግዚአብሄር አብርሃምን ሲያዘው “ኦ.ዘፍ 12፣1” ከአርኪዎሎጂስቶች ማስረጃዎች ተነስተን መረዳት ችንደምንችለው እግዚአብሄር አብርሃምን የቀደመ ቀለል ያለ ሕይወቱን በመተው ወደማያውቀውና ለደንነቱም አደገኛ ሊሆን ወደሚችለው ነገር ነገር ግን እግዚአብሄር ብቻ ሊመራው በሚችለው አግባብ ሲጠይቀዉ አብርሃም እንደ አዳማ እና ሔዋን ሳይሆን ለእርሱ መታመንና መገዛት ችሏል፡፡ “አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።” (ዕብ 11፣ 8)
-
ለአብርሃም የተገቡለት ቃልኪዳን
የአብርሃም እምነት የነበረው በተገባለት የበረከት ቃል ኪዳን ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ነበረበት እርሱም እንደተረዳው እግዚአብሄር የኃያላን ኃያልና ሁሉን በጥበቡ የፈጠረ የገባውን ቃል ኪዳን ሊፈፅማ በቃሉ የታመነ እንደሆነ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄርም ለእርሱ አለው፤ “ኦ.ዘፍ 12፣ 2-3”
በአብርሃምመ ዕድሜ ዘመን ሁሉ ይህ ቃል ኪዳን ተደጋግሞ ቢገባለትም በእያንዷንዷ ወቅትም በዋናው ቃል ኪዳን ላይ የተወስኑ ነገሮችም እየተጨመሩበት ነበር፡፡ ለአሁኑ ዋና ዋና የምንላቸውን ቃል ኪዳን በሚከተሉት ርዕስ እንመለከታቸዋለን፡፡
-
የአብርሃም ዘርች የካንአን ምድር ይወርሳል
-
የአብረሃም ዘሮች ታላቅ ህዝቦች ይሆናል
-
ከአብርሃም ዘሮች በአንዱ ምክንያት ሁሉም ህዝቦች ይባረካሉ
4.1 የአብርሃም ዘሮች የካንአንን ምድር ይወርሣሉ
በዚያን ወቅት እግዚአብሔር አብርሃምን ይመራው የነበረው ወደ ካንአን ወደምትባል ምድር ነበር፡፡ ይህም ስፍራ በተወሰነ መልኩ ወደ ምትቀራረበው የሜድትራንያን ባህር ምስራቃዊ ጫፍ የሚገኙ የአሁኑን ሊባኖስ፣ እስራኤል፣ ሲሪያ፣ እና ጆርዳን ናቸው፡፡ (ኦ.ዘፍ 13፣18-21) አብርሃም ካንአን ሲደርስ እግዚአብሔርም አለው፡፡ “እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።” (ኦ.ዘፍ 12፣7)
ይህም ቃልኪዳን ቆይታ ተደግሟል፡ “የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና።” (ኦ.ዘፍ 13፣15) በተለየ መልኩ እነዚህን የተጨመሩ ቃላትን እናስተውል “ላንተ” እና “ለዘላለሙ” በመጽህፈ እያሱ ላይ እንደተፃፈው እነዚህን ሁለት ነጥቦች ባያስፈልጉ ኖሮ ይህን ቃልኪዳን የሚያሳየን በቀደምት ዘመን የካንአንን በእስራኤላውያን መወረር እና በቁጥጥር ስር መዋል ነው ብለን በተረዳን ነበር፡፡ ቢሆንም ይህ ከዚያ መፈፀሙን ብቻ የሚያሳይ ነበር፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ ቃልኪዳኑ የተገባው ለአብርሃም እንዲሁም ለዘሮቹ ነበር፤ በሁለተኛ ደረጃም ይህም ለዘላለሙ በእርሱ ስር ይሆናል፡፡
በመጀመሪያው ነጥብ መፅሐፍ ቅዱስ አንደሚያሳየን በካንአን በሚኖርበት ወቅት፤ አብርሃም ልክ እንደ ዘመኑ ሠዎእ ነበር፤ እናም ሚሲቱም ስትሞትበት ለሚስቱ መቀበሪያ የምትሆን የተወሰነች መሬተረ መግዛት ነበረበት፤ በመጨረሻም ትወርሳለህ የተባለውን የተስፋይቷን ምድር ሣይወርስ ሞተ(የሐ.ሥራ 7፣ 2-5)በሁለተኛውም ነጥብ በግልፅ እንደተቀመጠው አብርሃምም ሆነ ዘሮቹ አንዲሁም ህዝበ እስራኤል ከካንአን ምድር ከወጡ ረጅም ጊዜን አሣልፏል፤ ለዘላለምም እስካሁን አልወረሳትም፡፡
-
ትንሣኤ ሙታን መልሱን ይሰጠናል
በግልፅ እንደተቀመጠው የዚህ የቃል ኪዳን ፍፃሜን ወደፊት ይሆናል፡፡ ይህ ቃልኪዳን ፍፃሜን ወደፊት ይሆናል፡፡ ሆኖም ይህ ቃልኪዳን ሊፈፀም አብርሃም እና እውነተኛ ዘሮቹ ከሞት መነሣታቸውን ይጠይቃል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልፅለን እነዚህም በእምነታቸው ና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በመጠበቅ አብርሃምን ይመስሉታል፡፡(ሮሜ 9፣ 8) ከትንሣኤ በኋላ ህያዋን ሆነው ካንአንን ለዘላለም ይወርሳሉ (ገላ 3፣7 ና 29 ፤ ዕብ 11፣39-40)ሌሎችን ቃልኪዳን ስንመለከት እነዚህ ነጥቦች ግልፅ እየሆኑልን ይሄዳሉ፡፡
-
የአብርሃም ዘሮች ታላቅ ህዝብ ይሆናሉ
ይህ ቃልኪዳን በአብርሃም ሕይወት ውስጥ ብዙ ጊዜ ተስጥቶታል (ኦ.ዘፍ 12፣2 ፤ ኦ.ዘፍ 13፣16፤ ኦ.ዘፍ 15፣5፤ ኦ.ዘፍ 22፣17)እና መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያሳየን አብዛኞቹም እየተፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ (1ኛነገ 3፣ 28)
የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ እንደተጠቀሰው የአብርሃም ልጅ ይሣቅ እና የልጅ ልጁ የሆነው ያዕቆብ (ስሙም ወደ እስራኤል የተቀየረው) የነገደ እስራኤል መነሻ ናቸው፡፡ እርሱምያዕቆብ በከፍተኛ ርሃብ እና ድርቅ ወቅት ቤተሰቡን ይዞ ወደ ግብጽ እስከሄደበት ጊዜ ድረስ በካንአን ይኖሩ ነበር፡፡ በኦሪት ዘፅአት መፅሐፍ እንደሚነግረን እንዴት የያዕቆብ ዘሮች በዝተው ከሁለት ሚሊዮን ህዝብ በላይ በመሆን ከዛም በግብፅ በባርነት ቀንበር መውደቃቸውን ያሳየናል፡፡ በ1500 ከክርስቶስ ልደት በፊት እግዚአብሔር ሙሴን በመላክ ነፃ አውጥቷቸውና እነርሱን በመምራት ወደካንአን መልሷቸዋል፡፡ በመጽሐፈ እያሱ የሙሴ ተከታይ እንዴት አስራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች ካናንን እንደወረሱ ይነግረናል፡፡ ቀጥሎም የምናገኛቸው መፃህፍት የእስራኤል እድገት ታላቅ ና ባለፀጋ መንግስትን በንጉስ ዳዊት እና ሠለሞን 1000ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት እስክትሆን ያለውን ዕድገት ይገልፅልናል፡፡
-
አዲስ ኪዳንም ስለ ቃልኪዳኑ ያብራራልናል
መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚያሳየን ከሠለሞን ሞት በኋላ እስራኤል እየወደቀች ና ከካንአን ቀስ በቀስ ተገንጥላለች ምክንያቱም ጠቅለል አድርገን ለመንገር የህል ህዝቦቿ እምነት የለሽ እና ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ነበሩ (ኦ.ዘዳ 28፣ 15-68) በአዲስ ኪዳን ለአብርሃም የተገባለትን ልዩ የሆነ ቃልኪዳን እናገኛለን፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሠዎች በላከው ደብዳቤ ግልፅ እንዳደረገው ፡ “ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥ነገር ግን። በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ።” (ሮሜ 9፣6-7)
ይህም የሚያስተዋውቀን አስፈላጊ የሆነውን በመጀመሪያው ቃል ኪዳን ላይ የሠጠው መርህ በማብራራት ነው፡፡ ይህም የሚያስረግጥልን ታላቅ ህዝብ የተባሉት የአብርሃም ዘሮች ሲባል የሚያምኑት የተፈጥሮ የዘር ግንድ ያላቸው ብቻ ሣይሆን ነገር ግን እንደ አንርሃም ያለ እምነት ያሣዩ መሆን አለባቸው፡፡ በእያንዳነዱ ትውልድ ጥቂቶች ሲኖሩ ነገር ግን ኢየሱስ ዳግመኛ ወደ ምድር ሲመጣ በትንሣኤ ሙታን ወቅት ከሞት ያስነሣቸዋል፤ በአንድም ስፍራ ተሰባስበው አነድ ታላቅ ህዝብ ይሆናሉ፡፡ ቀጥሎም አብርሃም ህያው ከሆኑ ዘሮቹን በዚያን ጊዜ ያያቸዋል፡፡ ስለ ድነታችን እግዚአብሔርን ያመልካሉ እናም ይህን ይመስሉታል፡፡ “ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤” (ራዕ 7፣9)
ይህም ወደፊት የሚፈጸም ቃልኪዳን ሲሆን ከበፊቱም እጅግ በተሸለ መንገድ የሚሆን ይሆናል፡፡
-
ከአብርሃም ዘሮች በአንዱ ሠዎች ሁሉ ይባረካሉ
ቢሆንም ይህ ታላቅ የበረከት ቃልኪዳን የሚመለከታቸው ሠዎች ሁሉ በአሁኑ ወቅት አልተቀበሉም - የምድር የኃጥያት ና ሞት መርገምትን ነፃ አልወጡም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልፅልን ይህ ጊዜ የሚመጣበት ወቅት ይመጣል፡፡ “ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።” (ኦ.ዘኁ 14፣21)
ለእግዚአብሔር ክብር የተወሰነ ቦታ ይኖረናል፤ የሠው ልጅ አለምን በብጥብጥ እና ጥንቀት ሞልቷታል እና ኃጥያት እና ሞት አሁንም አለ፡፡ በአብዛኛው መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት (ለምሳሌ፡ መ.ዳዊ 72 ና ት.ኢሳ 32) እንደምናነበውም ልዩ የሆነው የመባረክ ዘመን ሲመጣ ነገሮች ሁሉ እንደሚለወጡ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ለውጥ ቢያስፈልግም፤ የሚጠበቀው ውጤት እንደሚሆን እርግጥ ነው! ይህም የወንጌል(የምስራች ዜና) መልዕክት ነው፡፡ ይህም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተምረናል፡፡ ይህም እንደምናስተውለው ለአብርሃም ቃልኪዳን የተገባለት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ2000 ዓመታት በፊት ነበር፤ ይህም የወንጌል መሠረት ነው!
“መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ። በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።” (ገላ 3፣ 8)
-
ኢየሱስ ክርስቶስ - የአብርሃም ዘር
የወንጌል ማዕከላዊ ምስል እናም ለአብርሃምየተገባለት ቃልኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ አዲስኪዳን በእነዚህ ቃላት የጀምራል “ማቴ 1፣1” እና የኢየሱስ የዘር ሐረግ ወደ ኋላ ስናይ ኢየሱስ ከአብርሃም ግንድ ነው፡፡ ይህንንም የምናገኝው በአዲስ ኪዳን ውስጥ ነው፡፡ ጳውሎስ ለገላትያን ሠዎች በፃፈው ደብዳቤ እንዳሣወቀን አንድ ለየት ያለ ዘር ሀረግ በእያንዳንዱ ቃልኪዳን ላይ ተጠረቷል እና ይህም አንዱ ኢየሱስ ነው፡፡ “ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር። ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን። ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።” (ገላ 3፣16)
ኢየሱስ እንደተገለፀው ከተፈጥሮአዊ የአብርሃም ልጅ በላይ ነው፤ በተመሣሣይ ደብዳቤ እንደተገለጸው፡ “እንኪያስ ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ እወቁ።” (ገላ 3፣7)
ስለ መፅሐፍ ቅዱስ ስለ ማመን ስናስብ እግዚአብሔር ስለማመን እና ለእረሱም ስለመገዛትን ያካትታል (ከኃጥያት በእጅጉ የተቃረነ) በግልፅ እንደተቀመጠው ኢየሱስ ከአብርሃም ብዙ ልጆች ውስጥ የሁሉም የበላይ ነው፡፡ እርሱ ብቻ ከሁሉም የሰው ዘር ያለ ምንም ፍርሃት በፈተናዎች ሁሉ በእውነት ያለ ስህተት ማለፍ የቻለ ነበር፡፡ ”ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለ ምን አታምኑኝም?” (የሐ 8፣ 46) የአዲስ ኪዳን ዋናው መልዕክት ኢየሱስ በእምነቱ ኃጥያትን ማሸነፍ ችሏል እና ይህም፡ “አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።” (2ኛጢሞ 1፣ 10)
-
የወንጌል ስለ ሁሉም ህዝቦች ይሰብከናል
ቢሆንም ይህ ውድ ጊዜ እየመጣ ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ተመልሶ ስመጣ የሚገባቸውን ሁሉ ከሞት ያስነሣቸዋል፤ እነዚህም ጨምሮ “በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።” (ገላ 3፣ 26-29)
-
የእግዚአብሔር መንግስት በምድር ላይ
ስለዚህማ አብርሃም የተገባለትን ቃልኪዳን ወራሽ ሆኗል፡፡በዚያን ወቅትም የአብርሃም በረከት በሁሉም ህዝቦች ላይ በእውነት ይሆናል፡፡ ይህም የሚሆነው በዘር ሐረጉ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡(ገላ 3፣ 14) ኢየሱስ በአለም ላይ እና በሚመሠረተው በእግዚአብሔር መንግስት ላይም ይነግሣል፡፡ ይህችም ምድር አይታ በማታውቀው በረከት በዚያን ወቅት ትሞላለች፡፡ ይህም ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሲያስተምራቸው ሊፀልዩለትም የሚገባ ነው፡፡ “እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥” (ማቴ 6፣10)
ማጠቃለያ
-
ስለ ኃጥያት ና ሞት ማብቅያ ቃልኪዳን የተገባው አዳምና ሔዋን ኃጥያትን እንደፈፀሙ ነበር፡፡
-
የእግዚአብሔር የድነት ዕቅድ እንደሚገልፅልን ለሚያምኑ ቃል ኪዳንን ገብቶላቸዋል፡፡
-
የጥፋት ውሃ የሚያሣየን የሚድኑት ጥቂቶች መሆናቸውን ነው፡፡
-
እግዚአብሔር ከአብርሃም እምነት የተነሣ ታላላቅ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡
-
አንዳቸውም ቃልኪዳን ሙሉ በሙሉ ካልተፈፀሙም ቃልኪዳኑ ፍሬ ሃሣብ የሚጠቁሙት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን እርሱም ኃጥያትን እና ሞትን ድል አድርጓል፡፡
-
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ ሕይወትን እንደ አብርሃም በእግዚአብሔር ለሚያምኑ ና ለሚታዘዙ ይሰጣቸዋል፡፡
-
ቃልኪዳኑ ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ የሚሆኑት ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ሊመሰርት ሲመጣ ይሆናል፡፡
-
የእግዚአብሔር መንግስት የበረከትን ወቅት ወደ ምድር የሚያመጣ ይህም በእግዚአብሔር ክብር የተሞላ ይሆናል፡፡
ለንባብ የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ኦ.ዘፍ 6፤12፤15፤22 ፣ ኦ.ዘዳ 28 መ.ዳዊ 72 ት.ኢሳ 32 ፣ የሐ.ሥራ 7 ፣መ.ዳዊ 4 ፣ ዕብ 11
ትምህርት ክፍል 5፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
በኦ.ዘፍ 6፣9 ላይ እንደተፃፈው እግዚአብሔር እጅጉን የተደስተበት ሠው ስም ማን ነበር?
ሀ.አዳም ለ. ኖህ ሐ. ሔኖክ መ. አቤል
-
በኦ.ዘፍ 6-8 በተፃፈው መሠረት እግዚአብሔር እንዴት ኃጥያተኞእን እና ክፉዎችን ያጠፋቸዋል?
ሀ. በመሬት መንቀጥቀጥ ሐ. በጥፋት ውሃ
ለ.በርሃብና ድርቅ መ.በበሽታ
-
እንዴት አድርገው ነበር የሚያምኑ ሠዎች ከአደገኛው ወቅት ኦ.ዘፍ 6-7 የታደጋቸው?
ሀ. በጀልባይቷ ውስጥ በመሆን ሐ. በከፍታማ ተራራ ላይ በመኖር
ለ. እግዚአብሔር ደብቋቸው መ. እግዚአብሔር ለይቶ በመውሰድ
-
አብርሃም እግዚአብሔር ሣያናግረው በፊት የት ይኖር ነበር?
ሀ. ከንአን ለ. ቤቴል ሐ. ሰዶም መ. ኡር
-
ወደ የትኛው ምድር ነበር እግዚአብሔር አብርሃምን የመራው?
ሀ. ግብፅ ለ. ካንአን ሐ. ኤዶም መ. ሣሌም
-
የወንጌል መልዕክት ስለ አብርሃም ያስተምረናልን?
ሀ. አዎ ለ. አያስተምርም ሐ. ሊሆን ይችላል መ. አናውቅም
-
አብርሃም መቼ ነው እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ሙሉ በሙሉ የሚፈፅመው?
ሀ. ተቀብሏል
ለ. አናውቅም
ሐ. ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ለመመስረት ይመጣል
መ. አብርሃም ሞቷል ስለዚህም ቃልኪዳኑን አይፈፀምም
-
ከአብርሃም ዘሮች ሁሉ ታላቁ እና ኃያሉ ማን ነው?
ሀ. ይሁዳ ለ. ያዕቆብ ሐ. ዮሴፍ መ. ኢየሱስ
-
በአሁኑ ወቅት እውነተኛ የአብርሃም ዘሮች እነማን ናቸው?
ሀ. አረቦች ለ. ሁሉም ሠው ሐ. እምነት ያላቸው መ. የሞቱት ሁሉ
-
እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው ቃልኪዳን የትኛው ነው?
ሀ. እሱና ዘሮቹ የካንአን ምድር ይወርሳሉ
ለ. በሠማይ ለዘላለም ይኖራል
ሐ. ወዲያውኑ ታላቅ ባለፀጋ ይሆናል
መ. ሁሉም ዘሮቹ በእግዚአብሔር ታማኝ ይሆናሉ
ትምህርት ክፍል 6፡ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ
ይህ ትምህርት ክፍል የሚያጠነጥነው በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ነው - የአግዚአብሔር ማዕከላዊ ዓላማ፡
“ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። (ማቴ 1፣21) “ክርስቶስ” የሚለው ቃል የሚወክለው ርዕስንሲሆን ትርጓምውም “የተሾመ” ያም በልዩነት የተመረጠ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲባል የሐንስ መጥምቁ ተብሏል፡፡
የአግዚአብሔር የመጀመሪያ ዓላማ
በመጨረሻው የትምህርት ክፍል ለማሳየት እንደተሞከረው አግዚአብሔር በመጀመሪያ በኤደን አዳኝን አንደሚሠጣቸው ቃልኪዳን ገብቷል፡፡ ይህም አንዱ የሆነው የኃጥያትን ስልጣን ድል መንሳት የቻለ ነው፡፡ትምህርቱ እንደሚያሳየን እንዲህ ያለ በረከትን በሠው ዘር ላይ ላይመጣ የሚችለው በአብርሃም የዘር ሐረግ ላይ ነው፡፡ ማርያም እንዳስተዋለችው ልጇ ብቸኛው ቃል የተገባለት እና በምስጋና መዝሙር ስትዘምርም፡
“ማርያምም እንዲህ አለች።ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤…ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።” (ሉቃ 1፣ 46-47 ፤ 54-55)
የተለያዩ ነብያትም ስለሚመጣው አዳኝ ተናግረውለታል፡፡ ለምሳሌ ነብዩ ዳንኤል ስለ መሲው የመምጫ ጊዜን መቼ ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል፡፡ ነብዩ ሚኪያስ ስለ ትውልድ ቦታው ፅፏል፡፡ በወንጌላዊው ማቴዎስ ስለ ጠቢቡ ሠው ሄሮድስ ጉብኝት ተፅፏል፡፡ ማስታወሻ መያዝ ያለብን ምን ያህል ጊዜ በዚህ ንባብ ላይ ማቴዎስ ክስተቶች ሁሉ የተከሰቱት በብሉይ ኪዳን የተተነበየውን በሟሟላት ነው፡፡(ለምሳሌ ማቴ 1፣22 ፤ 2፣5 ፤ እና 15፤ 17 ፤23 )
ከመጀመሪያው ኢየሱስን መላክ የእግዚአብሔር ዓላማ ወደ ስራ ተፅዕኖ አይተናል፡፡ የሐንስ ሲፅፍ ፡ “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” (የሐ 1 ፣ 14)
ኢየሱስ ለምን ነበር የመጣው?
በሚገባ የተለመደ ቀደም ሲልም በዚህ ጥምህርት ክፍል የጠቀስነው ቁጥርን ብንመለከት የሚነግረን “የሐ 3፣16” ትርጉም ባለው መልኩ ገብረኤል ለማርያም ልግ ሊኖራት እንደሆነ ሊነግራት ተገልፆላት ነበር፡፡ ማርያምም ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብላ ጠይቃውም ነበር፤ ወንድ አታውቅምና፡፡ መልዐኩም እንዲህ መልሶላታል፡ “መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” (ሉቃ 1፣35) ይህም የትንቢቱ አንድ አካል ነበር፤ ማቴዎስ ላይ እንደሰፈረው (ማቴ 1፣22-23 ፤ ት.ኢሳ 7፣14)
መስዋዕትነት
እንደምታውቁት በብሉይ ኪዳን ወቅት እንስሳት ይሠው ነበር ይህም ለኃጥያት መዘዝ ተከታታይነት ባለው መልኩ ለማሰብ እና አንደ ይቅርታ ማግኛ መንገድም ነበር፡፡ ይህን የሠዋውም ሠው የሚያስተውለው ሞት የኃጥያት ውጤት መሆኑን ነው፤ እናም አንዳንዴ ከሚስዋው እንስሳ ጋር በማነፃፀር የዚህን መርህ ምልክት ያስተውላሉ፡፡(ኦ.ዘሌ 1፣ 3-4) ጳውሎስ እንደፃፈው፡ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፣23)
በዕብራውያን መልዕክት ላይ ሶስት ስለ ተፈፀሙ መስዋዕትነት ግልፅ ነጥቦችን አስቀምጧል፡፡
-
በብሉይ ኪዳን ወቅት የነበረው መስዋዕትነት የሚሰጠው ኃጥያት ሞትን እንዳመጣ የምናስተውልበት ነው - ይህም መርህ የተመሠረተው በመጀመሪያ ነው፡፡(ዕብ 10፣3)
-
እንስሳቶቹ ምንም አይነትስህተት ባይሠሩም እነርሱ የሚወክሉት ይህን ትምህርት ነው፡፡ “ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።”(ዕብ 10፣1)
-
የእንስሳት መስዋዕትነት ኃጥያትን ማስወገድ አልቻለም፡፡ “የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና።” (ዕብ 10፣4)
መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ እንደሚብራራው ኢየሱስ የእንስሳቱ መስዋዕትነት ሊያስገኝ የማይችለውን ለማስገኝት ሕይወቱን እንደ ፍፁም መስዋዕት ሰጥቶናል፡ “በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።” (ዕብ 10፣12)
አዲስ ጅማሬ
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያሳየን በአዳም ኃጥያት እና ባለመታዘዙ ምክንያት ሞት ወደ ዓለማችን መጣ ስለዚህም ኢየሱስ በእራሱ ሕይወት ፡”አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።” (2ኛጢሞ1፣10)
ምክንያቱም ኢየሱስ ከኃጥያት የፀዳ ሕይወትን ኖሯል፤ በሞተ ወቅትም ይህ “አልተቻለውም” ስለዚህም እሱ ሞቶ አልቀረም(የሐ.ሥራ 2፣24) ስለዚህም አግዚአብሔር ከሞት አስነስቶታል፡፡
ስለ አዳም አለመታዘዝ እና ስለ ኢየሱስ መታዘዝ በንፅፅር ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፡
“ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤” (ሮሜ 5፣ 12)
“በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።” (ሮሜ 5፣19)
“በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።” (ሮሜ 5፣ 21)
ልክ የአዳምን አካሄድ ለመከተል እንደመረጥን ሁሉ ስለዚህም በኢየሱስ የተቀመጠውን አካሔድ መምረጥ አንችላለን፡፡ “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።” (1ኛቆሮ 15፣22)
እምነት አስፈላጊ ነው
በትምህርተ ክፍል 4 እንደተብራራው ሠዉ ሟች ነውና ይሞታል፡፡ ሠው አግዚአብሔር ለስጠው እምነት ሊኖረው ይገባል፡፡
“አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።”(ዕብ 11፣ 4)
እንደተገለፀውም ይህ ሊን የኣለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ብቻ ነው፡፡ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”(ሮሜ 6፣23)
ስለዚህም በአግዚአብሔር የተሠጠውን ድነትበ ቅድመ ሁኔታ ሲሆን አግዚአብሔር እምነትና እርሱን ለሚፈልጉ ይሸልማቸዋል፡፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”(የሐ 3፣16) ለዚህም ነው የአግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ (“አግዚአብሔር አዳኝ ነው”) የተባለው “እርሱም ህዝቡን ከኃጥያታቸው ያድናቸዋል፡፡”
የኢየሱስ ሥራ በአሁኑ ወቅት
ከትንሣኤው በኋላ ኢየሱስ ወደ ሠማይ አርጓል፡፡ በዕርገቱም ወቅት ሁለት መላዕክት ዳግመኛ እንደሚመጣ ገልፀውልናል፡፡
“ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” (የሐ.ሥራ 1፣11)
ጴጥሮስም እንደተናገረው ኢየሱስ በሠማያት የሚቆየው እስከ “እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።” (የሐ.ሥራ 3፣ 19-21)
ኢየሱስ ዳግመኛ የአግዚአብሔርን የተቀሩትን ዓላማዎችን ለሟሟላት ይመጣል፡፡ በዚህም ወቅት በአግዚአብሔር እና በሠው መካከል የማማለድን ስራ ይሠራል፡፡ እርሱም የካህናት አለቃ በእኛ እና በአምላካችን መካከል በመሆን ያስታርቀናል፡፡
“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” (1ኛጢሞ 2፣5)
“ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤” (ዕብ 8፣1)
“ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” (ዕብ 7፣ 25)
ለዕብራውያን መልዕክት እንደሚያብራራው እየሱስ ሕይወቱን በምድር ላይ ኖሯል እና እርሱ “ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።” (ዕብ 2፣ 17) እርሱም እንዴት እንደሚሰማን መረዳት ይቻላል እና ስለሚያስፈልገን ነገር ጠንቅቆ ያውቃል፡፡”ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።” (ዕብ 4፣ 15-16)
ማጠቃለያ
-
ኢየሱስ የተወለደው መንፈስ ቅዱስ በድንግል ማርያም ላይ ፀልሎባት ነው ስለዚህም የአግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
-
“ኢየሱስ” ማለት “ደዳኝ” ማለትም ሲሆን ና ከመጀመሪያው የአግዚአብሔር አላማ የነበረው ሠውን ከተፈጥሮአዊ የኃጥያት መዘዝ ነፃ ለማውጣት ነው፡፡
-
የኃጥያት ደሞዝ ሞት ነው፡፡ የእንስሳት መስዋዕትነት የሚሠጠን በቋሚነት ይህን መርህ እንድናስታውስ ነገር ግን “ኃጥያታችንን ማስወገድ” በፍፁም አይቻልም፡፡
-
ኢየሱስ ትክክለኛውን መስዋዕት ሆኗል፡፡
-
ኢየሱስ አሁን በሠማይ የሚመሰገን የካህናት አለቃ ሆኗል ምክንያቱም ከእራሱ ልምድ መረዳት ይቻላል፡፡
-
አግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ዳግመኛ ወደ ምድር ንጉስ ሊሆን ይመጣል እናም ዓላማውን ለመፈፀም ምድርን በክብሩ ይሞላታል፡፡
ለንባብ የቀረቡ ጥቅሶች
ማቴ 1፣18 ፤ 2፣23 ፤ ሉቃ 1፣26-38 ፤ 2፣1-21 ፤ ሮሜ 5 ፤ ዕብ 4፣14-16 ፤ 8፣6
Carelinks Publishing
PO Box 152
Menai NSW 2234
AUSTRALIA
www.carelinks.net
email: info@carelinks.net
ትምህርት ክፍል 6፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
“ኢየሱሰ ክርስቶስ” የሚለው ስም ትርጉም?
ሀ. አዳኝ ለ. አደኝ ና የተመረጠ ሐ. የተመረጠ መ. የተመረጠ ና አዳኝ
-
የኢየሱስ እናት ማን ትባላለች?
ሀ. ኤላዛቤጥ ለ. ማርያም ሐ. ማርታ መ. ሩት
-
የኢየሱስ ትክክለኛ አባት ማን ይባላል?
ሀ. ዮሴፍ ለ. ዳዊት ሐ. አብርሃም መ.አግዚአብሔር
-
በትንቢተ ሚኪያስ 5፣ 2 የኢየሱስ ትውልድ ቦታ የት ነው ተብል ነበር?
ሀ. ናዝሬት ለ.ገሊላ ሐ. እየሩሳልም መ. ቤተልሔም ኤፍራታ
-
የእንስሳት መስዋዕት በብሉይ ኪዳን ወቅት…..
ሀ. ኃጥያት ሞትን እነዳመጣ የሚስቡበት ሐ. በሰፊው ስለተለመደ
ለ. የተቆጣን እግዚአብሔር ለማድረግ መ. ድነትን ለማግኝት
-
ኢየስስ ከ 2000ሺህ ዓመታት በፊት ለምን ተላከ
ሀ. አይሁዳውንን ለማዳን
ለ. ድሆችን ለመመገብ
ሐ. ትክክለኛውን የኃጥያት ስርየትን ሊያሰጠን
መ. የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ሊመሰርት
-
አሁን ኢየሱስ የት ነው ያለው?
ሀ. በመቃብር ለ. በሠማይ ሐ.በዚህች ምድር መ. አናውቅም
-
ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣልን?
ሀ. አዎ ለ. አይ ሐ. አናውቅም መ. ሊመጣ ይችል ይሆናል
-
ኢየሱስ በአሁኑ ወቅት ምን እየሰራ ነው?
ሀ. ሕይወታችንን እየተቆጣጠረ
ለ. እንደ ሊቀ ካህናት በእግዚአብሄር ፊት እያገለገለ
ሐ. መንግስታትን እየተቆጣጠረ
መ. አናውቅም
-
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የእግዚአብሄር ሥጦታ ምንድነው?
ሀ. ብልፅግና ሐ. አሁን ረጅም ዕድሜ
ለ. ወደፊት ዘላለማው ሕይወት መ.ሠላምና መረጋጋት በአሁኑ ወቅት
ትምህርት ክፍል 7፡ የእግዚአብሔር ቃለኪዳን -2
እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባለት ቃል ኪዳን ሁሉም በምድር ላይ ያሉ ቤተሰቦቹ በሙሉ በእርሱና በልጁ (ዘር) ይባረካሉ፡፡ በትምህርት ክፍል 5 አንዱ በረከትን ወደ ምድር ሊያመጣልን የሚችለው ኢየሱስ እንደነበር አይተናል፡፡ ይህ በግልፅ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተምረናል፡፡(ገላ 3፣16)
አብረሃም የእምነት ምሳሌ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ እናም እንደተነገረን እምነታችንን ማሳየት ከፈለግን ሕይወታችንን መኖር የሚገባን ልክ አብርሃማ የኖረውን ያደረገውን ማድረግ ይኖርብንል፡፡ለእግዚአብሔር መታመንና ለፍቃዱም መገዛት ይኖርብናል፡፡
እስራኤል ህዝቦች በአብርሃም የዘር ግንድ ያሉ በግብፅ የባርነተን ቀንበር ተሸክመዋል፡፡ በሙሴ እየተመሩ ግብፅን ለቀው ሲወጡ አስቸጋሪ ሰቆቃና እንግልትን አሳልፈዋል፡፡ ግብፃውያን በሠማይ ሆኖ የምድርን ጉዳዮች የሚቆጣጠር እግዚአብሔር
መኖሩነ እንዲያምኑ እስገድዷቸዋል፡፡ የኦሪት ዘፀአት መፅሐፍ (የስሙም ትርጉሞ መውጣት ማለት ነው) ስለዚህ ክስትት ይነግረናል፡፡
በመጨረሻም ህዝበ እስራኤል አብርሃም ይኖርበት ወደነበረው የከንአን ምድር ተሰባስበዋል፡፡ ሳኦልም የመጀመሪያው ንጉሣቸው ሲሆን ብዙውን መዝሙር የፃፈው ደግሞ ሁለተኛው ንጉሳቸው ነበር፡፡
ለዳዊት የተገባለት ቃልኪዳን
ዳዊት በመዝሙሩ እንደነገረን እግዚአብሔር የተለየ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡ “እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ። ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።“ (መ.ዳዊ 132፣ 11)
ዳዊት መንግስቱን ሲመስርትና ህዝቡን በሠላም እያሉ የእግዚአብሔር ን ቤተመቅደስ ለመስራት ፈለጉ፤ ይህም ለእግዚአብሔር የአምልኮ ቤት ነው፡፡ ነብዩ ናታን ወደ ዳዊት ተልኮ እግዚአብሔር እርሱ ቤተመቅደሱን አንዲሠራለት አለመፈለጉን ነግሮታል፡፡እግዚአብሔር የዳዊትን የንግስና ቤት መስርቶለታል እና አንድ በእርሱ ንግስና መስመር ውስጥ ያለ በዚህ መንግስት ላይ ይነግሣል፡፡
“ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥ መንግሥቱንም አጸናለሁ።እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ። …… ቤትህና መንግሥትህም በፊቴ ለዘላለም ይጠነክራል፥ ዙፋንህም ለዘላለም ይጸናል።” (2ኛ ሣሙ 7፣ 12-13 ፤ 16)
በዚህ ጥቅስ ሶስት ዋና ዋና ነጥቦእን እናገኛለን
-
የዚህ ቃልኪዳን የመጨረሻው ፍፃሜ የደዊት ልጅ ሠለሞን ለማመላከት አይደለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዳለው “የመንግስቱን ዙፋን” ለዘላለሙ ይኖራል፡፡ ከሠለሞንም መረዳት እንደምንችለው ባለጸጋና ጠቢብ በመሆኑ የተወሰኑት ቃልኪዳን በእርሱ ተፈፅመዋል (ለምሳሌ፡- ለስሜ ቤትን ይሠራልኛል) አሁን በእርግጥ ለዘላለሙ አልነገስም፡፡ በቁጥር 14 ላይ ናታን ለዳዊት ሲነግረው እግዚአብሔር ለዚህ ታላቅ ንጉስ አባት የሚሆነው ሲሆን በእርሱም የዘር ሐረግ ስር “እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ ሰው በሚቀጣበት በትርና በሰው ልጆች መቀጫ እገሥጸዋለሁ” (2ኛሣሙ 7፣14)
-
ንጉሡም በዳዊት ዙፋን ላይ ይነግሳል፡፡ “ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥ መንግሥቱንም አጸናለሁ።” (2ኛሣሙ 7፣12)
-
እግዚአብሔር እንደገለፀው ይህም እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡“ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ እተክለውማለሁ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋኋላ አይናወጥ እንደ ቀድሞው ዘመንና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም ከጠላቶችህም አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ። ቤት እሠራልሃለሁ ብሎ ይነግርሃል።” (2ኛሣሙ 7፣11)
የነብያት ትምህርት
ተመሣሣይ ነጥቦችን መፅሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ በአፅንዖት የሚነግረን፡፡ የሚከተለውን ንባብ ከትንቢተ ኢሳያስ ስናነብ ይህም በአብዛኛው ጊዜ በገና ወቅት መጠቀሱ የተለመደ ነው፡፡ እናም ሶስት ተመሳሳይ ነጥቦችን መያዝ እንችላለን፡፡
“የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጣ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ ዳዊትም፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ አለ እርሱም፦ እነሆኝ ባሪያህ አለ።ዳዊትም፦ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ የአባትህንም የሳኦልን ምድር ሁሉ እመልስልሃለሁ፥ አንተም ሁልጊዜ ከገበታዬ እንጀራ ትበላለህ አለው።” (ት.ኢሳ 9፣6-7)
ተመሳሳይ ነጥቦች ላይ ትኩረት ሰጥቷል፡-
-
መንግስቱም ይበዛል ሠላሙም ፍፃሜ አይኖረውም
-
በዳዊት ዙፋንና መንግስት ላይ
-
ይህም የጌታ ፍቃድ ነው፡፡
ኢየሱስም ከተገቡ ቃልኪዳን አንዱ ነበር
በዳዊት የዘር ሐረግ ውስጥ አንድ ታላቅ ንጉስ እንደሚኔር ጥርጥር የለውም፡፡ መላዕኩ ገብርኤል ከክርስቶስ ልደት በፊት ተገልፃለት ይህን ነግሯት ነበር፡፡ “በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።” (ሉቃ 1፣ 32-33)
አሁንም ተመሳሳይ የሆኑ ሱስት ነጥቦችን እንመልከት፡
-
በመንግስቱም ለዘላለም ይኖራል
-
በዳዊት ዙፋን ላይ ይነግሳል
-
እግዚአብሔርም ይህ እንዲያልፍ ያደርጋል
የማርያም የምስጋና መዝሙር
በኋላም በተመሳሳይ መዕራፍ ሉቃስ እንደጻፈው ማርያም ለእግዚአብሔር ቃልኪዳን በተለየ የምስጋና መዝሙር አመስገነላት፡፡ ይህም የሚገላፀው እንዲሁም መላዕኩ ለማርያም እንደተናገረው እግዚአብሔር ለዳዊት የገባለትን ቃልኪዳን ለመፈፀም ልጅ ይወልዳል፡፡ ማርያምም እግዚአብሔር ለአብርሃም ለገባለት ቃል ኪዳን አመስግናለች፡፡ ማርያም በእርግጠኝነት እነዚህ ሁለት ቃልኪዳን የሚፈፀሙት በአንድ ሠው እንደሆነ አውቃለእ ማለት ነው፡፡
“ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።” (ሉቃ 1፣ 54-55)
መንግስቱ
ኢየሱስ ያለምንም ጥርጥር ወደዚህች ምድር ይመጣል፤ ትክክለኛውንም የእግዚአብሄርን መንግስት ይመሰርታል፡፡ እርሱም ንጉስ ይሆናል የእርሱም ተከታዮች የመሪነት ድርሻ ይኖራቸዋል፡፤ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንደተናገረው፡፡
“ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።” (ማቴ 19፣ 28)
ከመጀመሪያው ጀምሮ የእግዚአብሔር አላማ ምድርን በክብሩና በሰላም መሙላት ነው፡፡ “ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።” (ኦ.ዘኁ 14፣21)
ይህም የሚሆነው ኢየሱስ ንጉስ ሆኖ ተመልሶ ሲመጣ ይሆናል፡፡ አንዱና ዋነኛው ነጥብ ጴጥሮስ ሊያደርስን የፈለገው በጴንጤቆስጤ ቀን ኢየሱስ እግዚአብሔር ቃል እንደገባው ታላቅ የዳዊት የዘር ሐረግ እንደሆነ ገልፆልናል፡፡ ጴጥሮስም ጠቅሶ የፃፈው ቀደም ሲል ያየነውን በመዝሙረ ዳዊት እንደሚያሳየን ዳዊት ስለ እግዚአብሔር መንግስት መመስረትና ክርስቶስንም እንደ ንጉስ ይጠብቀው እንደነበር ነው፡፡
“ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፥” (የሐ.ሥራ 2፣29-30)
በተጨማሪም እንዳብራራው የኢየሱስ ትንሳኤ እግዚአብሔር ለዳዊት የገባለትን ቃልኪዳን መሟላት አይነተኛ ምልክት ያሳየናል፡፡ “ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤” (የሐ.ሥራ 2፣32)
ጴጥሮስ እንደተናገረው ዳዊት የተረዳው ያ ወቅት የሚመጣው ታላቁ አምላችን ለኢየሱስ ክርስቶስም እንዲመጣ ስነግረው ይሆናል፡፡
“ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፥ ነገር ግን እርሱ። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለውአለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።” (የሐ.ሥራ 2፣ 34-36)
የእግዚአብሔር ዋስትና
ጳውሎስ የተሰጡንን ልዩ ተስፋ ለአቴነስ ህዝቦች ሲነግራቸው፡ “ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።” (የሐ. ሥራ 17፣31)
ማጠቃለያ
-
እግዚአብሔር ለዚህች ምድርና ለእኛ ያለውን አላማ በመፅሐፍ ቅዱስ አሳይቶናል፡፡
-
አብርሃምና ዳዊት ሁለቱም በእግዚአብሔር የተነገራቸው ሲሆን አንዱም ይህ የእግዚአብሔር ዓላማ የሚፈፀምበት ከእነረሱ ዘር ከሆነው በአንዱ ይሆናል፡፡
-
ኢየሱስ አንዱ ቃልኪዳን የተገባለት ነበር
-
የእግዚአብሔር መንግስት ሲመስረት እርሱም አለምን በፅድቅ ይመራል፡፡
-
ይህ ተስፋ መሠረት ያደረገው በብልይ ኪዳን ትምህርት ላይ ሲሆን ስለ ኢየሱስና ሐዋሪያት መልዕክት በግልፅ ተቀማጧል፡፡
ለንባብ የቀረቡ ጥቅሶች
2ኛ ሣሙ 7 ፤ መ.ዳዊ 132 ፤ ት.ኢሳ 35 ፤ ሉቃ 1 ፤ የሐ.ሥራ 2 ፤ ሮሜ 4
ትምህርት ክፍል 7፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
በምድር ላይ በረከትን የሚያመጣው የአብርሃም ዘር ማን ነው?
ሀ. ይሣቅ ለ. ዮሴፍ ሐ. ዳዊት መ. ኢየሱስ
-
እስራኤላውያን በየትኛው ሀገር ነው በባርነት ይኖሩ የነበሩት?
ሀ. አፍሪካ ለ. ግብፅ ሐ. ከንአን መ. ኢጣሊያ
-
መፅሐፍ ቅዱስ ስለ እስራኤላውያን ከባርነት ነፃ ያወጣን የሚነግረን መፅሐፍ የቱ ነው?
ሀ. ኦ. ዘፍጥረት ለ. ኦ.ዘጸአት ሐ. ኦ.ዘሌዋውያን መ. ኦ.ዘኁልቅ
-
የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉስ ማን ይባላል?
ሀ. ሣዖል ለ. ዳዊት ሐ. ሠለሞን መ. ሣሙኤል
-
ዳዊት ለእግዚአብሔር ሊገነባለት የፈለገው ምን ነበር?
ሀ. ቤተመንግስት ለ. ቤተ መቅደስ ሐ. ከተማ መ. መታስቢያ ሀውልት
-
እግዚአብሔር ለዳዊት የገባለት ቃል ኪዳን ምን ነበር?
ሀ. ከፍተኛ ሀብት ሐ. የሚመሠረተው ዙፋን ለዘላለም ይኖራል
ለ. ረጅም ዕድሜና መልካም ጤንነት መ. ደስታና ባለፀግነት
-
በየትኛው የእስራኤል ነብይ ነው ይህ የተባለው?
ሀ. ኢሳያስ ለ. ሣሙኤል ሐ. ዳዊት መ. ሆሴዕ
-
ለዳዊት ቃል የተገባለት በዙፋኑ ላይ ለዘላለም የሚነግሠው ማን ነው?
ሀ. ሠለሞን ለ. እየሱስ ሐ. ሕዝቅኤል መ. ርዕባም
-
የእግዚአብሔር መንግስት የሚመስረተው የት ነው?
ሀ. በዚህች ምድር ለ. በሠማይ ሐ. በሠው ልጅ ልብ መ. በአየር ላይ
-
ጳውሎስ ለአቴንስ ሠዎች ሊጠቁማቸው የፈለገው የእግዚአብሔር ማረጋገጫ የሚያሳየን?
ሀ. በወቅቶች ለ. የእየሱስ ልደት ሐ. ቀንና ሌሊት መ. የኢየሱስ ትንሣኤ
ትምህርት ክፍል 8፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ
“ትንሣኤ” የሚለው ቃል ትርጉም “ከት መነሣት” ማለት ሲሆን፤ በአዲስ ኪዳን በግሪክ “አናስታሊስ” ተብሎ የተፃፈ ሲሆን ትርጉሙም “መነሣት ” ወይም “ዳግመኛ መቆም” ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ ከሞት ተነስቷል- ይህም ያለምንም ጥርጥር ማሳየት ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር ለሠው ዘር ያለው ዓላማ ማዕከላዊ ሃሣብ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነው፡፡ የክርስትያን እምነትም የተመሠረተው በዚሁ ዚሪያ ላይ ነው፡፡ ክርስትና ህልውና መሠረት ያደረገው በክርስቶስ ልደት በኋላ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በነበሩ ደቀመዘሙር ነበር፡፡
የትንሣኤ አስፈላጊነት
ኢየሱስ ወደ ሠማይ ካረገ በኋላ እንደሚያስተምረን ሐዋሪያትን እንዴት እንደመረጡ ያስተምረናል፡፡ እንደምናነበውም ማትያስን መርጠዋል፡፡ “ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።” (የሐ.ሥራ 1፣22)
ሐዋሪያቱም በዚህም ምክንያት ታስረዋል፡ “ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ ተቸግረው፥ ወደ እነርሱ ቀረቡ፥” (የሐ.ሥራ 4፣2)
ጳውሎስ በነዚህ ጥያቄዎች ለእንግልት በቅቷል፡፡ “ጳውሎስ ግን እኵሌቶቹ ሰዱቃውያን እኵሌቶቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን አይቶ። ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊም ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስፋና ስለ ሙታን መነሣት ይፈርዱብኛል ብሎ በሸንጎው ጮኸ።” (የሐ.ሥራ 23፣ 6፤ የሐ.ሠራ 24፣21)
በአዲስ ኪዳን ያሉ መልዕክቶች ሙሉ በሙሉ የሚያስተምሩን ስለ እየሱስ ትንሣኤና ይህም ለእኛ የሚያስገኝውን ጠቀሜታ ነው፡፡ ይህም በሐዋሪያው ጳውሎስ በጥልቀት እንደተነገረው “ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤……..ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ።” (1ኛ ቆሮ 15፣14 ና 17)
እግዚአብሔር ኢየሱስን ለምን ከሞት አስነሣው?
በቀደሙት የትምህርት ክፍሎች እንደተማረው ለእኛ ኃጥያት የከፈለውን የመስዋዕትነት ሥራ አይተናል(ዕብ 9፣ 26) የኢየሱስ ሞት በእርግጥ ሞቶ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ የተዋጣለት መስዋዕትነት ባልሆነ ነበር፡፡ በትምህርት ክፍል 4 እንደተገለፀው ለእግዚአብሔር ትዕዛዝ አዳም ባለመታዘዙ ምክንያት እንዴት በሠው ልጆች ኃጥያትና ሞት እንደመጣ ተመልክተናል፤ በአንፃሩም ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ሁሉን ትዕዛዝ መጠበቅና የፅድቅን ሕይወትን በመኖሩ በትምህርት ክፍል 6 ተረድተናል፡፡
እየሱስ እርሱም “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤”(ገላ 4፣4) በተመሣሣይ የሞት ፍርድ ልክ አንደኛው ከአዳም ወረሷል፡፡ ቢሆንም እርሱ ግን ምንም ኃጥያትን ስላልሰራ ሞትም እርሱን ይዞ ማስቀረት አልቻለም፡፡ ፃድቅ የሆነው የእግዚአብሔር መርህ እንደነዚህ ያሉ ሠዎች እንዲቀሩ አያደርጋቸውም፡ እነዚህም ፍፁም ህጉን የጠበቁ በሞትና በኃጥያት እንዲታሰሩ አያደርጋቸውም፡፡ ሐዋሪያው ጴጥሮስ እንደሚነግረን፡- “እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።”(የሐ.ሥራ 2፣24)
በትምህርት ክፍል 3 እንደተማርነው የእግዚአብሔር ፍፁም ፍህታዊነትና እንዲሁም ለሠዎች የነበረው ፍቅር ምክንያት ኢየሱስን ከሞት አስነስቶታል፡፡ “በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው።” (የሐ 3፣ 16)
በትንሣኤ ስለማመን
እየተመለከትን እንዳለነው አብርሃምና ዳዊት የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ለማጣጣም ከሞት እንደሚነሱም ይጠበቃል፤ ይህም ተስፋ የእነሱ ብቻ አይደለም፡፡ ከመፅሐፍ ቅዱስ እንደተማርነው ከሞት ዳግመኛ መነሳት ከክርስቶስ ዘመን በፊት የነበሩ አማኞእ ተስፋ ነበር፡፡ ኢየሱስም ይህን ያለው ለዚህ ነበር፡፡ “አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።” (የሐ 8፣56)
ጴጥሮስም የእስራኤል የንጉስ ዳዊትን ቃላት እንደወሰደው “ዳዊት ስለ እርሱ እንዲህ ይላልና። ጌታን ሁልጊዜ በፊቴ አየሁት፥ እንዳልታወክ በቀኜ ነውና። ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ልሳኔም ሐሤት አደረገ፥ ደግሞም ሥጋዬ በተስፋ ያድራል፤ …..ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ።” (የሐ.ሥራ 2፣25-26 ፤ 31) የተወስደውም ” ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም።ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለችነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።” (መ.ዳዊ 16፣ 8-11)
ዳዊትም እንደተናገረው “እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።” (መ.ዳዊ 17፣15)
ዕዮብ እንደተናገረው፡ “እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።” (ኢዮ 19፣25-26)
ኢሳያስ እንደተናገረው፡ “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።” (ት.ኢሳ 26፣19)
ለዳንኤል እንደተነገረው፡ “በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።…..አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ አንተም ታርፋለህ፥ በቀኑም መጨረሻ በዕጣ ክፍልህ ትቆማለህ።”(ት.ዳን 12፣2 ፤ 13) እናም አርሱም በሞት አንቀላፍቷል፡፡
ሐዋሪያው ጳውሎስም እንዳረጋገጠልን ከእየሱስም በፊት የነበሩትም ይህን ተስፋ ያደርጉ ነበር፡፡ “ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ ይሆን ዘንድ ያለውን፥ ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በሙታንም ትንሣኤ ለሕዝብና ለአሕዛብ ብርሃንን በመጀመሪያ ሊሰብክ እንዳለው፥ ከተናገሩት በቀር አንድ ስንኳ የተናገርሁት የለም።” (የሐ.ሥራ 26፣ 22-23)
ትንሣኤ - ብቸኛው እውነተኛ ተስፋ
ጴጥሮስ በግልፅ እንደተናገረው፡ “ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፥” (የሐ.ሥራ 2፣34) እንደተመለከትነው ይህ የዳዊት ተስፋ አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር ቃልኪዳንን የገባው ክርስቶስ በእርሱ (ዳዊት) ዙፋን ላይ በእየሩሣሌም ይነግሣል፡፡(የሐ.ሥራ 2፣30)
ጳውሎስ በንግግሩ ለአቴንስ እንዳብራራው ወይም (በትምህርት ክፍል 7 እንደተጠቀስው፡፡) የኢየሱስ ከሞት መነሣት የክርስቶስን ምድርን በፅድቅ ወቅቱ ሲደርስ እንደሚመራ ማረጋገጫችን ነው፡፡(የሐ.ሥራ 17፣31)
የኢየሱስ ተከታይ የነበረችው ማርታና በግልፅ ማየት እንደምንችለው የእረሷየወደፊት ሕያወቷ ተስፋዋ ነበር፡፡ ወንድሟ አላዓዛር በሞተ ጊዜ የሠጠችውን ምላሽ እንደሰማነው፡፡ “ኢየሱስም፦ ወንድምሽ ይነሣል አላት።ማርታም። በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲነሣ አውቃለሁ አለችው።ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (የሐ 11፣ 23-25)
ጳውሎስም ሲከራከር ስለዚህ ተስፋ ተናግሯል፡፡ “እነዚህም ራሳቸው ደግሞ የሚጠብቁት፥ ጻድቃንም ዓመፀኞችም ከሙታን ይነሡ ዘንድ እንዳላቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ።”(የሐ.ሥራ 24፣ 15)
ከሞት ማን ይነሣ ይሆን?
ቅዱሳን መፃሕፍት እንደሚነግሩን፡ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”(ሮሜ 6፣ 23) እግዚአብሔርን የማይፈልጉና ወይም እርሱን ለማገልገል ፍቃደኛ ያልሆኑ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳየንን ዓላማ መረዳት ያልቻሉ የእግዚአብሔርን ሥጦታ አያገኙም፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ሁሉም ከሞት አይነሱም ለዳንኤል እንደተነገረው “በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።” (ት.ዳን 12፣ 2) ይህም እንደሚነግረን በዚያን ወቅት ሱስት የሠዎች ክፍፍል ይኖራል፡፡
-
ሰለ እግዚአብሔር ምንም የማያውቅና ከሞትም በፍፁም የማይነሱ
-
እግዚአብሔርን የማይወዱና የማይገዙ ሰዎች ሲሆኑ እነዚህም ዘላለማዊ የሞት ፍርድን ይቀበላሉ፡፡
-
ፃዲቅ ሠዎች እነዚህን ከሞት በመነሣት ዘላለማዊ ሕይወት ያገኛሉ፡፡
ስለ መጀመሪያዎቹ ምድብ አይነት ስዎች በብዙ ቦታዎች ላይ አንብበናል፡
-
“ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።” (ምሳ 21፣ 16)
-
“አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው እንደሚጠፋ እንስሶች መሰለ።” (መ.ዳዊ 49፣ 20)
-
“እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም ጠፍተዋል፥ አይነሡም ስለዚህ አንተ ጐብኝተሃቸዋል አጥፍተሃቸውማል፥ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ምንምን አድርገሃል።”(ት.ኢሳ 26፣ 14)
ስለ ሁለተኛዎቹ ምድብ አይነት ሠዎችም ብዙ ቦታ ተነግሯል፡፡
“እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።” (ማቴ 25፣ 46)
“በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።” (የሐ 5፣ 29)
“አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያችሁ ጊዜ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” (ሉቃ 13፣28)
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከእነዚህ አረፍተ ነገር በማነፃጸር ኢየሱስ እንዲህ በማለት ተስፋ ሰጥቶናል፡፡
“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” (የሐ 17፣ 3)
ስለ ፃድቃን የሚደረግላቸው ስጦታም የሚነገሩ ጥቅሶችንም እንመልከት፡፡
“ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።” (ማቴ 25፣ 34)
“ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ።…….ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ።” (መ.ዳዊ 37፣ 9 ና 29)
“በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።” (ማቴ 13፣ 43)
እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ባለው ዕቅድ ውስጥ ተካፋይ እንድንሆን፤ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል፡፡ እውነተኛውን እግዚአብሔርን ማወቅ እና ስለቃሉ ትክክለኛነት መረዳት ሊኖረን ይገባል፡፡ ቢሆንም ዕውቀት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን መውደድም ይኖርብናል እናም እግዚአብሔርን ከወደድን ትዕዛዘሁንም እናከብራለን፡፡ “የሐ 15፣ 10” በዚህ ዕውቀትና በዚህም ዕውነታ ማመን ወደ ቀጣዩ ደረጃ እናልፋለን ይህም በክርስቶስ መጠመቅ በትምህርት ክፍል 11 በስፋት እናያልን፡፡ ጳዉሎስ ለትክክለኛ አማኞች እና ትንሣኤን ማግኝት ለሚፈልጉ ስለጥምቀት አስፈላጊነትም ጠቃሚ ነጥቦችን ነቅሶ አውጥቷል፡፡ “ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤” (ሮሜ 6፣ 3-5)
ክርስቶስ የትንሣኤ መጀመሪያ - ሌሎችም ይከተሉታል
መፅሐፍ ቅዱስ በግልፅ እንደሚያሳየን እየሱስ ከሞት በመነሳት ህያው የሆነ የመጀመሪያው ነው፡፡ ጳውሎስም ስለዚህ ሲፅፍ ፡ “አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።” (2ኛ ጢሞ 1፣ 10) ይህ ሕይወትና ኢየሱስ ያገኝው ህያውነት ከሞት መነሣት የተስፋን ብርሃን ጭላንጭል በምድር ላይ እንዲሆን አድርጓል፡፡ ጳውሎስም እንደነገረን ፡ “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።” (1ኛ ቆሮ 15፣ 20) የመጀመሪያው ፍሬ የመጀመሪያው የእርሻ ውጤት ነው፤ ይህም ተጨማሪ የብዙ ጥሩ ነገሮች መምጣት ምልክት ነው፡፡ ጳውሎስ ይህን የእርሻ ምሳሌ የተጠቀመው ስለ ትንሣኤ ቅደም ተከተል ለማሳየት ነው፡ “ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤” (1ኛ ቆሮ 15፣ 23)
በኢየሱስ ዳግም መምጣት ወቅት ከሞት ስለሚነሱት በኢየሱስ ዳግመኛ መምጣት በመጨረሻም የሚኖረው ትንሳኤ ውስጥ መሰባስብ፡ “በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤” (2ኛ ጢሞ 4፣ 1)
ጳዉሎስ እንደፃፈው፡
“ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤” (1ኛ ተሰሎ 4፣ 13-16”
ትንሣኤና ፍርድ
እንደተመለከትነው ድንኤል እንደተነገረው “በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።” (ት.ዳን 12፣2) ይህም የሚነግረን በሞት የተነሱትን በጋራ መሰባሰብና በክርስቶስ ዳግም መምጣት ወቅት በሕይወት የሚኖሩ ስለ ፍርዳቸው ሲሆን በኢየሱስ ሊኖራቸው ስለሚችለው አለመፈለግ ነው፡፡ኢየሱስም ያስተማረው ይህንኑ ነው፡፡
“በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።” (የሐ 5፣ 28-29)
የሚመለከታቸውም ሠዎች በሙሉ (እነዚህም ስለ እግዚአብሔር የሚያቁና መንገዱን የተከተሉ ወይም ያልተቀበሉ ናቸው) በኢየሱስ ክርስቶስ በፍርድ ወንበር ስር ሁሉም ይቀርባሉ፡፡ በእግዚአብሔርም ታምነው የኖሩ፣ስለፍቅሩና ክብሩ ዕውቀት ያላቸውና እርሱንም ለማገልገል የሞከሩ እና ተወዳጅ ልጁን ምሣሌ በማድረግ የተከተሉት በእግዚአብሔር ክብር ፍቃድ በዚያች ቀን የዘላለም ሕይወት ስጦታን ይቀበላሉ፡፡
ኢየሱስ ለሁላችንም ሲነግረን እንዲህ በማለት ነው፡፡ “እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ አላቸው።” (የሐ 11፣ 15)
ማጠቃለያ
-
በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እውነት ነው ይህም የአዲስ ኪዳን ዋነኛ ትምህርት ነው፡፡
-
ኢየሱስ ከሞት መነሣት ችሏል ምክንያቱም ምንም ኃጥያትን አልሰራም የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍትሐዊነት በመቃብር እንዲቆይ አላደረገውም፡፡
-
ትንሣኤ የሁሉም አማኞች ተስፋ ነው፤ ከኢየሱስ ልደት በፊትም ሆነ ከዚያ ጀምሮ ያሉት፡፡
-
በአሁን ወቅት ዘላለማዊ ነፍስ የለንም፤ ይህን ቢኖረን ኖሮ እግዚአብሔር ይህን ቃልኪዳን ለእኛ መግባቱ ባላስፈለገው ነበር ወይም ለዚህም ተስፋ የማይገባልን ጉዳይ ነበር፡፡
-
ሠው በተፈጥሮው ሟች ነው፣ ኢየሱስም ለሠዎች ሁሉ ድነትን ለማምጣት መስዋዕት የሆነበትም ምክንያትም ይህ ነው፡፡
-
ሁሉም ከሞት አይነሱም፤ እነዚህም ምንም ዕውቀት የሌላቸው በመቃብር ይቀራሉ፡፡
-
መረዳት፣ማመንና መጠመቅ ክርስቶስንና ትንሣዬውን መቀበል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
-
ኢየሱስ የመጀመሪያው ህያው ሆኖ የተነሳ ነው፤ በእርሱ ምሣሌነት ተከትለን እኛም እንደ እርሱ እንሆናለን
-
ትንሣኤና ፍርድ ኢየሱስ ወደ ምድር ተመልሶ ሲመጣ ይደረጋል፡፡
ለተጨማሪ ንባብ የቀረቡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
መ.ዳዊ 37 ፤ ት.ኢሳ 26 ፤ ማር 16 ፤ የሐ 11 ፤ የሐሠራ 26 ፤ 1ኛ ቆሮ 15
ትምህርት ክፍል 8፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
“ትንሣኤ” ሚለው ቃል ትርጉም
ሀ.ገዳም ለ. ወደላይ መንጠራራት ሐ. ከሞት መነሳት መ. መባነን
-
በብሉይ ኪዳን የነበሩ የሚያምኑ ሠዎች ምንን በተስፋ የጠብቁ ነበር
ሀ. በስማይ ስለሚኖር ዘላለማዊ ሕይወት ሐ. አናውቅም
ለ. ትንሣኤን መ. ምንም ተስፋ አያደርጉም ነበር
-
ዘላለማዊ ሕይወትን ከሞት በመነሣት ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኝው መን ነው
ሀ. አላዓዛር ለ. ኢየሱስ ሐ. ሰቴፈን መ. የመቶ አለቃው
-
የኢየሱስ ትንሣኤ ለእኛ ምን ያስተምረናል
ሀ. ምንም
ለ. የሚያምኑ ሠዎች በፍፁማ አይሞቱም
ሐ. ከሞት መነሣት እንደምንችል
መ. ከኢየሱስ በፊት የነበሩ የሚያምኑ ሰዎች ከሞት ተነስተው በሠማይ ናቸው
-
እየሱስ ከሞት የተነሣው ለምን ነበር
ሀ. ምክንያቱም ኃጥያት ስላልሰራ እናም ሞት ስለማይገባው
ለ. ጥምቀት የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤ ተምሳሌት በመሆኑ
ሐ.እርሱ አልበነበረም - አሁኑም እንደ ሞተ ነው
መ. እርሱ አልነበረም - እርሱ አልሞተም
-
ከሚከተሉት ሦስቱ ስለ ወደፊቱ በምድር ላይ የሚኖረው ሥጦታ ያሳያል (1ኛነገ 14፣16ስለ ኢዮርብዓም እንመልከት)
ሀ. አብርሃም ለ. ዳዊት ሐ. ዳንኤል መ.ኢዮርብዓም
-
እያንዳነዱ ሰው ከሞት ይነሱ ይሆን
ሀ. ማንም አይነሳም ለ. አዎ ሐ.ሊነሱ ይችሉ ይሆናል መ. አናውቅም
-
ሙታን የሚነሱት መቼ ይሆን
ሀ. ከሞት በኋላ ሲኖሩ ሐ. ኢየሱስ የእግዘጀአብሔርን መንግስት ሊመስርት ሲመጣ
ለ. በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም አይነት ቃል ኪዳን የለም መ. አናውቅም
-
ከትንሣኤ ሙታን በኋላ ምን ይከሰታል
ሀ. ጥምቀት ሐ. መፅሐፍ ቅዱስ ይማራሉ
ለ. ፍርድ መ. ሁሉም የመ ስጋናን መዝሙር ይዘምራሉ
-
በመጨረሻው ቀን በኢየሱስ ማን ተቀባይትን ያገኛል
ሀ. እነዚያ መልዕክቱን የተረዱ፣በእርሱም ያመኑና የታዘዙለት
ለ. መልካም ነገርን የሠሩና ሠውን የረዱ
ሐ. እነዚያ ባለማመን የሞቱ
መ. እነዚያ በዚያን ወቅት በሕይወት የሚኖሩ
ትምህርት ከፍል 9 - የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የታሪክ ዕውነታ ሲሆን በዚህም የሁሉም ሠዎች ተስፋ በዚው ነበር፡፡ ልክ የኢየሱስን ከሞት መነሣት ዕርግጠኛ እንደሆን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃልኪዳንም ልጁ ዳግመኛ ወደ ምድር እንደሚመጣም እርግጠኞች ነን፡፡ ክርስቶስ ከሞት እንደተሰሣ ወደ ሠማይ አርጓል እናም መላዕክት ለደቀመዘሙራኑ እንዲህ የሚል ቃልኪዳን ነግረዋቸዋል፡፡”ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” (የሐዋ.ሥራ 1፣11) ልክ እንዲሁ ወደ ሠማይ እንደተነጠቀው እንዲሁ ተመልሶ ይመጣል፡፡
የኢየሱስ ዳግመኛ መምጣት ምንን ያመለክታል?
የተወሰኑት እንደሚሞግቱት ኢየሱስ ዳግመኛ መጥቷል ይላሉ፤ ይህም አመጣጡ ሚስጢራዊ ወይም ያም ደግሞ መምጣቱ ምናባዊ- በአማኞች ልብ መንገሱን፡፡ ቢሆንም ይህ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን አይደለም፡፡ እኛ የተነገረን “እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።” (ራዕ 1፣ 7) ቃል በቃል እንደተነገረን ኢየሱስ ዳግመኛ ይመጣል ፤ በአካል ወደ ምድር እናም ሁሉሙ የእርሱን ዳግመኛ መምጣት፤ በአካልም ወደ ምድር እናም ሁሉም የእርሱን ዳግመኛ መምጣት ያውቃሉ፡፡
“እንግዲህ። እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤….. የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤” (ማቴ 24፣ 26-27 ና 30)
ነገር ግን ኢየሱስ ዳግመኛ መምጣት ለምን አስፈለገው?
የኢየሱስ ዳግመኛ መምጣት ዓላማ
በጌታ ፀሎት ኢየሱስ እንዳስተማረን ተከታዮቹ ሲጸልዩ መንግስቱ በምድር እንድትመሠረት ነው፡፡ “ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤” (ማቴ 6፣ 10)
በዚህ ወቅት የዳዊት ቃል ይፈፀማል፡፡ “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ።” (መ.ዳዊ 37፣ 29)
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ተመልሶ የሚመጣው የእግዚአብሔርን መንግስት ለመመስረት ሲሆን አሁን ያለውን የሠዎች መንግስትን ይገለብጣል፡፡ የአለምንም ደካማነት ይለውጣል እናም ምድር በእግዚአብሔር ክብር ትሞላለች፤ ይህም አሁን ላሉ ችግሮች በሙሉ መለኮታዊ መፍትሔ ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ሐዋሪያው ጳውሎስ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ፤ ቲቶን ከእግዚአብሔር ያልሆኑና አለማዊ በለፀግነትን እንዲተው ሲያበረታታው እና ለዚህ ፡“ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤” (ቲቶ 2፣ 12-13)
ክርስቶስ መቼ ይመጣል?
ከመጀመሪያው እግዚአብሔር ክርስቶስ ወደ ምድር ለፍርድ መቼ እንደሚመጣ ቀን ወስኗል፡፡ ጰውሎስ ስለዚህ እንደነገረን፡ “ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።” (የሐዋ.ሠራ 17፣ 31)
በምድርም በነበረበት ወቅት ክርስቶስ በስብከቱ በጣም ግልፅ እንዳደረገው በእግዚአብሔር ዕቅድ የወጣለት ቢሆንም ክስተቶችን በቅድመ ተከተል ይከስታሉ፤ እርሱም ቢሆን የሚመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ አያውቅም፡፡ በማርቆስ 13 ክርስቶስ ስለ ዳግም መምጣቱ ለሚያደምጡ ሲናገርና ከመምጣቱ አስቀድሞ በሚከሰቱ ነገሮች የሠጣቸውን የተወሰኑ ማመላከቻ ከንግግሩ ውስጥ እናገኛለን፡፡
“በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።” (ማር 13፣ 26)
“ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።” (ማር 13፣ 32)
ክርስቶስ እንደ ሌባ ባልተጠበቀ ወቅት ይመጣል በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ ሠዎች በክርስቶስ ደግመኛ መምጣት አያምኑም፡፡ ይህም በትክክል ነገሮችን ተመልክቶ ስለኛ ዘላለማዊ ሕይወትን ካለመጠበቅ የመነጨ ነው፡፡ ሐዋሪው ጴጥሮስ እንደዚህ የሚያምኑትን ሲያስጠነቅቅ፡ “በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤እርሱም፦ የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው? አባቶች ከሞቱባት ጊዜ፥ ከፍጥረት መጀመሪያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራልና ይላሉ።……..ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።” (2ኛ ጴጥ 3፣ 3-4 ና 9)
እግዚአብሄር ቃሉን ሲፈፅም እንደማይዘገይ ማረጋገጫ ተሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን ይህ በአለም ላይ የሚከሰቱ ነገሮች በጊዜያቸውና እርሱ ባስቀመጣቸው አግባብ ይካሄዳሉ፡፡ “በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤” (1ኛተሰ 5፣ 2)
ትክክለኛውን የእየሱስ መምጫ ሠዓት ከእግዚአብሄር በስተቀር ማንም አያውቅም እናም ከቅዱሳን መፃህፍትም ይህን ፈልጎ ማግኝት አይቻልም፡፡ ኢየሱስ እንዳለው “ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።” (ማቴ 24፣ 44)
ይህም እንደሚያስተምረን አማኞች በክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ማመን ይኖርባቸዋል እናም ለዚሁ የተዘጋጁ መሆን አለባቸው፤ ምክንያቱም ይህ መቼ እንደሚሆን ትክክለኛውን ቀን የሚያውቀው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እነዚያ ይህን የማይጠብቁ፤ የእርሱ አመጣጥ በጨለማ ሳይጠበቅ እንደሚመጣ ሌባ ይሆንባቸዋል፡፡
የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ምልክቶች
ደቀመዛሙርቱ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት መቅረብ እንዴት መናገር እንዳለባአው ማወቅ ፈልገው በደብረ ታቦር ተራራ ሲቀመጡ በግል ጠየቁት፡ “እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።” (ማቴ 24፣ 3)
ኢየሱስም ለጥያቄያቸው ሲመልስ እርሱ የሚመጣበት ቀን ሲቃረብ ሊኖሩ ስለሚችሉ ሁኔታዎች አብራርቶላቸዋል፡፡ ብዙተጨማሪ የመፅሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችም እንደሚሠጡን “የጊዜው መቅረብ ምልክቶች” የክርስቶስን ተከታዮች ለማበረታታት እና ለእርሱም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ለመርዳት ሲባል ተፅፈዋል፡፡
-
የኖህ ምልክት
በመልሱም ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ከጥፋት ውሃ ቀን በፊት ስለ ነበረው አንዲያስታውሱ አድርጓል፡፡ምክንያቱም ከእርሱ ዳግመኛ መምጣት በፊት ተመሣሣይ ሁኔታ ሊከሰት ይችላልና፡ “የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።” (ማቴ 24፣37-39)
ለኖህ ወቅት ስለነበረው ጊዜ ኦሪት ዘፍጥረት መዕራፍ 6 እናንብብ፤ በዚህም በግልፅ እግዚአብሄር ሠውን ዘር ለምን እንዳጠፋው ይነግረናል እናምስምንት ሠዎች ብቻ ተርፈዋል፡፡ በሠው ሃሣብና ተግባር ክፋት ነግሶ ነበር፡፡እግዚአብሄርም ተመለከተ፡ “ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸች ምድርም ግፍን ተሞላች።” (ኦ.ዘፍ 6፣11)
ሕትመቶች፤ ኢንተርኔት፣ ሬድዮ ና ቴሌቭዥን በየቀኑ የሚያንፀባርቁትም ትርምስ የበዛበትንና እግዚአብሄር አልባ ከኖህ ወቅት የነበረውን ተመሣሣይነት ነው፡፡ በብዙ መልኩ ከሐዋሪያው ጳውሎስ ስለ መጨረሻዎቹ የክርስቶስ መምጫ ወቅት ስለ ሰዎች የገለፀው ጋር እጅጉን ይመሳሰላል፡፡ “ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።” (2ኛጢሞ 3፣1-5)
በጥንቃቄ እያንዳንዱን የገለፃ የትንቢት ቃላት ብንመለከት ይህ የሚያሳየን ገለፃው በትክክል ከእኛ ዘመን በእጅጉ በበለጠ የእኛን ዕድሜ ዘመንን ይገልፃሉ፡፡
-
የበለሷ ዛፍ ትምህርት
ኢየሱስ እራሱ አጠር ባለ ምሳሌ እንደተጨማሪ ምልክት ለደቀ መዛሙርቱ መምጫው ሲቃረብ ሲነግራቸው፡ “ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።” (ማቴ 24፣ 32-33)
ቀደም ሲል ባነበብናቸው የማቴዎስ 24 ስለ ምልክቶቹ የተተነበየባቸው ቁጥሮች ላይ ያለው ሲፈፀም ፤ እኛም የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት መቅረቡን እናውቃለን፡፡
የተወሰኑ ሠዎች ይህ ምሳሌ የሚናገረው ስለ እስራኤል በሰዕላዊ ቋንቋ ነው ብለው ያምናል፤ እስራኤላውያን ወደ ምድራቸው ተመልሠው ሲመጡ በእግዚአብሄር በተገባላቸው ቃልኪዳን መሠረት ገና ጀማሪ ሕዝቦች ነበሩ፡፡ ልክ እንደ ዛፍ ስር ስር የሰደደ ነው፡፡ ይህ የእስራኤል መሰባሰብ በ1948 ተፈፅሟል፤ የእስራኤል መንግስት ዕውቅናን አግኝታለች፡፡ ከ200ዓመታት በኋላ በተለያዩ ሀገራት ውስጥ ከተበታተኑት ና ከጠፉ በኋላ መሰባሰብ ችለዋል፡፡ ይህ ዳግም መሰባስብ ምን ይከተለው ይሆን?
“የሰላምም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘላለምም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል እኔም እባርካቸዋለሁ አበዛቸውማለሁ መቅደሴንም ለዘላለም በመካከላቸው አኖራለሁ።” (ት.ሕዝ 37፣ 26)
የይሁዳውያን ዛሬ በእራሳቸው ምድር ላይ ናቸው ነገር ግን የእግዚአብሄር ፍፅም ጥባቆት እስካሁን አልተመሠረተም፤ የይሁዳውያን ወደ እስራኤል መመለስ ትንቢቱን ሙሉ በሙሉ ሲፈጸም የእግዚአብሄር መንግስት መመስረትን የውጃል፡፡
ማስታወስ የሚኖርብን፡ “እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።” (ማቴ 24፣ 33)
-
እስራኤልን በተመለከተ የእየሱስ ትንቢት
ኢየሱስ እጅግ ግልጽ የሆነ በሕዝቦች ላይ በቅርብ ስለሚከሰተውና ስለወደፊትም ዕጣ ፋንት እጅግ ግለፅ የሆነ ትንበያን ሰጥቷል፡፡ የሀገራትም መሪዎች የእግዚአብሔርን ዕቅድን ለማየት ተስኗቸዋል፡፡ እርሱ አንድያ ልጁንም መሲ (አዳኝ) ልኮላቸው እነርሱም ገድለውታል፡፡ ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ በተራራ ላይ ቆመው እየሩሳሌምን ተመልክተው ሁሉም ለእርሱ እስራቱና ስቅላቱ ቀድሚያ ሰጥተዋል፡፡ የቤተመቅደሱን ውበት ሲመለከት ደቀመዛሙረቱም በመደነቅ ተናግረዋል፡፡
“ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል አለ።……..በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።” (ሉቃ 21፣6 ና 24)
ይህም ትንቢት መፈፀም የጀመረው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ 70 ዓመተ ምህረት የሮማውያን መንግስት ወታደሯን በላከችለት ወቅት ሲሆን በቲቶም በመጠቀም ወረራን አካሂደዋል፡፡ የእሩሳሌምን ከተማ በማውደም ና መሬቷንም በመቆፈር ምስቅልቅሉን አውጥተዋል፡፡ ኦሪት ዘዳግም 28 በተጨማሪ ሲፈፀም ና የሁሉም ህዝቦቿ ተበታትነው አልቀዋል፡፡ አንድም አይሁድ በዚህች ምድር እንዲቀር አልተፈቀደለትም፡፡ ከክርስቶስ ልደት በኋላ 135 ዓ.ም ሌላ በይሁዳ እያንሰራሩ ያሉ አይሁዳውያኑን የማስወገጂያ መንግስታዊ ተዕዛዝ ዓላመን አንግበው በመነሳት እንዲሁም እስራኤል የሚለው ስያሜ “ኤሊያካፒቶሊና” በሚል ሊቀየር ችሏል፡፡
አይሁዳውያንንም ስያሳድዷቸው ዘመናት ተቆጥሯላ፤፤ በወቅቱ በተለያዩ የጦር አውድማ የተማረኩ ምርኮኛ አይሁዳውያን በአለም ዙሪያ ሁሉ በመበታተን በባርነት አገልግለዋል፡፡ ከዚህም ስቃይና እንግልት ያመለጡ ጥቂት ዕድለኞች ሀባታምና ነጋዴዎች ሆነዋል፡፡ በሁሉም የአለም ስፍራ ሁሉ በመፍለስ ሠፍረዋል፡፡ ነገር ግን እንግልትና መድሎ የሕይወት ጎዳናቸው ሆኗል፡፡ በመጨረሻም የሚጠበቀው ታምራዊ የእስራኤል ዳግም መሰባሰብ እና እየሩሳሌምን በእራሳቸው ቁጥጥር ስር የሚያውሉበትም ቀን ዕውን ሆኗል፡፡ በ 1967 እስራኤላውያን እየሩሳሌምን ተቆጣጠሩ እናም ወደ 2000 ዓመታት የሚጠጋ ያጧትን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ዋለች፡፡
-
የእስራኤል ዳግመኛ መወለድ
ኤርምያስ በትንቢት ከነገረን በላይ ምንም ግልፅ የሚያደርገው የለም፡፡ “እነሆ፥ በቍጣዬና በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፥ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ” (ት.ኤር 32፣ 37)
ወደ 2000ዓመታት በአለም ዙሪያ ባሉ ህዝቦች መካከል ከተበታተኑ በኋላ፤ የትንቢቱ ፍፃሜ ሲመጣ አይሁዳውያኑ ወደ እስራኤል ምድር ተመልሰው በ 1948 እራሳቸውን የቻሉ መንግስት ሆነዋል፡፡ ልክ እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘመናት እግዚአብሄር ህዝቡን በመምራት ለድል አብቅቷቸዋል፡፡ በዚህም ነብያት ቀድመው የነገሩን ሁሉ በመፈፀማ አልፈዋል፡፡
ትንቢተ ሕዝቅኤል 36- 37 ውስጥ እጅግ የሚያስገርም ትንቢትን ይዟል፤ ይህም የሚያሳየን በመንግስታት ጉዳይ ላይ እግዚአብሄር ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ነው፡፡ ነብያት ነየእስራኤላውያንን ወደ ምድራቸው መሰባሰብ እግዚአብሄር
በራዕይ ገልፆላቸው ስለዚህም አስቀድመው ነግረውናል፡ “ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ ወደ ገዛ ምድራችሁም አመጣችኋለሁ።……….አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።……….ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ ሕዝብም ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።” (ት. ሕዝ 36፣ 24፤ 26፤ 28)
ቀጥሎም በደረቅ አጥንት የተሞልን ሸለቆን በኃያል ክንድ የመቀየሩ ራዕይ ውስጥ እግዚአብሄር ተጨማሪ ለዚህ ማረጋገጫን ሰጥቶናል፡፡
“እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።……አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ከአሕዛብ መካከል እወስዳለሁ ከስፍራም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ” (ት.ሕዝ 37፣ 10፤21)
ከ1948 ጅምሮ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ አይሁዳውያን ወደ እስራኤል ተመልስዋል፤ ቀጣዩም ታላቅ ክስትም መንግስቱን በእስራኤልና በመላው አለም ዙቲያ ለመመስረት የክርስቶሰ ዳግም መምጣት ይሆናል፡፡
-
የናቡከደነፆር ህልም ምልክት
በትምህርት ክፍል 3 ይህን ህልም ሙሉ በሙሉ አያተናል፡፡ ዳንኤለም የሰጠው ፍች የዚህችን አለም ታሪክ አሳይቶናል፡፡
እኛ ዛሬ በምስሉ እግዚአብሄር የተገለፀን ሁነን እናገኛለን፤ አንዳንድ ኃያላን ሐገሮች (ብረት) እና የተወስኑት ደካማ ሐገራት(ሸክላ) እነዚህን በሚፈለገው ደረጃ ሊዋሃድ አይችሉም፡፡ ዳንኤል በመቀጠልም፡ “በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።” (ት.ዳን 2፣ 44)
ይህም እንደሚያሳየን ክርስቶስ ዳግመኛ አስኪመጣ ድረስ ምንም አይነት ተጨማሪ የአለም መንግስት አይኖርም፡፡
ይህም የዳንኤል ትንቢ ፍፃሞ ይሆናል፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ አስከ እርሱ ጊዜ ስለ ነበሩት ትንቢቴእ ኑሉ በሙሉ እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ ነበር፡፡ በቆላሲያስ የነብሩ አማኞችንም ሊያበረታታ ችሎ ነበር፡፡ ምክንያቱም ስለ ክርስቶስ ዳግም መምጣት በእርግጠኝነት ያውቅ ነበረና፡፡
“ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።” (ቆላ 3፣4)
-
አጠቃላይ የአለማችን አለመረጋጋት ምልክት
ይህም በግልጽ እየሆነ ያለ ዕውነታ ነው፤ ክርስቶስም በስዕላዊ አገላለፅ ስለ መሪዎች ስልጣን ሲናገር በባህርና ወጀብ ህዝብን መስሏል (በት.ኢሳ 57፣ 20) የህም የሚሰጠን ምስል በምድር ላይ ያሉ ህዝቦች በክስተቶች ሁኔታዎች ላይ ስልጣን አላቸው፡፡ እናም የመሪዎቻቸውንም ደንነት ያናውጣሉ፤ የዚህም ውየጤት የሚሆነው ስጋትንና ፍርሃትን በመንግስታት መካከል ይፈጥራል፡፡
ይህ ማለት ልክ አሁን በአለም ላይ ያለውን ሁኔታ ለማለት አይደለምን?
አንዴ ደግመን እንመልከት ክርስቶስ የነገረን አለም ልክ በእርሱ እንደተገለፀው አይነት ክስተቶችንቸ ስታሲተናግድ የእርሱን መምጫ መሆኑን መጠበቅ ግድ ይላል፡፡
“በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።” (ሉቃ 21፣ 27)
በምድር ላይ የሚመጡ ግጭቶች
ክርስቶስ ለተከታዮቹ ነገሮችን ሁሉ በማስተዋልና ነቅተው እንዲጠብቁ እስጠንቅቋቸዋል፡፡
“ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።” (ማቴ 24፣ 42)
የአለማችንን ሁኔታ እንደምንመለከተው፤ ምን አናያለን? እስራኤልን እንደምኛያት በሕዝቅዕኤል መዕራፍ 37 ውስጥ ያለውን ትንቡት ተፈፅሞ ወደ ምድራአው ተመልሰዋል፡፡ ከየአቅጣጫው በእስራኤል ላይ የሚነሱባትን ተቃውሞ እያየን ነው፡፡ የአረብ ና ሙስሊም ህዝቦች አንድ ላይ በመሰባሰብ በእግዚአብሔር ህዝብ ላይ ተነስተዋል፡፡ እናም አነርሱን ለመርታት ለረጅም ጊዜ እየጣሩ ነው፡፡
“ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።” (መ.ዳዊ 83፣ 4)
ሌላም ተጨማሪ ትንቢቶች አሉ፡፡ ወደፊት ስለሚኖረው ጦርነት የሚያሳዩ፡
“አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።” (ት.ዘካ 14፣ 2)
“አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፤………ጕልበቶች ስለ ምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለ ምን ጠባሁ?” (መ.ኢዮ 3፣ 9 ና 12)
ይህም ቀን አግዚአብሔር በሰዎቸወ ጉዳይ ላይ ዳግመኛ ጣልቃ የሚገባበትና በምድር ላይ የራሱን ዓላማ ዕውን ያደርጋል፡፡
“የፈረሰውን ለራሳቸው ከሚሠሩት ከምድር ነገሥታትና መካሮች ጋር፥” (መ.ኢዮ 3፣14)
“ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ።” (መ.ኢዮ3፣16-17)
እነዚህም ወቅቶች የሚመሩን ወደ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ነው እርሱም የምድር መሪ ይሆናል፤ ብዚ ነብያቶች በተለይ እዩኤልና ዘካሪያስ ያቀረቡልን የእግዚአብሔርን ዕቅድ ነው፡፡ በመጨረሻም የማጠቃለያ ግጭት ቀን ይመጣል ይህም በመፅሐፍ ቅዱስ “አርማጌዶን” በመባል ይታወቃል ፡፡ይህም ካለፈ በኋላ ፡-
“እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።” (ት.ዘካ 14፣9)
የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ዕውነታ
በጊዜያችን የምናያቸው ምልክቶች፤ እንደተመለከትነው የእግዚአብሔርን ዕቅድ አይለወጥም እናም እንደምናምነው የኢየሱስ ክርስቶስ ቀርቧል - አለምን በሚያስገርም መልኩ ለመውሰድም ተዘጋጅቷል፡፡
ምልክቶቹን በመመልከትና ትርጉማቸውን በማወቅ፤ በእነዚህ ነገሮች ተማርከን ባለመውሰድ ፀንተን ባለንበት መቆየት የቅተናልን? ለእነዚህ ነገሮች በሚያሳዝንና ሞኝነት በተሞላበት አኳኍን አይመሮአቸውን ዘግተው ምንም እንደማይስሩት ይቻለናል፡፡ ለነዚህም ሰዎች ክርስቶስ ልክ በጨለማ እንደሚመጣ ይሆንባቸዋል፡፡
ባንፃሩም ምልክቶችን ከግምት ውስጥ እያስገባን እናም ጊዜው ሳይረፍድብን ለማስጠንቀቂያዎቹ ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል፡፡ “ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።” (ሉቃ 21፣28) አሁን ባሉት ሁኔታዎች ከመማረክ ይልቅ ቀና ብለን መመልከት እንችላለን እናም ስለ ድነታችንም ቸስፈላጊነትም እናያለን፤ ይህም በአዳኛችን በሆነው በክርስቶስ ነው፤ “የታላቁ እግዚአብሔርን ታላቅ ቀን” ክፍዎችም ከዚያን በፊት ይጠፋሉ፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ ለኛ ዘላለማዊ ሕይወትንና በእግዚአብሔር መንግስት ቦታን ሰጥቶናል ይህም መንግስት በፅድቅና በሠላም ክርስቶስ ይነግሣል፤ ይህም “ንግስና በልብ ባለ ክብር” ሣይሆን ነገር ግን ዕውነተኛ መንግስት በምድር ላይ ይሆናል፡፡ ለመዘጋጀት መወሰን የእኛ ምርጫ ነው፡፡
አስተዋዮች ከዚህ ድምዳሜ ሊደርሱ ይችላሉ፡-
-
የክርስቶስ መምጣት እጅጉን አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡
-
የእግዚአብሔር ማስጠንቀቂያ ቃላት ሊተውና ሊዘነጉ አይገባም፡፡
-
አሁን ያለን ሕይወት ዘላለማዊ እርካታን አይሰጠንም፡፡
-
በወንጌል ወይም በምስራች ዜና በእግዚአብሔር መንግስት ማመንና እና በአዳኛችን ክርስቶስ ስም መጠመቅ እጅጉን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ምክንያቱም ዘላለማዊ ሕይወትን የምንፈልግ ከሆነ፡፡
ማጠቃለያ
-
የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት እወነት ነው፡፡
-
ይህም ዳግመኛ ስለ መምጣቱ በእርገቱ ወቅት በመላዕክት ቃል ተገብቷል፡፡
-
ኢየሱስ ተመላሶ ሲመጣ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መንግስት ይመሰርታል፡፡
-
ማናችንም ብንሆን ትክክለኛውን የክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን አናውቅም፡፡
-
ምልክቶች በግልፅ እንደሚያሳዩን የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት አጅጉን ተቃርቧል፡፡
-
የኖህ ዘመን ከእኛ ጋር ይነፃፀራል አይሁዳውያን ወደ እስራኤል መመለሳቸው የምናየው ምልክት ነው፡፡
-
አሁን እየኖርን ያለነው በናቡከደነፆር ራዕይ የመጨረሻው ክፍል ነው፡፡
-
የአለማችን አለመረጋጋትን የሚከተለው የክርስቶስዳግም መምጣት ነው፡፡
ለንባብ የቀረቡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ት.ዳን 2 ፤ ት.ሕዝ 37 ፤ ማቴ 24 ፤ የሐ.ሥራ 1፣ 1-2 ፤ የሐ.ሥራ 35 ፤ 1ኛ ተሰሎ. 4
ትምህርት ክፍል 9፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
የኢየሱስ ዳግመኛ ወደዚህች ምድር ስመጣ ዋነኛ አላመው ምንድነው
ሀ. እርሱ ተመልሶ አይመጣም ሐ..እግዚአብሔርን መንግስት ለመመስረት
ለ. ጦርነትን ለማስቆም መ. በሽተኞችን ለመፈወስ
-
የኢየሱስ ዳግመኛ መምጣት ምን ይመስላል
ሀ. እርሱ ተመልሶ መጥቷል
ለ. ሁሉም ያዋል
ሐ. የእርሱ ዳግመኛ መምጣት ምናባዊ ነው - በአማኞች ልብ ነግሷልና
መ. በሚስጢር ተመልሶ ይመጣል እናም እውነተኛ አማኞች ብቻ ያዩታል
-
ኢየሱስ ሲናገር የምመጣበት ቀን የሚያውቀው ማን ብቻ ነው ብሎ ነበር
ሀ. መላዕክት ለ. ኢየሱስ ሐ. ዕግዚአብሔር መ. ጳውሎስ
-
ኢየሱስ በቶሎ እንደሚመጣ የሚያሳየንን ምልክቶች ከየት እናገኛለን
ሀ. ከመፅሐፍ ቅዱስ ለ. ከወረቀት ሐ. ከክዋክብት መ. ከህግ
-
በማቴዎስ 24፣ 32-33 ካለው የበለስ ዛፍ ምሳሌ ምን እንማራለን
ሀ. የበለስ ዛፍን እናሳድጋለን ሐ. ኢየሱስ ዳግመኛ እንደመጣ
ለ.የኢየሱስን ዳግመኛ መምጣት መቃረብን ያሳየናል መ. ምንም አይነግረንም
-
የደረቅ አጥንት ሸለቆ ራዕይ ምን ያሳየናል
ሀ. ክንድእስራኤልን እንደሚያጠፋ ሐ. አይሁዳውያን ወደ እስራዜል መመለስ
ለ. የፍፃሜ ቀን መቃረቡን መ.በአርማጌዶን ብዙዎች ይሞታሉ
-
የኖህ ዘመን ምን ይመስል ነበር
ሀ. ሠላማዊ ሐ. ሁላቸውም እግዚአብሔርን እንደሚወዱ
ለ. ብዙ የመርከብ አምራቾች መኖራቸው መ. የአመፅና የብጥብጥ
-
ይህም እንዴት የኢየሱስን መቅረብ ያሳየናል
ሀ. የኖህ ዘመን ከክርስቶስ ዳግም መምጣት መቃረብ ጋር ይመሳሰላል
ለ. የቀስተ ዳመና ምልክት የክርስቶስን ዳግም “መምጣት ያሳያል
ሐ. ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የለም
መ. ዛሬም በተለያዩ ቦታዎች የጥፋት ውሃ አለ
-
ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ምን እነዲያደርጉ ነግሮአቸዋል
ሀ. በመመልከት ለእርሱ መዘጋጀት ሐ. የአለም ሙቀትን መቆጣጠር
ለ. ዕለት በዕለት ጋዜጣ ምንበብ መ. ምንም አልነገራቸውም
-
ከሚከተሉት ምልክቶች ውስጥ የኢየሱስን በቶሎ መምጣት ዛሬ የሚያሳየን ምንድነው
ሀ. አይሁዳውያን ወደ እስራኤል መመለስ ሐ. የብጥበጥ ና ሁከት ወራት
ለ. የአለም አለመረጋጋት መ. የተወሰኑ ኃያላንና ክፉ ህዝቦች መኖር
ትምህርት ከፍል 10፡ ወንጌል
በዚህ የትምህርት ክፍል የምንመለከተው በባለፉት የትምህርት ክፍሎች የተማርናቸውን ዕውነታዎች በአንድ ላይ በማጠቃለል ይሆናል፡፡ “ወንጌል” የሚለው ቃል ትርጉም “የምስራች ዜና” ማለት ነው፡፡
የክርስቶስ ማዕከላዊ ትምህርት
ማቴዎስ፣ ማርቆስ እና ሉቃስ ሁሉም የሚነግሩን በእስራኤል ምድር በመዘዋወር ስለ መንግስቱ መቅረብ ወንጌል (የምስራች ዜና) ሰብኳል፡፡
-
“ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።” (ማቴ 9፣35)
-
“ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።” (ማር 1፣14)
-
“እርሱ ግን፦ ስለዚህ ተልኬአለሁና ለሌሎቹ ከተማዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል አላቸው።” (ሉቃ 4፣43)
ኢየሱስ ስለ የምስራቹ ዜና ደቀመዛሙርቱን ባስተማረበት ፤ እነሱን ሌሎችን እንዲያስተምሩ ልኳቸዋል፡-
-
“ሄዳችሁም። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ።” (ማቴ 10፣7)
-
“ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ፥ ብዙ አጋንንትንም አወጡ፥” (ማር 6፣12)
-
“የእግዚአብሔርንም መንግሥት እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ላካቸው፥” (ሉቃ 9፣2)
ከሞቱና ትንሣኤ በኋላ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ተመሣሣይ ስራን እንዲሰሩ ነግሯቸዋል፡፡
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” (ማቴ 28፣19)
“እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።” (ማር 16፣15-16)
ከዚህ የመጨረሻ ቃላት እንደምናየው ማወቅ ያለብን ድነትን ለማግኝት ወንጌልን ማመን እና መታዘዝ ይኖርብናል፡፡
የወንጌል ስልጣን
ምክንያቱም ይህ ወንጌል ሕይወትን ወደ እኛ ያመጣል፤ ሐዋሪያው ጰውሎስ እንደፃፈው፡ “በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።” (ሮሜ 1፣16)
ኢየሱስና ሐዋሪያቱ ያስተማሩንን የምስራች ዜና በግልፅ ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ጳውሎስ ደግሞ እንደፃፈው፡ “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።” (ገላ 1፣ 8)
ደቀመዛሙረርቱ ስለ “ወንጌል” ምን ተረድተዋል?
ከኢየሱስ ስቅለት በፊት ደቀመዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት የምስራች ዜና በመዘዋወር ሰብከዋል፡፡ ይህ “የምስራች ዜና” ለእነርሱ ምን ማለት ነበር? ከትንሣኤው ሁለቱም ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፡ “እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት። በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤……..እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።” (ሉቃ 24፣ 19 ና 21)
ኢየሱስ ወደ ሠማይ ከማረጉ በፊት ደቀመዛሙርቱ ጠይቀውታል፡ “ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤” (የሐ.ሥራ 1፣6) እነርሱም ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት እዛውና አሁኑኑ ይመሰርታል ብለው ጠብቀው ነበር፡፡ እንዲህ ሣለ መልካም ዜና በፍጥነት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡ ኢየሱስም እንደነገራቸው ጊዜው እንዳልደረሰ ነበር፡፡
“እርሱም፦ አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤” (የሐ.ሥራ 1፣7)
የእገዚአብሔር ቃል ኪዳን
ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ ሲያርግ በሚያዩበት ወቅት ሁለት መላዕክት ከፊታቸው በመቆም ነግረዋቸዋል፡፡
“ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” (የሐ.ሥራ 1፣ 11)
ይህ ቃልኪዳን በሐዋሪያት ሥራ ና መልዕክት ላይ እንደምናነበው የሐዋሪያትን ትምህርትን በመድገም አንድ የሚያደርግ ነው፡፡ እነርስም የኢየስሰን ዳግመኛ መምጣት የእግዚአብሔርን ስለ መንግስቴ የገባውን ቃልኪዳን መፈፀም ይጠባበቁ ነበር፤ ምክንያቱም “ወንጌል” የሚለውን ቃል የምናገኝው በአዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ስለ እግዙአብሔር መንግስት መምጣት የምስራች ዜና የእግዙአብሔር ሁሉም ቃል ኪዳን ከመጀመሪያው ጀምሮ መሠረት ነው፡፡
“እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።” (የሐ.ሥራ 3፣ 19-21)
-
ወንጌል በኤደን
በመጀመሪያ አዳምና ሔዋን የእግዙአብሔርን ትዕዛዝ ከተላለፉ በኋላ ለዕባቡ እርሱ የሰጠው ቃላት “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”(ኦ.ዘፍ 3፣15)
ይህ የምስራች ዜና ነበር ይህም የኃጥያትና ሞት ስልጣን የሚጠፋበት ሁኔታ መኖሩን ያሣየናል፡፡ ይህንንም ኢየሱስ መጥቶ ስርቶታል፡፡ ዕብ 2፣ 14-15 እንመልከት፡፡
“እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” (ዕብ 2፣14-15)
-
ወንጌል ለአብርሃም
እግዙአብሔር ለአብርሃም የገባለትን ቃልኪዳን ተምረናል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደፃፈው፡ “እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።” (ኦ.ዘፍ 3፣8)
ኢየሱስ ሲመጣ አብርሃምን ከሞት ያስነሣዋል እናም ሁሉም እግዙአብሔር ለአብርሃምና ለዘሮች የገባውን ቃልኪዳን ምንም ሳይቀር ይፈፅማል፡፡
እነዚህም ቃልኪዳን ለይሣቅ ና ለያዕቆብ ተገብቶላቸዋል ኣናም ኢየሱስ ዳግመኛ ሲመጣ እነርሱም ከሞት ይነሣሉ እናም በእግዙአብሔር መንግስት የክብር ቦታን ይጎናፀፋሉ (ማቴ 8፣11)
-
ወንጌል ለዳዊት
የምስራች ዜና ስለ እግዙአብሔር መንግስት ለዳዊት በነብዩ ናታን በኩል ተነግሮታል፡፡
“ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥ መንግሥቱንም አጸናለሁ።እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ ሰው በሚቀጣበት በትርና በሰው ልጆች መቀጫ እገሥጸዋለሁከፊቴም ከጣልሁት ከሳኦል እንዳራቅሁ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም።ቤትህና መንግሥትህም በፊቴ ለዘላለም ይጠነክራል፥ ዙፋንህም ለዘላለም ይጸናል።” (2ኛ ሣሙ 7፣ 12-16)
እስራኤላውያንም በመጨረሻም እግዙአብሔርን ይፈልጋሉ፤ እርሱም ቃልኪዳኑን አይረሳም፡፡ በመዝሙረ ዳዊት ደጋግመን እንደምናገኝውና በነብያት መፃህፍት ስናነብ እናገኛቸዋለን፡፡ እግዙአብሔር በነብዩ ሕዝቅኤል በኩል የመጨረሻው የየሁዳ ንጉስ ለነበረው ለዘዳቂያ እንደተነገረው “ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደርጋታለሁ ፍርድ ያለው እስኪመጣ ድረስ ይህች ደግሞ አትሆንም፥ ለእርሱም እሰጣታለሁ።” (ት.ሕዝ 21፣27)
ኢየሱስ በመጣ ጊዜ መልዓኩ ለማርያም ቃልኪዳኑን አድርሷል፡፡ “እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።” (ሉቃ 1፣32-33)
-
ወንጌል ለእኛ
ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናውቀው ስለእግዙአብሔር መንግስት መምጣት ይህ የምስራች ዜና ነው፡፡ ኢየሱስ በቶሎ ወደ ምድር የእግዙአብሔርን መንግስት ለመመስረት ተመልሶ ይመጣል፡፡ ማቴ 25 ን እናንብብ፡፡ በዚህ መዕራፍ ሶስት ምሳሌዎች በእግዙአብሔር መንግስት ተካፋይ እንድንሆን ያስተምረናል፤ ለዚህም የተዘጋጀን መሆን ግድ ይላል፤ ለእግዙአብሔር እንስራ እናም የክርስቶስን ፍቅር እናንፀባርቃለን፡፡
-
ስለ አስሩ ዳናግላን ምሳሌ (1-13)
እራሳቸውን ያዘጋጁ እናም ዝግጁ ስለነበሩ ወደ ጋብቻው ስነ-ስረዐት ተጋብዘዋል ነገር ግን እነዚያ ዘየታቸው ያለቀባቸው በሩ ተዘግቶባቸዋል፡፡ እኛም እንደተነገረን በመዘጋጀት ነቅተን መጠበቅ የግድ ይላል ምክንያቱም እኛ ኢየሱስ መቼ እንደሚመጣ አናውቅም (ማቴ 24፣42 ና 44)
-
የስጠታ ምሳሌ (ቁጥር 14-30)
እግዙአብሔር በሰጠን ችሎታችን መጠቀም በኢየሱስ እንድናስተውል ነግሮናልና እርሱም በዕውቀታቸውና ዕጣ ፍነታቸው በሚችሉበት ወቅት ከተጠቀሙበት ይሸልማቸዋል፡፡
-
በጎቹን የከፋፈለው እረኛ ምሣል(ቁጥር 31-16)
መልካም እረኛ በጎቹን ያውቃቸዋል እናም አቅማቸውን ያውቃል (በተጨማሪማ የሐ 10፣ 1-6 እንመልከት)
ማን በአከባቢያቸው ያሉትን ሠዎች ለመርዳት ምን ያህል ጥረዋል የሚለውን እርሱ ያውቃል እናም ይህን ድጋፍ ልክ ለእርሱ እንደተደረገለት አድርጎ ይቀበለዋል፡፡
ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
ንስሓ መግባት ይኖርብናል፤ ይህም ማለት መንገዳችንን መቀየር ማለት ነው፡፡
“ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።” (ማር 1፣15)
“እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።” (የሐ.ሥራ 3፣19-20)
“እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።” (የሐ.ሥራ 17፣ 30-31)
ልባችንንም አይመሮአችንንም ለመቀየር ኢየሱስን መከተል ይኖርብናል፡፡ በጥምቀትም ዳግመኛ መወለድ ግድ ይለናል፡፡ በቀጣዩም ትምህርት ክፍል ይህን እንማራለን፡፡
“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።……እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።” (ገላ 3፣27ና29)
ይህ ወንጌል ነው፤ የእግዙአብሔር መንግስት የምስራች ዜና እኛም እንደ ደቀመዛሙርቱ በቶሎ እንዲፈፀም እንመኝ፡፡ ለዚህም ነው ስንጸልይ ኢየሱስ ለተከታዮቹ እንዳስተማረው፡ “መንግስትህ ትምጣ” የምንለው፡፡
“አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።” (ሉቃ11፣2-4)
ማጠቃለያ
-
“ወንጌል” የሚለው ቃል ትርጉም የምስራች ዜና ማለት ነው፡፡
-
ስለ እግዙአብሔር መንግስት የምስራች ዜና የኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ዋናው የጋራ ትምህርት ነው፡፡
-
ወንጌልን ማወቅ፤ ማመን እና ለእርሱ መታዘዝ ለድነት አስፈላጊ ነው፡፡
-
ወንጌል በአዲስም ሆነ በብሉይ ኪዳን ቅዱስ መጽሐፍ በሙሉ ያተምራል፡፡
-
ስለ የምስራች ዜና አሁንም እየተሰበክን ነው፡፡
-
የወንጌልን መልዕክት ካዳመጥን፣ ከተረዳን እና ከተገነዘብነት በእግዙአብሔር መንግስት ቦታ ይኖረናል፡፡
-
ልክ እንደ አብርሃም ና ሁሉም ያለፉ ታማኝ የእግዙአብሔር አገልጋይ ለወንጌል ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል፡፡
ለንባብ የቀረቡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
2 ሣሙ 7 ፤ መ.ዳዊ 96 ፤ ት.ኢሳ 55 ፤ ማቴ 25 ፤ ማር 16 ፤ የሐ.ሥራ 9 ፤ ገላ 3
ትምህርት ክፍል 10፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
ወንጌል የሚለው ቃል ትርጓሜ ምንድነው
ሀ. ዜና ለ. የምስራች ዜና ሐ. መንግስት መ. መልዕክት
-
ከሚከተሉት በውስጥ ኢየሱስ ስለ መንግስቱ ወንጌል ያስተማረንን በየትኛው ቁጥር ላይ እናገኛለን
ሀ. ማር 1፣14 ለ. ሉቃ 3፣16 ሐ. ማር 4፣18 መ. ማቴ 9፣35
-
ከኢየሱስ በተጨማሪ ስለ ወንጌል ማን አስተምሯል
ሀ. የአይሁድ ካህናት ሐ.የሮማውያን ገዠዎች
ለ. ደቀመዘሙራን መ. ጠቢባን ሠዎች
-
የእግዙአብሔር መንግስት በምድር ላይ መቼ ይመስረታል
ሀ. አናውቅም ሐ. ተመስረቷል
ለ. ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ መ. አይመሠረትም
-
ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ እየሱስ ወደ ሠማይ ሲያርግ እንደተመለከታችሁት እንዲሁ ተመልሶ ይመጣል ያላቸው ማን ነው
ሀ.እግዙአብሔር ሐ. ኢየሱስ
ለ. አንድ መላዕክ መ. ሁለት መላዐክት
-
በመጽሐፍ ቅዱስ የተገቡልንን የድህነት ቃልኪዳን እንዴት እናገኛለን
ሀ. ለጓደኞኣእን መልካም በማድረግ
ለ. ሁሉንም ቁሳቁሳችንን በጋራ በመጠቀም
ሐ. ለሀገርን ህግ ተገዢ በመሆን
መ. ወንጌልን በማወቅ፣ በማመን እና በመታዘዝ
-
ከእግዙአብሔር ቃልኪዳን ውስጥ የኃጥትና ሞት ድል መንሣት ቀድሞ የነገረን ማን ነው
ሀ. በኤደን የተሠጠን ቃልኪዳን
ለ. ለአብርሃም የተገባለት ቃልኪዳን
ሐ. ለኖህ የተገባለት ቃልኪዳን
መ. ለዳዊት የተገባለት ቃል ኪዳን
-
ለአብረሃም ስለ ወንጌል መሠበኩን የሚነግረን የአዲስ ኪዳን ጥቅስ የትኛው ነው
ሀ. ሮሜ 3፣8 ለ. ሮሜ 8፣3 ሐ. ገላ 3፣8 መ. ገላ 8፣3
-
ለዳዊት የምስራች ዜና ስለ እግዙአብሔር መንግስት የነገረው ነብይ የቱ ነው
ሀ. ዳንኤል ለ. ኢሳያስ ሐ. ኤሊያስ መ. ናታን
-
ደቀመዛሙርቱ ተዘዋውረው ይሰብኩ የነበረው ምንድነው
ሀ. ስለ ነፍስ ህያውነት
ለ. በሽታን ወዲያውኑ እንዴት መፈወስ እንደሚቻል
ሐ. ጊዜው ሲደርስ ኢየሱስ እነደሚነግስ
መ. ስለ ንስሃ እና ስለ እግዙአብሔር መንግስት መምጣት
ትምህርት ከፍል 11 ፡ ጥምቀት
ባጠናቀቅነው ትንህርት ክፍል እንዳየነው ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ሲል አዟቸዋል፡፡ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” (ማቴ 28፣19) ስለዚህም ይህ ጥምቀት ምን ማለት ነው እናም ለምን ይጠቅማል?
ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው?
“መጠመቅ የሚለው” ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት የግሪክ ቋንቋ “ባብቲዞ” የሚለውን የሚወክል ሲሆን የዚህም ትርጉም መስመጥ፤ ወደ ታች መውረድ ወይም ሙሉ በሙሉ በፈሳሽ ወስጥ መነከር ማለት ነው፡፡ በግሪክ ይህ ቃል የሚያመላክተን አንድን ነገር ቀለም የመንከርን ዘዴ ለማሣየት ይጠቀሙበታል፤ አንድን ቁስ ቀለም ለመንከር ሙሉ በሙሉ በቀለም ውስጥ ይኖርታል፤ ስለዚህም የዚህ ቁስ ቀለም ሙሉ በሙሉ ይቀየራል፡፡
የዚህ ቃል አጠቃቀምን በአዲስ ኪዳን ላይ በግልፅ እንደሠፈረው ውሃን መርጨት ወይም ውሃን በአንድ ሠው ላይ ማፍሰስ በቂ አለመሆኑን ይነግረናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥምቀት የሚፈልገው በውሃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መነከርን ነው፡፡ ስለዚህም ፊሊጲስዮስ ላይ ስናነብ ኢትዮጲያዊውን ጃንደረባ ሲጠመቅ “ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም።” (የሐ.ሥራ 8፣38)
ደግሞም መጥምቁ የሐንስ በኤኖን ሣሊም አቅራቢያ ሲያጠምቅ እንዳነበብነው፡ “ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥” (የሐ 3፣23)
የድነታችን ሁኔታ
በጨረስነው የትምህርት ክፍል እንደተመለከትነው በውነጌል ማመን እና ማወቅን ተከትሎ የሚመጣው ለትምህርት ከፍል 10 ትዕዛዛት መገዛት ነው፡፡ ይህም ለድነታችን አስፈላጊ ይሁናል፡፡ከትንሠኤው በኃላ ኢየሱስ የተናገራቸውን ቃላት እንደምናነበው፡ “እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።” (ማር 16፣ 15-16)
እኛም እንዳየነው ይህም ትክክለኛ ጥምቀት መከናወን ያለበት አንድ ወንድና ሴት የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትና መገዛት ስችሉ ነው፤፤ በተጨማሪም እኛ በእግዚአብሔር ተቀባይነትንም ለማግኝት አስፈላጊ ሁኔታ ነው፡፡
የቆርኖሊዮስን ምሳሌ ወስደን መመልከት እንችላለን፤ የሮማው የጦር አዛዥ የነበረ ሲን በየትኛውም ደረጃ ቢለካ “መልካም” ሆነ ሠው ነበር፡፡ (የሐ.ሥራ 10፣2 እንመልከት) እና በኋላም እግዚአብሔር ጴጥሮስን እንደሚልክለት ነግሮታል፡፡
“እንግዲህ ያን ጊዜ ኢየሱስ በግልጥ። አልዓዛር ሞተ፤” (የሐ.ሥራ 11፣14) ጴጥሮስም መጥቶ ቆርኖሊዮስን ስለ ኢየሱስ አስተምሮታል፡፡
“ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።” (የሐ.ሥራ 10፣42-43)
አሁንም ቢሆን አንድ ነገር አስፈላጊ ነው፡፡
“በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።” (የሐ.ሥራ 10፣48)
ከዚህና ከሌሎች የሐዋሪየት ሥራ ከተጻፉት በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው እግዚአብሔር ሶስት ለድነታችን አስፈላጊ የሆኑ ሁኔታዎችን አስቀመጦልናል፡ ዕውቀት፣ እምነትና ጥምቀት (በእርግጥ ሕይወታችን እግዚአብሔር መንገድ ቀጣይነት ባለው መልኩ መኖር ይኖርብናል፡፡) የሐ.ሥራ 2፣37-38 ና 41 ፤ የሐ.ሥራ 8፣35-38 ፤ የሐ.ሥራ 16፣25-33
“ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።” (የሐ.ሥራ 8፤12)
የጥምቀት አስፈላጊነት
አዲስ ኪዳንን በጥንቃቄ ብናነብ ስለ ጥምቀት አስፈላጊነት አራት ነጥቦች፡
-
ቆሻሻችንን ያስወግድልናል ፤ ያነጻናል
“አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ።” (የሐ.ሥራ 22፣16)
“ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ……ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።” (1ኛ ቆሮ 6፤9ና 11)
ተመሳሳይ ምልክትን በብሉይ ኪዳንም እናገኛለን፡፡ የአንድን ስዕል ቀለም ከመቀየር ጋር በማያያዝ
“ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ ክፉ ማድረግን ተዉ፥ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ ክፉ ማድረግን ተዉ፥ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።” (ት.ኢሳ 1፣16-18)
-
ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር በማያያዝ
በጥምቀት ጊዜ ሙሉ በሙሉ እራሣችንን ውሃ ውስጥ በምንነክርበት ጊዜ ሞቱን ሰንሞት ከውሃው ተመልስን ስንወጣ ደግሞ በአዲስ ሕይወት መነሣታችንን ምሣሌ ነው፡፡ በዚህ መንገድ እራሳችንነ ከኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ጋር እናመሣስላለን፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስም ለሮማውያን ስለዚህ ነገር ፅፎላቸዋል፡፡
“ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤” (ሮሞ 6፣ 3-5)
በጥምቀት ምናባዊ ሞትንና በአዲስ ሕይወት መነሣትን እናከናውናለን፤ የባህሪ ለውጥ ማምጣታችን ለእግዚአብሔር መታዘዝ አስፈላጊው ክፍል ነው፡፡
ኢየሱስ እንደተናገረው፡ “እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።” (የሐ 3፣5) ጳዉሎስ ለቆላሲያስ አማኞች ስለ ጥምቀት ፅፎላቸዋል፡፡
“በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ።እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ።” (ቆላ 2፣ 12-13)
-
ሁላችንም በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ አንሆናልን
እኛ ለክርስቶስ ጥምቀት አንድ እንሆናለን ስለዚህም ከክርስቶስ ጋር በእርሱ በኩል የተገባልን ቃልኪዳን እንወርሳለን፡፡
“አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።” (1ኛ ቆሮ 12፣ 12-13)
“እንኪያስ ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ እወቁ።…..ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር። ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን። ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።……በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤…………ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።” (ገላ 3፣ 7 ፤16፤ 26-29)
ጳወሎስ ደግሞ ለኤፌስዮን በጥምቀት ወቅት ስለሚኖረን ለውጥ ፅፏል፡
“በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።………….እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።” (ኤፌ 2፣12-13 ና 19)
-
የመምህራን ለውጥ - የመለየት ጥሪ
2ኘቆሮ 6፣ 14-18 ፤ የሐ2፣ 15-17 ፤ እናንብብ
“ስለዚህም ጌታ። ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።” (2ኛቆሮ 6፣17)
እግዚአብሔር በአለም ላሉ ጣኦት አምላኪዎች ደስተኛ አይደለም፤ በተፈጥሮ ወንድና ሴትየሐጥያት ባሪያ ናቸው፡፡ እኛም ስንጠመቅ አገልግሎታችን ይለወጣል፡፡
“ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤……….እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤…….ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ።ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።” (ሮሜ 6፣ 6-7 ና 11-12 ና 16-18)
በጥምቀት ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ለዚህም የእግዚአብሔር የቃልኪደኑን ስጦታ የምንወርስበትን አዲድ ሕይወት እንጀምራለን፡፡
“አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፣ 22-23)
እኛም ስንጠመቅ ሙሉ በሙሉ የዚህችን ዓለም መንገድና የሠውን ጎዳና እንተዋለን በጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንገድ ለመምጣት መርጠኛል ማለት ነው፤ ለወንጌሉም ታዛዥ መሆን የተነገረንን “ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔርን ድነትን፣ ስልጣንን” ያገኛል፡፡
የኖህ ምሣሌ
ኖህ ያደረገው ይህን ነበር፡፡ በእርሱ ዘመን የነበረችው አለም በብጥብጥና ክፋት የተሞላች ነበር፡፡ ኖህም ጀልባን ስርቶ ቀሪዎኡ አለም እንዳለ በጥፋት ውሃ አልቀዋል፤ ኖህና ቤተሠቦች ወደ መርከቢቱ ገብተው መትረፍ ችለዋል፡፡
“ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤” (1 ኛጴጥ 3፣20-21)
በክፉዎች የሚፈረድባቸው ክርስቶስ በድንገት በመምጣት ሲሆን እናም በመጨረሻውም በኖህ ዘመን እንደነበረው ይሆናል፡፡ ልክ ኖህ በመርከቧ ሁኖ መትረፍ እንደቻለ ሁሉ እኛም በክረስቶስ ውስጥ ከሆንን እኛም ድነትን እናገኛለን፡፡ እንደተመለከትነው በክርስቶስ መሆን መንገዱ በዕቀት፣ በእምነት፣ ጥምቀትና ቀጣጥይነት ያለው ታዛዥነት ናቸው፡፡
ጥምቀት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
ብዙዎች እንደሚሰማቸው የሕይወት መንገዳቸውን ወደ ተሸለ መንገድ መለወጥ እስከፈለጉ ድረስ ወደዚህ ድረጊት መሸነፍ አይኖርባቸውም፡፡ በሚያሳዝን መልኩ ስህተትን ያደርጋል እናም ትክክለኛ ነገርን ለመስራት የሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ውጤታማ አይደለም”፡፡ የሲሪያውን ናማን ክስትተ እንመልከት (2 ነገ 5) የእግዚአብሔር ሰው የሆነው ነብዩ ኤልሳ በዮርዳኖስ ወንዝ ታጥቦ ከለምፅ በሽታ ተጥቦ እንዲድን ነግሮታል፡፡ በመጀመሪያም አልተቀበለውም ነበር ነገር ግን አገልጋዮቹ ከእግዚአብሔር የተስጠውን ግልፅ ትዕዛዝ እንዲያደርግ ሲወተውቱት የተባለውን በማድረግ በእንዲት ቅፅበት ሊፈወስ ችሏል፡፡
“ኤልሳዕም። ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ ሥጋህም ይፈወሳል፥ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ።ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፥እንዲህም አለ፦ እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን? ዘወርም ብሎ ተቈጥቶ ሄደ።ባሪያዎቹም ቀርበው። አባት ሆይ፥ ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር ይልቁንስ። ታጠብና ንጹሕ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ! ብለው ተናገሩት።ወረደም፥ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ።” (2ኛ ነገ 5፣ 10-14)
እኛም በተቻለን አቅም ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል ከታዘዝን ፈውስ አግኝተን አዲስ ሕይወት ይኖረናል ነገር ግን ከጥምቀት በኋላ ለምንፈፅመው ስህትተ እና ኃጥትስ? ቀደም ሲል እንደተመለከትነው፤ በጥምቀት ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ ጋር እንመሣሰላለን፤ ይህም ክሰተት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጥያት የተከፈለ መስዋዕትነት ነው፡፡ እናም በክርስቶስ አዲስ ሕይወተወነወ ከጀመርን በኋላ ለምንፈፅመው ስህተታችን በሙሉ ለአዲስ ለድነታችን መሠረት ለሆነን በፀሎት ይቅርታን ማግኝት እንችላለን፡፡ እኛ ተፀጽተን እና የእግዚአብሔርን ይቅርታ ስንጠይቅ ኃጥያታችን በሙሉና ስህተታችን ከመዝገባ ይጠፋል አናም ስለዚህ እያንዳንዷ ቀን ወደፊት ከእግዚአብሔር ጋር መሔድ ይቻላል፤ ትክክለኛ ነገርን ለመስራት መሞከርን ቁጥር በራስ መተማመናችን ይጨምራል፤ እግዚአብሔርን ለይቅርታ ከጠየቅነው ቃል በገባልን መሠረት ይቅርተውንና አርነቱን ይለግሰናል፡፡
“በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”( 1ኛየሐ 1፣ 9)
እግዚአብሔር ለየት ያለ ዕድልን በቃሉ እንደሠጠን፤ ሕይወታችንን በድጋሚ እንደ አዲስ ለመጀመር ፍላጎት ይኖር የሆናል፤ ስህተት ከመስራት ልምዳችን እና ከቀድሞ ጨለማ ሕይወታችን የተወሰነውን ለማጥፋት ፍላጎት ቢኖረን፤ለዚህም እጅግ የተለየ ግሩም ዕድል የሠጠን ስለሆነ መጀመር ያስችለናል፡፡ነገር ግን በዚህ ወቅት ወደ መቃብር ሚመራን መንገድ ላይ ሣይሆን ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚመራን ጎዳና ላይ ሰንሆን በዚህም የእግዚአብሔርን መንግስት ክብር እናያለን፡፡የእግዚአብሔር መንገድ ብቸኛው ወደ ፈጣሪያችን የምንሰባሰብበት መንገድ ነው፡፡
“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (የሐ.ሥራ 4፣12)
ይህም የጥምቀት አስፈላጊነት ነው፡፡ ይህም አስፈላጊው የመታዘዛችን ውሳኔ ሲሆን ከእግዚአብሔርም የድነት መንገድ ዋነኛው አካል ነው፡፡
ማጠቃለያ
-
ኃጥያታችን ታጥበው ይወገዳሉ፡፡
-
ከጌታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር እንመሣሰላለን
-
እኛም በክርስቶስ አንድ እንሆናለን ስለዚህም የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን በክርስቶስ እንቀበላለን፡፡
-
የስለጠነብንን በመቀየር ከሃጥያት ተገዢነት ይልቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንሁናለን እናም እራሳችንን
-
ከአለም እንለያለን
ለንባብ የቀረቡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ኦ.ዘፍ 6-8 ፤ ማር 16 ፤ የሐ.ሥራ 8 ና 10 ፤ ሮሜ 6
ትምህርት ክፍል 11፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
“ጥምቀት የሚለው ቃል ትርጉም?
ሀ. መርጨት ለ. ማፍሰስ ሐ. መነከር መ. ማርጠብ
-
ኢትዮጵያዊውን ጃንንደረባ ያጠመቀው ማን ነው?
ሀ. ስቴፈን ለ. ጳውሎስ ሐ. ፊሊፕ መ. በርናባስ
-
በመፅሐፍ ቅድስ ለደቀመዘሙረቱ ስለ ወንጌል ስብከት የተሰጣቸውን ትዕዛዝ የሚያሳየን የትኛወ ጥቅስ ነው?
ሀ. ማር 15፣ 15-16 ለ. ማር 16፣ 15-16 ሐ. ማር 5፣ 15-16 መ. ማር 6፣ 15-16
-
ከእነዚህ መካከል ሶስት የተጠመቁትን ለይ?
ሀ. ጲላጦስ ለ. ጳውሎስ ሐ. የፊሊፒንሱ እሰር ቤት ጠባቂ መ. ሊዲያ
-
እውነተኛ ጥምቀት የሚፈፀመው መቼ ነው?
ሀ. በውልደት ጊዜ ሐ. ትምርተ ስንጨርስ
ለ. በሞት ጊዜ መ. የ እግዚአብሔርን የማዳን ዓለማ ሙሉ በሙሉ ተረድተን ስናምን
-
የጥምቀት ድርጊት ምንን ይወክላል?
ሀ. ትክክለኛውን የሠው ሞት ሐ. የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ
ለ. የእግዚአብሔርን ስጦታ መ. የኖህን መርከብ
-
በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትኛው መዕራፍ ነው የጥምቀትን ትርጓሜ የሚበረራራልን?
ሀ. ሮሜ 6 ለ. ሩት 4 ሐ. ራዕይ 6 መ. ቆላ 4
-
ጴጥሮስ አያይዞ የጥምቀትን ድርጊት በትይዩ ያቀረበው ከየትኛው ክስተት ጋር ነው?
ሀ. በዘፀአት ላይ ቀይ ባህርን መሻገራቸው
ለ. ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመሄድ ዮርዳኖስን ማቋረጣቸው
ሐ. በምድረበዳ ውሃ ስላመነጨ
መ. በጥፋት ውኃ ወቅት በኖህ የተስራችው መርከብ
-
ከመጪው የእግዚአብሔር መንግስት ቡታን ለማግኝት እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው?
ሀ. ፍቅር ለ. ማመንና መጠመቅ ሐ. እምነት መ. ታማኝነት
-
የምንጠመቀው ለምንድነው?
ሀ. መጠመቅ አይኖርብንም
ለ. መክንያቱም ሰባኪው ስለተናገረን
ሐ. መጽሐፍ ቅዱስ አውንደሚነግረን ለኃጥያታችን ስርየትን ለማግኝት
መ. ምክንያቱም መልካም ስለሚመስል፡፡
ትምህርት ከፍል 12፡ የእግዚአብሔር መንግስት
ክርስቶስ ዳግመኛ ሲመጣ ና ቀደም ሲል ባየናቸው ትምህርቶች መሠረት ሁሉም ምልክቶእ የሚያሳዩት ይህም በቅርብ እንደሚሆን ነው፡፡ የእርሱም የመጀመሪያ ስራ የሚሆነው ሙታንን ማስነሣት ነው፡፡
“በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።” (ት.ዳን 12፣ 2)
“በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤” (1ኛ ተሶሎ 4፣ 15-16)
ይህንንም ትንሣኤ ተከትሎ ፍርድ ይሆናል፤ የዘላለም ሕይወትንም ፃድቃን ያገኛሉ፤ እነርሱም በእግዚያብሔር መንግስት አጋዥ ይሆናል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልኪዳን አንደሚያሳየን የክርስቶስ መንገስ በአሁኑ ወቅት አለምን የሚበዘብዙ ከፉዎች ፍፃሜን ያሳየናል፡፡
በመንግስቱም የሚኖረው ሁኔታ
“በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።” (ት.ኢሳ 2፣ 4)
“እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንምነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።” (ት.ኢሳ 11፤ 3-4)
“በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።” (ት.ኢሳ 35፣ 5-6)
“በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።ደረቂቱ ምድር ኵሬ፥ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆ ደንገልም ይሆንበታል።” (ት.ኢሳ 35፣ 6-7)
“እነሆ፥ አራሹ አጫጁን፥ ወይን ጠማቂውም ዘሪውን የሚያገኝበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር ተራሮችም በተሀውን የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ይቀልጣሉ።” (አሞ 9፣ 13)
“በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል።ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤” (1ኛ ቆሮ 15፣ 24-26)
“እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።” (ራዕ 21፣ 4)
ስለዚህ ስለ እግዚያብሔር መንግሰት ትምህርት ለምን ወንጌል እንደተባለ ግልፅ ነው፤ ቀደም ሲል እንደተማርነው ወንጌል ማለት የምስራች ዜና ማለት ነው፡፡
የድነት ጎዳና
ከትንሣኤው በኋላ ኢየሱስም ደቀመዛሙርቱን እነዚህን ተዕዛዝ በመስጠት ልኳቸዋል፡ “እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።” (ማር 16፣ 15-16)
ማየት እንደምንችለው ጥምቀት የግድ መከተል ያለበት በወንጌል ከማመን ቢሆንም የመጨረሻውንም ቁጥር በሚገባ ማስተዋል ይኖርብናል “ያላመነ ግን ይፈረድበታል”
በጴንጤቆስጤ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ትንሣአኤ እና ስለ ዳግም መምጣቱ ተስፋ ተናገሯል፡፡ አብዛኞቹ ይህ መልዕክት ደርሷቸው ያዳመጡ በንግግሩም በመመሰጥ እነዲሁ ምን ማድረግ በእንዳለባቸው ጠይቀዋል፡፡ ንሰሃ በመግባትና መጠመቅ እንዳለባቸው ነግረአቸዋል፡፡ ንስሐ ማለት አሁን ዕያደረግን ካለነው ነገር መለወጥ ማለት ነው - አዲስ ሕይወት መጀመር፡፡
“ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።” (የሐ.ሥራ 2፣ 41-42)
የህንኑ ትዕዛዝ እናስተውል፤ መረዳትና ማመን ሚከተለው በጥምቀት መታዘዝን ነው ይህንንም ተከትሎ እግዚያብሔር በሚያስደስት መልኩ በሙሉ አቅማችን በፈቀደው ሁሉ አማኞች እርሱን የእርሱን የሕይወት ጎዳና መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ የተጠመቁ ክርስቲያኖች እንዲህም ተብሎ የተነገራቸው፡፡ (ቆላ 3፣ 1)በእርግጠኝነት የጌታን መምጣት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡
“እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ።በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና።ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።” (ቆላ 3፣ 1-4)
ይቅር ባይነት
ክርስቶስን በምንጠባበቅበት በዚሀ ወቅት ላይ እያለን ክርስቲያነ ስህተትን ቢፈፅም ይቅርታን ከጠየቀ እግዚያብሔር ይቅር እንደሚለው ያውቃል፡፡ እናም ኢየሱስም እረሱን ችግር የተጋራ፤ ከእግዚያብሔርም የሚያስማማ ሊቀካህናት ነው›› ምክንያቱም ፈተና ምን ማለት እንደሆነ እሱም ያውቀዋል፡፡ ወደ ዕብራውያን መልዕክት ላይ እንደምናገኝው እኛ እንደምንፈተነው የእኛ የካህት አለቃ የሆነውም እንደተፈተነ እንድናስታውስ ያደርፈናል፤ እርሱም መቋቋምችሎ እናም ኃጥያትን አላደረገም (ዕብ 4፣ 15) ክርስቲያኖችም ይህ ፀሎት እንደሚሰማላቸው እርግጠኛ ናቸው፡፡ (ማቴ 21፣ 22 ና 1 የሐ 3፣ 22 ና 5፣14)
“እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” (ዕብ 4፤ 16)
የእግዚያብሔር ስጦታ
በራሳችን አቅም ሕይወታችንን በእግዚያብሔር መንገድ መኖር አንችልም ይህ የሚሆነው በእግዚያብሔር ፍቅር ና ቸርነት ብቻ በክርስቶስ ድነትን እናገኛለን፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው ጳውሎስ ሲፅፍ “ኤፌ 2፣ 8”
“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፣ 23)
ቀጣዩ ደረጃ
አሁን አስራ ሁለቱነ ትምህርት አጠናቀናል፡፡ ይህ ትምህርት የተብራሩ የመፅሐፍ ቀዱሰ ስለ እግዚያብሔር ምን እነደሚያስተምር እና ለዚህች ምድር ስላለው አላማ በግልፅ አይተንበታል፡፡
እኛም ልክ እንደተወሰኑ የአቴንስ ሠዎች እነዚህም ጳውሎስን አድምጠውና፡ “የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኵሌቶቹ አፌዙበት፥ እኵሌቶቹ ግን። ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን አሉት።” (የሐ.ሥራ 17፣ 32) በሌላ አገላለፅ አድምጠዋል ነገር ግን በትምህርታቸው መቀጠል የፈለጉ አልነበሩም፡፡
በልላ በኩል ሐዋሪያው የጎበኛቸው እንደ ቤሪአ ሕዝቦች እንመስል ይሆናል እነርሱም፡ “እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።”(የሐ.ሥራ 17፣ 11) የትኛውም የሠዎች አይነት ውስጥ እንካተት፤ እስካሁን የእግዚያብሔርአላማ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ ጴጥሮስም እንደፃፈው በመጨሻው ቀናት ሰዎች የክርስቶስን ዳግመኛ መምጣት ያጣጥሉታል፡፡ ጴጥሮስ እንደተናገረው የኖህ ስብከት ላይ ያጉለመርማል፡፡ ነገር ግን የተባለችው ቀነወ ስትመጣ ዝናብ ይጀምራል፡፡ በተመሣሣይ አካሔድ ሰዎች አስተዋሉ ወይም አላስተዋሉም “የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።” (2ኛ ጴጥ 3፣ 10)
ልዩ መልዕክት ለእናንተ
ሐዋሪያቱ ይህን መልዕክት ሲደመደሙ ይህን እንድናስታውስ በማድረግ ነበር፡፡ “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።” (2ኛ ጴጥ 3፣9)
እግዚያብሔር ኢየሱስን መልሶ ይልከዋል እና መንግስቱን ይመስርታል፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው ይህን ዕድል እንዲያጣው አይፈልግም፡፡ ሁላችንም ምርጫችንን መወስን አለብን በመንግስቱ ተካፋይ ለመሆን ወይም አለመሆን እናም ይህን ካደረግን የኢየሱስን “የተከተሉኝ” ጥሪ መቀበል ግድ ይላል፡፡ “ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።” (ማቴ 9፣ 9) ይህንንም ምረጫ ለመወሰን ለእያንዳንዱ ተማሪ ሊተው ይገባል፡፡ አናንተም ይህን ጥሪ እንደምትቀበሉ ሙሉ እምነት አለን፡ “ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥” (2ኛጴጥ 3፣ 14)
ማጠቃለያ
-
የድነት መንገድ በእምነት፣ በመጠመቅ እና በመታዘዝ ነው፡፡
-
ከጥምቀት በኃላ በጸሎጽ ለኃጥያታችን ይቅርታን ማግኝት እንችላለን፡፡
-
እግዚያብሔር ሁላችንም መንግስቱን እንድንወርስ ይፈልጋል፤ ነገር ግን እርሱን መከተልና መታዘዝ የእኛ ምርጫ ነው፡፡
ለንባብ የቀረቡ ጥቅሶች
ት.ኢሳ 65፣ 17-25 ፤ ት.ኢሳ 66፣ 1-2 ፤ ኤፌ 2 ና 5 ፤ ቆላ 3 ፤ ዕብ 11 ፤ 2 ጴጥ 3
ትምህርት ክፍል 12፡ ጥያቄዎች
ትክክለኛ የሆነውን መልስ ከስር በማስመር ቀጥሎም ለመልስ መስጫነት በቀረበው የመልስ ወረቀት ላይ ትክክለኛውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡ ጥያቄዎቹ ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሊኖራቸው ስለሚችል መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን ምረጡ፡፡
-
ኢየሱስ ወደ ምድር ተመልሶ ሲመጣ የመጀመሪያው ስራው ምን ይሆን?
ሀ. ለሁሉም ሠው መምጣቱን መናገር ሐ. ለሁለሀም ደስታ መስጠት
ለ. ሙታንን ማስነሳት መ. ክፉዎችን ማጥፋት
-
በእግዚያብሔር መንግስት የትኛውን ሁኔታ እናገኛልን?
ሀ. ምንም አይነት በሽታ ና ጦርነት አይኖርም ሐ. በዝባዥ ና ሙሠኛ መንግስት
ለ. ምንም አይነት ርሐብና ድርቅ አይኖርም መ. በቂ የሆነ ምግብ መኖር
-
ጴጥሮስ በጴንጤቀስጤ ቀን ለህዝቡ ሲናገር ለመዳን ምን አድርጉ ብሏቿል?
ሀ. በሠሩት ኃጥያት ማዘን ሐ.ለመዳን ምንም አናደርግመ
ለ. ምንም፤ እግዚያብሔር ሁሉን ያድናል መ. ንስሀ ገብተን መጠመቅ
-
አንድ ተጠመቀ አማኝ ሕይወቱን እንዴት መኖር ዘለበት?
ሀ. በገዳም
ለ. በአርምሞ፤ በመለየት
ሐ. እግዚያብሔርን በሚያስደስት
መ. ጠቃሚ ስራ በመስራት
-
ክርስቲያን እንዴት ይቅርታን ይጠይቅ?
ሀ. በጥናታዊ ፅሁፋ ሐ. በልግስና
ለ. በመስዋዐትነት መ. በጸሎት
-
በሮሜ 6 ያለው ስጦታ የሚያመላክተው ማንን ነው?
ሀ. ዘላለማዊ ሕይወትን በኢየሱስ ሐ. መፅሐፍ ቅዱስ
ለ. ተፈጥሮ መ. ወቅቶች
-
በአቴንስ የነበሩ የተወሰኑ ሠዎች ጳውሎስን ስብት ሲሰሙ ምን አደረገጉ?
ሀ. ተጨማሪ ወደፊት እንስማለን አሉ ሐ. ጳውሎስን አመሰገኑት
ለ. ጳወሎስን ወገሩት መ. ጳውሎስን አከበሩት
-
በቤሪያ የነበሩ ስዎች የጳውሎስን ስብከት ስስሙ ምን አደረጉ?
ሀ. የምስጋና መዝሙር ዘመሩ
ለ. ዕለት ተዕለት ቅዱሳት መፅሐፍትን ፈለጉ
ሐ. ሰበኩ
መ. ንብረታቸውን ሁሉ ሸጡ
-
ስለ እግዚያብሔር መንግስት የሚነግረን ጥቅስ የቱ ነው?
ሀ. ት.ኢሳ 65፣17-25 ለ. ማቴ 9፣9 ሐ. የሐሥራ 2 መ. ራዕ 21፣4
-
የትኛው ሐዋሪ ነው ምንም አይነትበደልን በእግዚያብሔር ፊት እንዳንሰራ የመከረን?
ሀ. ጳውሎስ ለ. ፊሊፕ ሔ. የሐንስ መ. ጴጥሮስ